Get Mystery Box with random crypto!

#ሱዳን የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ለ3ኛ ጊዜ ለ72 ሰአታት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታ | ebstv worldwide📡☑️

#ሱዳን
የሱዳን ተፋላሚ ኃይላት ለ3ኛ ጊዜ ለ72 ሰአታት የሚዘልቅ የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው ተሰማ።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ነው ጦርነት ውስጥ ያሉት አካላት ለ72 የሚዘልቅ ስምምነት እንዲደርሱ ማስቻላቸው ነው የተነገረው ።
ብሊንከን የሱዳን ጦር እና የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ሀይላት አዲስ ለተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተፈጻሚነት አበክረው እንዲሰሩ መጠየቃቸውን አልጀዚራ ዘግቧል።

******
የምስራቅ አፍሪካ አገራት በሱዳን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ዜጐቻቸውን ከሀገሪቱ ማውጣት ጀመሩ፡፡
ሶማሊያ ፣ ጅቡቲ እና ኬንያ በሱዳን ያሉ ዲፕሎማቶቻቸውን እና ዜጐቻቸውን እያወጡ መሆኑ ሲነገር የሶማሊያ 27 ዜጐች ከሱዳን ወጥተው ኢትዮጵያን ከሱዳን በሚያዋስነው መተማ መግባታቸው ነው የተዘገበው፡፡
ኬንያ በበኩሏ ከሱዳን የነበሩ 29 ዜጐቿን አስወጥታ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ማድረግ መቻሏን አናዶሉ ዘግቧል።

******
አሜሪካ ከሱዳን የሚወጡ ዜጎቿን ለመደገፍ የጦር መርከቦቿን በቀይ ባሕር ላይ ማስፈር መጀመሯን አስታወቀች።
ይህንን የተናገሩት ለኤቢሲ ኒውስ ቃለ መጠይቅ የሰጡት የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት ቃለ አቀባይ ጆን ኪርቢ ናቸው፡፡
እንደ ቃል አቀባዩ ገለጻ ሀገራቸው ዜጎቿን ከሱዳን ለማስወጣት የጦር መርከቦችን በፖርት ሱዳን አቅራቢያ እያስጠጋች ነው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አማካይነት በተዘጋጀ የበረራ ፕሮግራም በርካታ አሜሪካውያን ከካርቱም እየወጡ መሆኑንም ነው ጆን ኪርቢ አክለው የገለጹት፡፡