Get Mystery Box with random crypto!

በመጠበቅ ጊዜያችሁን አታባክኑ! • ደስተኛ ለመሆን ሰዎች በሚያሳይዋችሁ ሁኔታ ደስተኛ እስከሚያያ | Dr. Eyob Mamo

በመጠበቅ ጊዜያችሁን አታባክኑ!

• ደስተኛ ለመሆን ሰዎች በሚያሳይዋችሁ ሁኔታ ደስተኛ እስከሚያያደርጓችሁ አትጠብቁ፡፡ ከማንም ሰው ውጪ ደስተኛ የመሆን ብቃት አላችሁ፡፡

• ችግራችሁን ለማሸነፍ ችግራችሁን ሰዎች እስኪፈቱላችሁ አትጠብቁ፡፡ በመጀመሪያ ችግራችሁን ለመፍታት በራሳችሁ የመንቀሳቀስ ብቃት አላችሁ፡፡

• ሙሉ ሰው ለመሆን በሰዎች ተቀባይነት እስከምታገኙ አትጠብቁ፡፡ ሰዎች ቢቀበሏችሁም ሆነ ባይቀበሏችሁም ሙሉ ሰው ናችሁ፡፡

• የተሟላ ኑሮ ለመኖር ሁሉም ነገር እስኪሟላ አትጠብቁ፡፡ ነገር ሞላም አልሞላም ከዚያ ጋር ባልተነካካ ሁኔታ ከፈጣሪ ጋር ሙሉ ሰው ናችሁ፡፡

• ውስጣችሁ እንዲያርፍ ያሰባችሁበት ዓላማ ላይ እስከምትደርሱ አትጠብቁ፡፡ ከጅማሬው አርፋችሁና በጉዞው እየተደሰታችሁ ወደ ዓላማችሁ የመገስገስ ብቃት አላችሁ፡፡

ሕይወት ሂደት እንጂ የአንድ ቀን ክስተት አይደለችም!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/