Get Mystery Box with random crypto!

የቀጠለ ... ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከመሠረተ ልማት ግንባታ በተጨማሪ ሌሎች የሰራቸው ስራዎች ፦ | EBS TV NEWS

የቀጠለ ...

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከመሠረተ ልማት ግንባታ በተጨማሪ ሌሎች የሰራቸው ስራዎች ፦

የተሳካ አገልግሎት ለማቀረብ አንዲሁም የሙያ እና የክህሎት ሽግግርን ለማጠናከር ብቃት ያለው የአመራሮች ሰብስቦ አዋቅሯል።

የሰው ኃብቱን ወደ 500 ያሳደገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 320ዎቹ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። በቀጣይም ከሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ ሠራተኞች እንዲኖሩት ለማድረግ እየሰራ ነው።

50 አዲስ ተመራቂ ተማሪዎችን መልምሎ ጊዜውን የዋጁ ኃሳቦችን እና መፍትሔዎችን ሊጠቁም የሚችሉ ዲጂታል የፈጠራ ክህሎት ያላቸው ኢትዮጵያዊያንን ለመፍጠር ጥረት እያደረገ ሲሆን ተጨማሪ 100 አዲስ ተመራቂዎችን ለመመልመል በልዩ ልዩ ክልሎች ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በትብብር እየሠራ ነው።

በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች ሊያዳርሱ የሚችሉ 29 አከፋፋዮችን በአቅራቢነት በመያዝ ድርጅቶቹ አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እየተሰራ ነው።

አገልግሎት መስጠት ለመጀመር ያዘጋጀነው ዕቅድ የችርቻሮ መደብሮችን እንዲያካትት በማድረግ በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ድርጅቶች ጋር አጋርነት ለመፍጠር የሚያስችሉ ጨረታዎች አውጥቷል።

ማህበራዊ ኮንትራቱን ማዘጋጀት የቀጠለ ሲሆን 'ዲጂታልን በመጠቀም ሕይወትን የማሻሻል' ርዕዩን በሚያሳካ መንገድ ለዚህ መሠረት ለመጣል የሚያስችሉ እቅዶችን አውጥቷል።

#SafaricomEthiopia

@EBS_TV_NEWS