Get Mystery Box with random crypto!

#update የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ህገወጥ የመሬት ወረራ ፣ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

#update

የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ህገወጥ የመሬት ወረራ ፣ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደሚኒየም ቤቶች፤ የቀበሌ መኖርያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በጥናት የተገኘው ግኝትቶች ላይ ዛሬ የውሳኔ ሃሳብ አሳልፏል።

በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንዲሆኑ ወስኗል።

በጥናቱ የተገኘው ህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ፤ ባዶ ሆነው የተገኙ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል ተወስኗል።

ይህ በዋናነት በ1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤ የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወቶላቸው ለደሆች፤ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ሰዎች ተነጥቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንሰጥ ሲሉ ወስነዋል፡፡

ምንጭ ፦ የአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ዕ/ቤት
@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot