Get Mystery Box with random crypto!

#ዩክሬን የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም በሩሲያ እና | ebstv worldwide📡☑️

#ዩክሬን
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል የሰላም ውይይት ይደረጋል ብለው እንደማይጠብቁ አስታወቁ።

ዋና ፀሐፊው ጉቴሬዝ ዩክሬንም ሆነ ሩሲያ በወታደራዊ እርምጃዎች ብቻ ጥቅማቸውን ለማስከበር መወሰናቸው እና ለውይይት ዝግጁ ባለመሆናቸው ነው የድርድር ተስፋ እንደማይታያቸው ያስታወቁት፡፡

ጉቴሬዝ ለአስተያየታቸው ምክንያታቸውን ሲያቀርቡ ሩሲያ ከያዘቻቸው የዩክሬን ግዛቶች ለመልቀቅ አለመፈለጓና ዩክሬን ደግሞ በሞስኮ የተያዙባትን ግዛቶች በኃይል አስመልሳለሁ ማለቷ ድርድር የሚባል ነገር እንዳይታሰብ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት በበኩላቸው ቻይና የዩክሬን ጦርነት እንዲቆም ይረዳል ያለችውን የሰላም ሀሳብ ይዛ መምጣቷን ተቃወመውታል፡፡
ዘገባው የአር ቲ ነው፡፡