Get Mystery Box with random crypto!

#ሱዳን የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን በቀጠለው ግጭት ሳቢያ ከአገሪቱ በ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች | ebstv worldwide📡☑️

#ሱዳን
የመንግስታቱ ድርጅት በሱዳን በቀጠለው ግጭት ሳቢያ ከአገሪቱ በ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ አስጠነቀቀ፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ቃለ አቀባይ ኦልጋ ሳራዶ ይሄን የተናገሩት ከሱዳን በትንሹ 20ሺ ዜጐች ወደ ቻድ መሰደዳቸውን እና ሌሎች በርካቶች ወደ ግብፅ እየተሰደዱ መሆኑን ለጋዜጠኞች ሲያብራሩ ነው፡፡
ኃላፊዋ አክለውም ግጭቱን ተከትሎ ወደ ጐረቤት ሀገራት ከተሰደዱት ሱዳናዊያን ባሻገር ሌሎች በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በአገር ውስጥ ተፈናቅለዋል ብለዋል ።
ዘገባው የአሶሺትድ ፕሬስ ነው።
*********

በእስር ላይ የነበሩት የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር እና ሌሎች በርካታ ባለስልጣናት ከማረሚያ ቤት መውጣታቸው ተነገረ።
በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን የወረዱት የሱዳን የቀድሞ የሱዳን መሪ አልበሽርና ሌሎች 30 ባለስልጣናት "ኮበር" ከተባለ ማረሚያ ቤት መውጣታቸውን አንድ ባለስልጣንን ዋቢ አድርጎ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።