Get Mystery Box with random crypto!

#ቱርክ የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን የሱዳን ጦርነት እንዲቆም ሁለቱንም ተፋላሚ ኃይሎች | ebstv worldwide📡☑️

#ቱርክ
የቱርክ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን የሱዳን ጦርነት እንዲቆም ሁለቱንም ተፋላሚ ኃይሎች ለማደራደር ሀገራቸው ዝግጁ መሆኗን ይፋ አደረጉ።

ኤርዶሀን ከሱዳን ጦር ኃይል አዛዥ ከጄኔራል አብደል ፈታ አል ቡርሃን ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት በሱዳን የቀጠለው ግጭት አሳሳቢ መሆኑን ነግሬአቸዋለሁ ብለዋል ::
ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን በሱዳን የአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ሰዎች ድጋፍ ለማቅረብ ከመንግስታቱ ድርጅት ጋር እየመከሩ መሆኑን ነው አር ቲ የዘገበው ።

*********
የቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሀን ለቱርክ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ማድረጋቸውን አስታወቁ።
ፕሬዝዳንቱ ለ700ሺ የመንግስት ሰራተኞች የሚከፈለውን ደሞዝ በ45 ከመቶ መጨመራቸው የተሰማው በአገሪቱ ከ 3 ቀናት በኃላ ከሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ቀደም ብሎ ነው።
ኤርዶሀን፣ “ከዚህ በኋላ የመንግስት ሰራተኞች በዋጋ ግሽበት ምክንያት የሚጐዱበት ጊዜ አይኖርም፤” ሲሉ ተደምጠዋል ከውሳኔው በኋላ፡፡
ዘገባው የአር ቲ ነው፡፡

#አሜሪካ
ግዙፉ የአሜሪካው ጐልድ ማን ባንክ መድልኦ አድርሶባቸዋል ለተባሉ ሴት ሰራተኞቹ የ 215 ሚሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ ለመፈፀም መስማማቱ ተሰማ።

የባንኩ 2 ሺ 8 መቶ የቀድሞ ሴት ሰራተኞቹ ባንኩ የሚከፍለው ደሞዝ ላይ አድሏዊ አሰራር ፈፅሞብናል ሲሉ በአውሮፓውያኑ 2010 የመሰረቱት ክስን ተከትሎ ነው ባንኩ የካሳ ክፍያውን ለመክፈል የተስማማው፡፡
የቀድሞ የባንኩ ሰራተኞች የክስ ሂደትን የተከታተሉት አሊሰን ጋምባ የተባሉት ጠበቃ ውሳኔው የሴቶችን የእኩልነት ጥያቄ የሚመልስ ሆኖ አግኝቼዋለሁ ብለዋል።
ዘገባው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው፡፡