Get Mystery Box with random crypto!

' ወያኔም አልቻለም፤ ብልፅግናም አልቻለም ' - አቶ ጃዋር መሀመድ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ | EBS TV NEWS

" ወያኔም አልቻለም፤ ብልፅግናም አልቻለም " - አቶ ጃዋር መሀመድ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ከወራት በፊት ከእስር ከተፈቱ በኃላ በአደባባይ ንግግር ሲየደርጉ/ ሃሳባቸውን ሲገልፁ/ለሚዲያ ቃላቸውን ሲሰጡ አልተስተዋለም።

ባለፉት ቀናት በነበረው የፓርቲያቸው ጉባኤ ላይ ግን ንግግር አድርገዋል።

አቶ ጃዋር በንግግራቸው ሊበታትኗቸው የፈለጉ ኃይሎች ሁሉ ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ገልፀዋል።

አቶ ጃዋር መሀመድ " ' ይሄን ካላደረጋችሁ እናፈርሳችኋለን " ይሄን ወያኔም አልቻለም፣ ብልፅግናም አልቻለም። ሊበታትኑን በፍፁም አይችሉም። ኦሮሞን በፍጹም ማስፈራራት አይቻልም በፍጹም " ብለዋል።

"እኔ በራሴ ከኦፌኮ ከወጣክ ይሄን እናደርግልሃለን ፣ ይሄንን ካላደረክ እንደዚህ አናደርግም ብለውኛል " ያሉት አቶ ጃዋር " ሞተን እንገኛለን እንጂ ካመንበት ነገር ወደኋላ አንመለስም " ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለው፥ " ብልፅግና ከግማሽ በላይ ኦነግን ወስዶት እንኳን ኦነግን ማፍረስ አልቻለም። ኦነግ ፈርሷል? አልፈረሰም " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጃዋር፥ " ከቦረና፣ ከጉጂ የሚነሳውን ቅሬታ እንሰማለን፣ እንመካከራለን፣ እናስተካክላለን " ያሉ ሲሆን " እኔ ያልኩትን ካልወሰዳችሁ አርሲን ከዚህ አወጣለሁ፣ ሸዋን አወጣለሁ፣ ወለጋን ከዚህ አወጣለሁ ካልክ አንተ ነህ የምትወጣው እንጂ ጉጂም አርሲም አይወጡም " ሲሉ ተናግረዋል።

"እኔ OMN በነበርኩበት ሰዓት እንደዚህ አይነት ሙከራዎች ነበሩ " ያሉት አቶ ጃዋር " አንደዚህ ካላደረክ ከሀረርጌ የሚመጣውን ገንዘብ አንቆርጥብሃለን ከወለጋ የሚመጣውን ገንዘብ እንቆርጥብሃለን...ከቆረጣችሁ ትቆርጣላችሁ እንጂ የኦሮሞ አንድነት አይቆረጥም። ከተበታተንን እንበታተናለን እንጂ ወደኋላ አንመለስም" ብለዋል።

@EBS_TV_NEWS