Get Mystery Box with random crypto!

#Endertas_Jok በመጀመሪያ ይሄን ፅሁፍ ለምታነቡ እንደኔ አይነ ስውር ለሆናቹ ድንግል አባቶ | ENDERTA'S JOKE 😀

#Endertas_Jok
በመጀመሪያ ይሄን ፅሁፍ ለምታነቡ እንደኔ አይነ ስውር ለሆናቹ ድንግል አባቶች ይሁንልኝ

ያው ከእለታት 68 ቀን ግንቦት 73 በተክልዬ ቀን እኔ ሙስሊሙ ወንድማቹ በ7 አመቴ ተወለድኩ

ያው በ70 ቀኔ አንዋር መስጊድ ክርስትና ተነሳው
የክርስትና እናቴም ተቀዳሚ ሙፍቲ ናቸው።

እናም ሙስሊም አርጎ የፈጠረኝን እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ ወደዋናው ጉዳይ ስገባ በበር በኩል ነው

እናም ይሄን ፅሁፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ የናቴ ጥፊ ነው

ግድግዳዬ ላይ ተጋድሜ ነበር በመዳፏ ጯ አረገችኝና ስሜን ረስቼ ተነሳው

እኔኮ ግን ወድጄ አደለም የምተኛው ደስ ብሎኝ እንጂ

ያው እረፍት የለኝም በቀን 24 ሰአት እየተኛው እንዴት ልረፍ?

ትናንት ራሱ ለሊቱን ሙሉ አልተኛውም

እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝኮ ለጥ ብዬ ነው ያደርኩት

ብቻ ምናለፋቹ ባለፈው ልደቴ ነበር
በተክልዬ ቀን

ያው ልደቴን ሚያከብርልኝ ባላገኝም
Insta ላይ እየፖሳሰቱ ሲያዝጉኝ ነበር

ምናለበት አዋታቹ የሆነ ነገር ብታረጉልኝ ከምትፖስቱኝ?

ደሞ ባለፈው ጡዘትነቶ 200k ሚያወጣው መኪና ይገባዎታልና እገዛሎታለው አለኝ

ከንቱ ወረኛ ወገኛ ...

እውነት ብታስቡልኝ 500k ሚያወጣውን ለምን አዋታቹ አገዙልኝም?

ስለ ሽልማት ሳወራ ግን አንድ ነገር ረሳው

የሚቀጥለው ወር ላይ የአንድ የኮዬ ፈጬ አህጉር ልጅ ገረመው አብዲሳ ሚባል ሰውዬ ነበር
እና ቁጭ ሀይለ ገብረ ስላሴን ነው ሚመስለው

እናም ሀይልሻ ይሄን አይቶ በጣም ተገርሞ
እውነትም ገረመው ስምን መላክ ያወጣዋል ብሎ ተደንቆ

ለልደቱ የቆርቆሮ ቤቱ ድረስ ሄዶ
ህይወቱን ቀየረው

አንድ ዘመናዊ ሆቴል
አንድ G+2 ዘመናዊ ቤት
2.5 ሚልዮን የሚያወጣ መኪና... እንዲኖርህ ከፈለክ ጠንክረህ ሩጥ ብሎታል

ሀይልሻኮ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሆን ራስ
ለህዝቡ ከመጨነቅ ይልቅ ከ ፕሬዝዳንት ደሞዝ ላይ ስንት ፐርሰንት ነው ታክስ የሚቆረጠው ብሎ ሚጨነቅ ስው ነው

ብቻ ያው እኔ ከራሴ በላይ ምወደው የለም
እናም እንኳን ተወለድኩ

ደሞ አሳማዬ በግ በግ እያለች ነው እስኪ ሀሳብ ነገር ስጡ
@E70jokes