Get Mystery Box with random crypto!

#አፍጋኒስታን አፍጋኒስታንን እያስተዳደረ ያለዉ ታሊባን የዛሬ 3 አመት በካቡል የደረሰውን የቦንብ | ebstv worldwide📡☑️

#አፍጋኒስታን
አፍጋኒስታንን እያስተዳደረ ያለዉ ታሊባን የዛሬ 3 አመት በካቡል የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ ያቀነባበረውን የአሸባሪውን የአይ ኤስ ኤስ መሪ መግደሉ ተሰምቷል ።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደሚሉት በታሊባን የተገደለው የአሸባሪው የአይ ኤስ ኤስ መሪው ሳኑላህ ጋፋሪ በአውሮፓውያኑ 2021 በካቡል መዲና የደረሰውን እና 170 ንፁሃን ዜጐች እና 13 የአሜሪካ ወታደሮች የሞቱበትን የቦንብ ፍንዳታ ያቀነባበረ ነው ።
አሜሪካ የአይ ኤስ ኤስ መሪ ሳኑላህ ጋፋሪን አድራሻ ለጠቆመ 10 ሚሊየን ዶላር ወሮታ እከፍላለሁ ስትል ከዚህ ቀደም መጠየቋ ይታወሳል፡፡
ዘገባው የቢቢሲ ነው ።
#ደቡብ አፍሪካ
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ሀገራቸው ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት " አይ ሲሲ" ልትወጣ መሆኑን አስታወቁ፡፡
ፕሬዚንዳንቱ ይሄን ያሉት ከፊንላንዱ ፕሬዚዳንት ሳዑሊ ሻይናሞ ኒሲቶ ጋር በኘሪቶሪያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ራማፎሳ የገዢው የ "ኤኤንሲ" ፓርቲ ደቡብ አፍሪካ ከዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ጠቅልላ እንድትወጣ ውሳኔ አሳልፏል ብለዋል።
ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በደቡብ አፍሪካ አዘጋጅነት በሚካሄደው የብሪክስ አገራት ጉባኤ ላይ በሚታደሙት የሩሲያው መሪ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣቱን ተከትሎ ደቡብ አፍሪካ ከፍርድ ቤቱ ለመውጣት ወስናለች ሲሉ ራማፎሳ ይፋ አድርገዋል፡፡
ዘገባው የሳባክ ቴሌቪዥን ነው፡፡
#ቻይና
ቻይና ከአሜሪካ በ4 አመት ቀደም ብላ በአውሮፓውያኑ 2030 በጨረቃ ላይ አዲስ የጠፈር ጣቢያ ልታቋቁም ማቀዷ ተሰማ፡፡
ቻይና ከ7 አመታት በኋላ በጨረቃ ላይ የራሷን የጠፈር ጣቢያ የማቋቋም ትልሟ ከተሳካ አሜሪካንን ቀድማ የመጀመሪያዋ ሀገር እንደምትሆን ነው የተዘገበው ።
ዘገባው የሜል ኦን ላይን ነው ።