Get Mystery Box with random crypto!

ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል: የሸዕባን ግማሽ ሌሊት #ጥያቄ↶ አንዳንድ ዳእዋዎች ላይ | Ethio Muslims ☪️

ዶክተር ዛኪር ናይክ ቻናል:
የሸዕባን ግማሽ ሌሊት

#ጥያቄ↶

አንዳንድ ዳእዋዎች ላይ የሸዕባንን ግማሽ በፆም ሌሉቱን ደግሞ በኢባዳ ማሳለፍ በሀዲስ እንዳለ ሲናገሩ ሰምቼ ነበርና ሀዲሱ ትክክል ነውን

መልስ↶

በመጀመሪያ ደረጃ በሸዕባን ወር አጋማሽ ላይ ቀኑንም ሆነ ሌሊቱም በፆም እና በዒባዳ መለየት ዙሪያ የመጡት ሀዲሶች ከዶዒፍነት አልፈው በነብዩ     ላይ የተቀጠፉ ሀዲሶች መካከል የሚመደቡ ናቸው። ይህ በመሆኑም ሳቢያ በነዚህ ሀዲሶች መስራት ይቅርና ማስተላለፉም የተከለከለ ነው።

ለዚህም ሲባል በርካታ ዑለሞች ይህን ወቅት ቀኑንም ሆነ ሌሊቱን በማንኛውም የዒባዳ አይነት ልዩ አደርጎ የማሳለፍ ተግባር በሸሪዓችን መሰረት ከሌላቸው ቢድዓዎች መካከል እንደሚመደብ ተናግረዋል። ሆኖም በየወሩ አያመል_ቢድ (ሶስቱ አብሪ ቀናት) ማለትም የወሩን 13ኛ ፣  14ኛ እና 15ኛ ቀንን መፆም የተወደደ ከመሆኑ ጋር መፆም የፈለገ ከዚሁ ከሸዕባን ግማሽ ጋር ይገጥማልና አይቻልም አይባልም። አያመልቢድ መፆምን እስካሰበ ድረስ የተወደደ ተግባር ነው።



#ምንጭ↶

አልመውዱዓት ለኢብኑል ጀውዚይ ፣ 2/440–445
አልባዒሱ አላ ኢንካሪል ቢደዒ ወል ሀዋዲሲ  ፣ ለአቡ ሻመቲ አሽሻፊዒይ ፣ ከገፅ 124 –137 ‏
መጅሙዑል ፈታዊ ፣ ለኢብኑ ተይሚያህ ፣ 28/138
ፈታዋ ኢስላሚያህ ፣ ለኢብኑ ባዝ ፣ 4/511
አልባሂሱል ሀሲሱ ፣ ለኢህመድ ሻኪር ፣ 1/278

#share_share_Share_share

https://t.me/drzakirnaiki
https://t.me/drzakirnaiki