Get Mystery Box with random crypto!

#MoE መንግስት ከ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ስርጭት ጋር በተያያዘ ከባድ ፈተናዎች ገጥሞት እን | EBS TV NEWS

#MoE

መንግስት ከ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ስርጭት ጋር በተያያዘ ከባድ ፈተናዎች ገጥሞት እንደነበር እና የፀጥታ ኃይሎችም ተሰውተው እንደነበረ ገለፀ።

ይህን የተሰማው ትምህርት ሚኒስቴር የ9ወር የአፈፃፀም ሪፖርቱን ለህ/ተ/ም/ቤት ካቀረበ በኃላ ከምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ነው።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰጠው ማብራሪያ በፈተና ስርጭት ወቅት እጅግ ከባድ የሚባል ፈተና እንደነበር ገልጿል።

" ስርጭት ሲባል ፈተናውን ማድረስ እና የፈተናውን የመልስ ወረቀት መመለስ ጭምር ያካታታል ያሉት " የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ፥ " በስርጭቱ ሂደት ከዚህ በፊታ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወደ 3000 የሚጠጉ የፈተና ጣቢያዎች (ንዑስ ወረዳ ድረሥ) ላይ ፈተና የደረሰ ሲሆን ከባለፉት ዓመታት በ3 እጥፍ ያደገ ነው " ብለዋል።

" ፈተና መፈተን እራሱ ፈተና ነው የሚያስብል ነገር ያጋጠመን ስርጭት ላይ ነው " ያሉት ም/ ዋና ዳይሬክተሩ ፥ " በብዙ ቦታዎች ላይ የክልል መንግስታት ፣ የክልል የፀጥታ ኃይሎች ዋጋ እየከፈሉ እየተሰው ያደረሱበት ቦታ አለ። " ብለዋል።

የፌዴራል ፖሊስ አባላትም የተሰውቡት ሁኔታ መኖሩን ገልፀዋል።

" አንድ፣ ሁለት ፈተና ጣቢያዎች ላይ ማድረስም አቅቶን እስከመጨረሻ ድረስ ፈተናው ላይ እርምጃ የተወሰደበት ሁኔታ ነው የነበረው። " ሲሉም አስረድተዋል። እርምጃውን ግን በግልፅ አላብራሩም።

ከዚህ ባለፈ የፈተናው የመልስ ወረቀት በሚመለስበት ጊዜ ከባድ ፈተናዎችም እንደነበሩ ተጠቁሟል።

" ከዚህ በፊት የተማሪዎች መልስ የሚመጣው በአውቶብስ ነው ፤ ዘንድሮ ግን የተማሪዎችን የመልስ ወረቀት ለማውጣት የፌዴራል ፖሊሶች የተሰውቡት ሁኔታ ነበር የነበረው " ብለዋል።

የተማሪዎችን የፈተና መልስ ወረቀት ይዘው ለመውጣት በነበረ ሂደት 3 የፌዴራል ፖሊስ መሰዋታቸውን ተገልጿል።

በ3 ጣቢያዎች ላይ ደግሞ አንድ ሳምንት ሙሉ የፈተናውን ወረቀት ማውጣት ያልተቻለበት በኃላ በሀገር ሽማግሌ የወጣትበት ሁኔታ ነበር ተብሏል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ፥ " ስርጭቱ ከባድ ፈተና ነበር ፤ በፈተና ክዘና ላይ፣ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት ያልተፈቀዱ ቁሳቁሶች ይዞ መገኘት ፣ ለሰው መፈተን ፣ ፈታኞችን Abuse የማድረግ በጣም ብዙ ቦታዎች ችግሮች ነበሩ። ይህ ችግር አንድ ክልል ብቻ ተብሎ የሚወሰድ ሳይሆን ሁሉም አካባቢ ነበር " ብለዋል።

@EBS_TV_NEWS