Get Mystery Box with random crypto!

#ሕንድ ሕንድ በህዝብ ብዛት ቻይናን በልጣ የዓለም ቁጥር ቀዳሚ ሀገር ደረጃን መያዟ ተነገረ፡፡ ሕ | ebstv worldwide📡☑️

#ሕንድ
ሕንድ በህዝብ ብዛት ቻይናን በልጣ የዓለም ቁጥር ቀዳሚ ሀገር ደረጃን መያዟ ተነገረ፡፡

ሕንድ ከ1.4 ቢሊዮን ሕዝብ በላይ ያላትንና ላለፉት 73 አመታት በሕዝብ ብዛት ቀዳሚ የነበረችውን ቻይናን መብለጧን ነው የመንግስታቱ ድርጅት ያስታወቀው ።
በሕንድ በየእለቱ 86 ሺ ሕጻናት እንደሚወለዱ ሲነገር በቻይና ደግሞ 49 ሺ 4 መቶ ሕፃናት ምድሪቱን እንደሚቀላቀሉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
ሕንድ ቻይናን በአውሮፓውያኑ 2027 በህዝብ ብዛት ትበልጣለች በሚል ከተቀመጠው ትንበያ 4 አመት አስቀድሞ ነው መሪነቱን የተቆናጣጠችው፡፡
ዘገባው የዘ ጋርዲያን ነው፡፡

#አሜሪካ
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በአውሮፓውያኑ 2024 ለሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ ይፋ አደረጉ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በለቀቁት የቪዲዮ መልዕክታቸው ከ1 አመት በኋላ በሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደሚወዳደሩ ገልፀው ምርጫው በፈተና ውስጥ ያለውን የአሜሪካን ዴሞክራሲ በተግባር መታደግ ዋና ግቡ መሆኑን ገልጸው “የጀመርኩትን ጠንካራ ሥራ ከዳር ለማድረስ ምረጡኝ፤” ብለዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው፡፡

#ቡርኪናፋሶ
በቡርኪናፋሶ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 60 ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል።

የቡርኪናፋሶ አቃቤ ህግ ባወጣው መግለጫ በያቴንጋ ግዛት ባርጋ በተባለ አካባቢ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 60 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መጎዳታቸውን ነው የገለጸው።
የሀገሪቱ መንግስት ጥቃቱን ፈፅመዋል ብሎ በሚያስባቸው የፀጥታ ኃይሎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ትዕዛዝ ማስተላለፉን ኤ ኤፍ ፒ ዘግቧል።