Get Mystery Box with random crypto!

የወቅት ጉልበት! “በዓለም ላይ ወቅቱ እንደደረሰ ጽንሰ-ሃሳብ ኃይለኛ ነገር ተፈልጎ አይገኝም” – | Dr. Eyob Mamo

የወቅት ጉልበት!

“በዓለም ላይ ወቅቱ እንደደረሰ ጽንሰ-ሃሳብ ኃይለኛ ነገር ተፈልጎ አይገኝም” – Victor Hugo

የምሽቱ ጊዜ አልፎ የጠዋት ተረኛት ሲመጣና ብርሃን ጨለማውን ሲያስለቅቀው፣ ይህንን የወቅት ለውጥ ሊስቆመው የሚችል ምንም አይነት ኃይል በዓለም ላይ የለም፡፡ በውስጥህም በወቅቱ የሁኔታ ጨለማ ተደብቆ የነበረው ራእይ፣ ሃሳብ፣ ዓላማ ጊዜው ሲደርስ እንዲሁ ነው፤ ሊያስቆመው የሚችል አንዳች ነገር የለም፡፡

አንዲት ሴት ለዘጠኝ ወራት የተሸከመችው ጽንስ የመወለጃው ጊዜ ሲደርስና ልጁ ከጽንስነት ወደ ውጪው አለም ለመውጣት ሲገፋ፣ ያንን የምጥ ኃይል ሊይዘውና ልጁ እንዳይወለደ ሊያደረግ የሚችል ኃይል ተፈልጎ አይገኝም፡፡ በውስጥህም ጊዜው እስኪደርስ ተደብቆ የነበረው የራእይ፣ የሃሳብ፣ የዓላማ ጽንስም ወቅቱ ሲደርስ እንዲሁ ነው፤ ወደገሃዱ ዓለም እንዳይወጣ ሊያስቆመው የሚችል አንዳች ነገር የለም፡፡

ሁሉም ነገር ሁለት ጊዜ ነው የሚፈጠረው፣፤ በመጀመሪያ በሃሳብህ ውስጥ ከዚያም ደግሞ በገሃዱ አለም፡፡ ከዚህ በፊት በውስጥህ ተፈጥሮ የነበረው ጽንሰ-ሃሳብ ራእይም በለው ዓላማ፣ የዚህ ሃሳብ ጊዜው ሲደርስ በዚህ ምድር ላይ ማንም፣ ምንም ሊያስቆመው አይችልም፡፡

ምንም እንኳን በውስጥህ ይዘህ የከረምከው ሃሳብ ከመቆየቱ ወይም ካለህበት የወቅቱ ሁኔታ አንጻር ስታየው የማይደርስ ቢመስልህም፣ ወቅቱ ሲደርስ ግን ምንም ነገር ሊያስቆመው አይችልም፡፡

ምናልባት ለዘመናት በውስጥህ ተጸንሶ የቆውን ሃሳብ በእጅህ ልትይዘውና በአይንህ ልታየው ጊዜው ደርሶ ይሆን???!!!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623