Get Mystery Box with random crypto!

ክርስትያኖ ሮናልዶ የሳውዲውን ክለብ ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደረሰ ኅዳር 21/2015 (ዋልታ) | EBC(Ethiopian Brodcasting Corboration(EBC)

ክርስትያኖ ሮናልዶ የሳውዲውን ክለብ ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደረሰ

ኅዳር 21/2015 (ዋልታ) ክርስትያኖ ሮናልዶ የሳውዲውን ክለብ አልናስርን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ መድረሱ ተዘገበ፡፡

የስፔኑ ማርካ እንዳስነበበው የአምስት ጊዜ የባሎንዶር ኮከቡ ክርስትያኖ ሮናልዶ ለሳውዲው ክለብ የሁለት ዓመት ከስድስት ወር ኮንትራት ለመፈረም ተስማምቷል፡፡

እንደመረጃው ከሆነ 137 ሚሊየን ዩሮ በዓመት የሚከፈለው ሲሆን በእግር ኳስ ተጨዋቾች ታሪክ ውዱ ክፍያ እንደሚሆንም ተነግሯል፡፡

የ37 ዓመቱ ተጨዋች የዓለም ዋንጫ ውድድሩ ሲጠናጠቀቅ ውሉን እንደሚፈፅም እና በይፋ የክለቡ ተጨዋች እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

እስከ 40 ዓመቱ መጫወት እንደሚፈልግ የሚናገረው ሮናልዶ ከፒርስ ሞርጋን ጋር ካደረገው አወዛጋቢ ቃለመጠይቅ በኋላ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በስምምነት መለያየቱ ይታወሳል፡፡