Get Mystery Box with random crypto!

#ሩሲያ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዓለማችን እጅግ ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች አ | ebstv worldwide📡☑️

#ሩሲያ
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ዓለማችን እጅግ ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ደርሳለች አሉ።

ፑቲን አክለውም ምዕራባዊያኑ በሩሲያ ላይ የከፈቱትን ጦርነት በድል አድራጊነት እንደሚወጡ ተናግረዋል ።
ፕሬዚዳንቱ ሩሲያ ናዚ ጀርመን ላይ ድል የተቀዳጀችበት የድል በዓል ላይ ባደረጉት ያለ ንግግር የጀርመን ናዚዎችን የተዋጋነውን ያህል ዛሬም የሩሲያን ነጻነት ለማስከበር ተገቢውን ተጋድሎ እናደርጋለን ብለዋል ።
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

#አሜሪካ
በአሜሪካ ባለፉት አምስት ወራት ውስጥ ብቻ በጦር መሳሪያዎች በተፈፀሙ የጅምላ ግድያዎች 14ሺ 6 መቶ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።

በተያዘው የአውሮፓውያኑ 2023 ያለፉት 5 ወራት ውስጥ በአሜሪካ 199 የጅምላ ግድያዎች ሲመዝገቡ 93 ህፃናትን ጨምሮ 14 ሺ 6 መቶ አሜሪካውያን በጅምላ ግድያዎቹ ህይወታቸውን ማጣታቸው ነው የተገለጸው፡፡
በቴክሳስ ግዛት አንድ ታጣቂ በፈፀመው ጥቃት በትንሹ 8 ሰዎች መገደላቸው ነው የተነገረው፡፡
ዘገባው የቲአር ቲ ወርልድ ነው፡፡

******************

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያው ፌስቡክ በወር አንዴ የትስስር ገፁን የሚጐበኙ ተጠቃሚዎቹ ቁጥር 3 ቢሊዮን መድረሱን አስታወቀ።

የፌስቡክ የማህበራዊ የትሰስር ተጠቃሚዎች በአብዛኛው እድሜቸው የገፋ መሆኑ ሲነገር ኩባንያው በተለይ ወጣት ተጠቃሚዎችን የትስስር ገፁ ደንበኛ ለማድረግ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም ማቀዱ ተነግሯል፡፡
በአሜሪካ እድሜያቸው ከ18 እስከ 34 ያሉ ወጣቶች ውስጥ 46 ከመቶ የቲክ ቶክ መተግበሪያ የሚጠቀሙ ሲሆን ፌስቡክን የሚጠቀሙት 28 ከመቶ ብቻ እንደሆኑ አንድ ጥናት ጠቁሟል።
ዘገባው የአሶሼትድ ፕሬስ ነው።

******************

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ከአየር ንብረት ለውጥ በባሰ ሁኔታ በሰው ልጆች ላይ አደጋ ሊደቅን እንደሚችል አንድ ሳይንቲስት ተናገሩ፡፡

“የሰው ሰራሽ አስተውሎት የጡት አባት” በመባል የሚጠሩት ጆፍሬይ ሂንተን የሰዉ ሰራሽ ቴክኖሎጂ ከአየር ንብረት ለውጥ በከፋ ሁኔታ ለሰው ልጅ አደጋ ሊሆን እንደሚችል ነው የገለጹት፡፡
ሳይንቲስቱ ጂኦፍሬይ ሂንተን የሰዉ ሰራሽ አስተውሎት የሚያስከትላቸውን አደጋዎች በነጻነት ለመግለፅ ስል ከግዙፉ የአልፋቤት ኩባንያ በገዛ ፈቃዴ ሥራዬን ለቅቄአለሁ ብለዋል።
የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ውስጥ የሚካተቱት እንደ ቻት ጂፒቲ ያሉት መተግበሪያዎች የተማሩ ሰዎች የሚሰሯቸውን ሥራዎች ሊተኩ የሚችሉ መሆናቸው ይበልጥ ስጋት አንብሯል፡፡

የትዊተር ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢሎን መስክንና የዘርፉ ምሁራን እንደ ቻት ጂፒቲ ያሉ የሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂዎች ላይ የ6 ወራት እገዳ እንዲጣል መጠየቃቸው ተነግሯል፡፡
ዘገባው የሲጂቲኤን ነው፡፡