Get Mystery Box with random crypto!

ከሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎች ተጠንቀቁ - የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ************ | EBC (Ethiopian Broadcasting Corporation)

ከሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎች ተጠንቀቁ - የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር
**************************

WinSCP (Windows Secure Copy) የተሰኘ የፋይል ማስተላለፊያ ፕሮቶኮልን በመጠቀም ተጠቃሚዎችን ዒላማ ያደረጉ አሳሳች እና ተንኮል አዘል ሶፍትዌሮችን በጉግል ማስታወቂያዎች ላይ በማጣበቅ ወደ ኮምፒውተራችን/ስልካችን እንድንጭናቸው ከሚያደርጉን አጭበርባሪዎች እንጠንቀቅ ሲል ‘ዘሃከር ኒውስ’ በድረ ገጹ አስነብቧል።

የሳይበር ጥቃት ፈፃሚዎቹ እንደ WinSCP ያሉ ሕጋዊ ሶፍትዌሮችን ለማውረድ የሚፈልጉ ተጠቃሚዎችን ተመሳስሎ የተሠራ ማልዌር እንዲጭኑ በማድረግ የተጭበረበሩ የፍለጋ ውጤቶችን እና ሐሰተኛ የጉግል ማስታወቂያዎችን እየጠቀሙ እንደሆነ ዘገባው አመላክቷል።

አጥቂዎቹ በተንኮል አዘል ማስታወቂያ አማካኝነት ተጠቃሚውን ወደ ተንኮል አዘል የዎርድፕረስ ድረ-ገጽ gameeweb[.]com ይመራዋል፣ ይህም ተጠቃሚውን በአጥቂው ቁጥጥር ስር ወዳለው የማስገሪያ (phising) ጣቢያ በመምራት መረጃዎችን ይዘርፉታል።

ተጨማሪ ለማንበብ ... https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=pfbid02KUibb2tnK5Zm2LftW7A7hVpJ3ubXD5xdBdh1TfntJHEkE7Mizc7WLuuFCJwaJLS4l&id=61550945701729