Get Mystery Box with random crypto!

የዚና (ዝሙት) አስከፊነት ================= «ዛሬ ዛሬ ዚና እንደስልጣኔ መገለጫ ሆኗ | Ethio Muslims ☪️

የዚና (ዝሙት) አስከፊነት
=================
«ዛሬ ዛሬ ዚና እንደስልጣኔ መገለጫ ሆኗል ቢባል ማጋነን አይሆንብነኝም»!!
||
ዚና እንደቀላል በየአካባቢያችን ይፈፀማል፣ ቦይ ፍሬንድ ገርል ፍሬንድ እየተባባሉ ያለ ኒካህ መገናኘት፣ መጨዋወት፣ ሻይ ቡና መባባል የተለመደ ሆኗል፣ ነውርነቱ ከህብረተሰቡ ላይ ተነስታል ሃያዕ፣ ሀፍረት (ጥብቅነት) የሚባል ነገር እንደ ኃላ ቀርነት እየታየ መጥቷል፡፡

ያለ ኒካህ እንዴት ብለህ ስትላቸው አክራሪ ወገኛ አድርገው  ያዩሃል፡፡
ዚና በመጨረሻ ዘመን እንደሚስፋፋ ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ጠቁመውናል:-
«ከቂያማ ቀን ምልክቶች እውቀት፣ ይነሳል፣መሀይምነት ይነግሳል፣ ዝሙት ይስፋፋል፣ አስካሪ መጠቶች ይጠጣሉ፣ የሴቶች ቁጥር ይበረክታል፣ የወንዶች ቁጥር ያንሳል፣ ለሃምሳ ሴቶች አንድ ወንድ እስከሚደርስ…»።
ቡኳሪ ዘግበውታል

አምለካችን አላህ እንዲህ ይላል:-
وَلَا تَقْرَبُوا الزِّنَا ۖ إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلًاَ۝
«ዝሙትን አትቅረቡ፣ እርሱ አፀያፊና መንገዱም የከፋ ነው»፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ኢስራዕ (32)

አላህ በዚህ የቁርአን አንቀፅ ዝሙትን
አስከፊነት በጥብቅ አስታውቋል፣

ዝሙት አፀያፊና መንገዱ የከፋ የሆነበት በዚህ በዱንያ በአኼራም አደገኝነቱ ከሌሎች ወንጀሎች ለየት
ያለ መሆኑ ነው፣ እዚህ ዱንያ ላይ ቅጣቱ
ይመለከታቸዋል፡

አብደላህ ኢብኑ አባስ «ዝሙት
የሚፈፅም ሰው አላህ የቀልቡን ኑር ብርሀን ይገፈዋል ብለዋል»፡፡ የቀልቡን ኑር የተገፈፈሰው የፊቱ ኑር ይጠፋል፡፡ በዚህችም በቅርቢቱ አለም አሰቃቂ አስከፊ በሽታ ይገጥመዋል፡፡

ነብያችን (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዳሉት «…ዝሙት እየተበራከተና እየተስፋፋ ሲመጣ ቀደምቶቻችሁ የማያውቁት ወረርሽኝ ይከሰታል»። ብለዎል።

ከዚህ አስቀያሚ ድርጊት እንድንርቅ የዛኒና የዛኒያ  የወንድና የሴት ዝሙተኛን ቅጣት እንዲህ ሲል ነግሮናል:-
الزَّانِيَةُ وَالزَّانِي فَاجْلِدُوا كُلَّ وَاحِدٍ مِّنْهُمَا مِائَةَ جَلْدَةٍ ۖ وَلَا تَأْخُذْكُم بِهِمَا رَأْفَةٌ فِي دِينِ اللَّهِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۖ وَلْيَشْهَدْ عَذَابَهُمَا طَائِفَةٌ مِّنَ الْمُؤْمِنِينََ۝
ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን (ያላገቡ እንደኾኑ) መቶ ግርፋትን ግረፉዋቸው፤ በእነርሱም በአላህ ፍርድ ርኅራኄ አትያዛችሁ፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደኾናችሁ (አትራሩ)፡፡ ቅጣታቸውንም ከምእምናን ጭፍሮች ይገኙበት፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል ኑር (2)

قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونََ۝
ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡
ቅዱስ ቁርኣን ሱራ አል-ኑር (30)

«ሁላችንንም አላህ የከለከለንን የምንከለከል፣ ያዘዘንን የምንታዘዝ ያድርገን»
#ሼር_አድርጉት

ቴሌግራም ቻናሉን ተቀላቀሉ!

[[[[[ https://t.me/drzakirnaiki ]]]]]]
((([ https://t.me/drzakirnaiki ]))))