Get Mystery Box with random crypto!

ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ቡናን ቆልቶ ፈጭቶ የሚያሽግ ዘመናዊ ፋብሪካ ተመረቀ። የኦሮሚ | ዶይቸ ቬለን | DW AMHARIC NEWS🇪🇹

ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ቡናን ቆልቶ ፈጭቶ የሚያሽግ ዘመናዊ ፋብሪካ ተመረቀ።

የኦሮሚያ የቡና አምራች ገበሬዎች ሕብረት ስራ ዩኒዬን በገላን ከተማ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያስገነባዉን ዋን ኮ ኮፊ 'ONE-KOO COFFEE' ቡናን ቆልቶ ፈጭቶ የሚያሽግ ዘመናዊ ፋብሪካ አስመርቋል።

ፋብሪካውን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ መርቀው ከፍተዋል። በተመሣሣይ መልኩ ወደ 50 ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ወጪ በቡሌ ሆራ ከተማ የተገነባዉ ዘመናዊ መጋዘንም ተመርቋል።

የዩኒዬኑ ምክትል ሥራ አስጂያጅ አቶ ደጀኔ ሂርጳ በ800ሺህ ብር ካፒታል የተቋቋመዉ ዩኒዬኑ ከ600 ሚሊዮን ብር ካፒታል ማፍራቱን ተናግረዋል።

የተመረቀዉ ዘመናዊ ፋብሪካም በኦሮሚያ ክልል የሚመረተዉን ቡና በዘመናዊ መንገድ ለሃገር ዉስጥና ለዉጪ ሃገር ገበያ ለማቅረብ ያስችላል ብለዋል።

@dwamharic_news
@dwamharicnewsbot