Get Mystery Box with random crypto!

የዝምታ ጨዋታ! (Silent treatment) ለፍቅረኛሞች፣ ለእጮኛሞችና ለባለትዳሮች . . . | Dr. Eyob Mamo

የዝምታ ጨዋታ! (Silent treatment)

ለፍቅረኛሞች፣ ለእጮኛሞችና ለባለትዳሮች . . .

በፍቅር ግንኙነትም ሆነ በትዳር አጋርነት ውስጥ አንዱ ሌላውን ጊዜ እየጠበቀ ባለማናገር፣ በመዝጋትና የቀድሞውን ትኩረት በመንፈግ የሚያሳልፍበትን የዝምታ ወይም የመዝጋት ልምምድ ፈረንጆቹ Silent treatment በማለት ይጠሩታል፡፡ ይህ ባህሪይ አብዛኛውን ጊዜ በወንዶች ላይ የሚንጻበረቅ እንደሆነ ቢናገሩም፣ ቁጥራቸው ቀላል ያልሆኑ ሴቶችም ፍቅረኛቸውን ወይም የትዳር አጋራቸውን የመዝጋት አባዜ አለባቸው፡፡

በድንገትና ባልታወቀ መንገድ አጋራቸውን የሚዘጉ ሰዎች ለአያያዝ እጅግ አስቸጋሪ ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎቸ በድንገት አጋራቸውን በመዝጋትና ቀድሞ ይሰጡት የነበረውን ትኩረት በመንፈግ ለቀናት፣ ለሳምንታት፣ አንዳንዴም ለወራት ይቆዩና በፈለጉበት ቀን ልክ እንደቀድሞው በመሆን ይመለሳሉ፡፡

መንስኤው የአኩራፊነት፣ የቂመኝነት፣ በቀላሉ የመጎዳት ስስነት ወይም ደግሞ አጋርን በዚህ መልኩ የመቅጣትና ልክ የማስገባት ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱ ያም ሆነ ይህ ይሀ ባህሪይ ከፍቅር ግንኙነት አንቅፋት ከመሆኑም ባሻገር እጅግ በጣም ያለመብሰል ምልክት ነው፡

አጋራችሁ በየጊዜው እናንተን የመዝጋት ልማድ ካለበት …

1. በየጊዜው ለምን ያንን ባህሪይ እንደሚያሳዩ በግልጽ ማነጋገርና መሞገት፡፡

2. መንስኤው እናንተ ከሆናችሁ በግልጽ መናገር እንዳባቸው እንጂ መዝጋት እንሌለባቸው መሳሰብ፡፡

3. ከገቡበት የዝምታ ዋሻ ምንም እንዳልተፈጠረ ሲወጡና እንደቀድሞው መሆን ሲፈልጉ የቻላችሁትን ያህል መታገስ፡፡

4. ሁኔታው ከልክ ካለፈ በፈለጉበት ጊዜ እንደቀድሞው ሊሆኑ ከዝምታቸው ሲመለሱ በዚያው ፍጥነት እናንትም እንደዚያ መሆን እንደማትችሉና መለስ ለማለት ጊዜ እንደሚፈልግባች በመንገር የራሳችሁን ጊዜ መውሰድ፡፡

5. አሁንም ካልታረመ ከእንዳንዷ ዝምታ በኋላ ሲመለሱ ለምን ዘግተዋችሁ እንደከረሙ በሚገባ ሳያብራሩ፣ ስህተት ከሆነ ይቅርታ ሳይጠይቁና ይህባህሪይ ወደፊት እንደማይቀጥል ቃል ሳይገቡ መቀጠል እንደማይችሉ ማሳሰብ፡፡

6. ከዚህ ሁሉ እርምጃ በኋላ ነገሩ አሁንም ከባሰ፣ የፍቅር ግንኙነት ከሆነ የመቀጠሉን ጉዳይ በሚገባ ማሰብ፣ ግንኙነቱ የትዳር ከሆነ ግን አማካሪ መፈለግ አስፈላጊ ነው፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/