Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ የጤና መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ drethiohealth — ኢትዮ የጤና መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ drethiohealth — ኢትዮ የጤና መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @drethiohealth
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 539
የሰርጥ መግለጫ

በአገራችን በብዛት ስላሉ በሽታዎች በአማርኛ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-22 21:02:24 ለተመረዘ ሰው ምን ማድረግ አለብን?

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአቅራቢያዎ ያለ ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ቢመረዝ እርዳታ እስከሚመጣ ድረስ መደረግ የሚገባቸው እና የሌለባቸው የህክምና እርዳታዎች አሉ፡፡

መመረዝ ስንል ምንን ያጠቃልላል?

1.የሚጠጣ ወይንም የሚዋጥ መርዝ
2.በአየር ወይንም በትንፋሽ አካል የሚገባ መርዝ
3.በቆዳ ንክኪ ወደ ሰውነት የሚገባ መርዝ እና
4.የእባብ መርዝ በሚባል ይጠቀሳሉ፡፡

1.የሚጠጣ/ የሚዋጥ መርዝ (ምሳሌ፡ የቤት ውስጥ የፅዳት ፈሳሾች፣ ፀረ-ነፍሳትና ፀረ -ተባይ መድሃኒቶች ፣ የሥራ ቦታ ኬሚካሎች፣ መድኃኒቶች…ወዘተ)

•የህክምና ዕርዳታ እስከሚመጣ ድረስ ግለሰቡን በግራ ጎኑ አስተኝተው መከታተል ÷ ማስመለስም ሆነ ማንቀጥቀጥ ከተከሰተ ትንታ እንዳይፈጠር ይከላከላል።

•በጤና ባለሙያ ካልታዘዙ በስተቀር እንዲያስመልሱ አያድርጉ! ይህም አንዳንድ ጠንካራ መርዞች በጉሮሮ እና በላይኛው የጨጓራ እና አንጀት ክፍል በሚያልፉ ጊዜ ከባድ ጉዳት የሚያደርሱ ስለሆነ እንዲያስመልሱ ማድረግ ለዚህ ጉዳት ድጋሚ ማጋለጥ ስለሆነ ነው።

•የተመረዘው ሰው ካስመለሰ ወይም በአፉ ውስጥ የቀረ መርዝ ካለ በጣት ላይ ጨርቅ በመጠቅለል የግለሰቡን አፍ ማጽዳት ይገባል።

•የመርዙ መያዣ ዕቃን በማንበብ ለድንገተኛ መመረዝ ማድረግ የሚገባዎትን መመሪያዎች ከያዘ በመከተል÷ የመርዙን ዕቃ የጤና ባለሙያ እስኪያየው ድረስ በቅርብ ማቆየት።

•ራሱን ለሳተ ሰው በአፍ ምንም ነገር አለመስጠት!

•በጤና ባለሙያ ካልታዘዘ በስተቀር መርዙን በሎሚ ጭማቂ ወይም በሆምጣጤ፣ ወይም በሌላ በማንኛውም ንጥረ ነገር ለማርከስ አለመሞከር!

•ለሁሉም መርዞች በተለምዶ ‘ፈውስ ናቸው’ ተብለው የሚታሰቡ ማርከሻዎችን (እንደ ወተት ያሉ) አለመጠቀም!

• አንድ ሰው ተመርዟል ተብሎ ከተጠረጠረ የሕመም ምልክቶች እስከሚታዩ ድረስ አለመጠበቅ እና ወደ ሆስፒታል በፍጥነት መሄድ ይገባል!

2.በአየር/ በትንፋሽ አካል የሚገባ መርዝ

(ምሳሌ፡ ካርቦን ሞኖክሳይድ የተባለ ጋዝ ዋናው ሲሆን ÷ በሚከተሉት ክስተቶች ይመረታል። በተዘጋ ቤት ውስጥ ከሰል ከማቀጣጠል፣ ከጋዝ ሞተሮች፣ ከእሳት አደጋ ጭስ፣ ከአየር ማሞቂያ ማሽኖች ወዘተ)

•እራስን አደጋ ላይ ባለመጣል በተቻለ ፍጥነት ግለሰቡን ወደ ንጹህ አየር መውሰድ

•ወደ ተበከለው አየር ሲገባም በአፍንጫ እና በአፍ ላይ እርጥብ ጨርቅ መያዝ እንዲሁም በሮች እና መስኮቶችን መክፈት

•ግለሰቡ ፍጹም ደህና ቢመስልም ወደ ሕክምና ዕርዳታ መውሰድ! ይህም በትንፋሽ አካል የሚገቡ መርዞች በተለይም የእሳት አደጋ ጭስ ከሰዓታት በኋላ በድንገት የሚባባስ ምልክቶች፣ ትንፋሽ ማጠር እንዲሁም ሞት ስላሚያስከትሉ ነው።

•አንዳንድ ጋዞች እሳት ሊያያዙ ስለሚችሉ ክብሪት/ የትኛውም እሳት አለማብራት

3.በቆዳ ንክኪ ወደ ሰውነት የሚገባ መርዝ

(ምሳሌ፡ ማዳበሪያዎች ፣ ፀረ -ተባይ መድኃኒቶች ፣ ዕፅዋት)

•ጓንት/የእጅ መሸፈኛ በመጠቀም ማንኛውንም የተበከለ ልብስ ማስወገድ
•የተበከለ ቆዳን ከ 15 እስከ 20 ደቂቃ መከከለኛ ሙቀት ባለው ውሃ መታጠብ

4.የእባብ መርዝ

•የእባብ መርዝን በአፍ መጦ ለማውጣት አለመሞከር!
በተለምዶ የእባብ መርዝን ከተነከሰው የሰውነት ክፍል በአፍ መጦ ማውጣት እንደ መፍትሄ ይታያል።
ነገር ግን የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ መርዙ በፍጥነት ስለሚሰራጭ ይህ ልምድ ጥቅም የለውም።
ከዛም ባሻገር ለኢንፌክሽን እና ለተጨማሪ የደም ቱቦ እና ነርቭ ጉዳት ያጋልጣል።

•መርዙ በፍጥነት በደም ስርጭት እንዳይዛመት የሚከተሉትን መተግበር ያስፈልጋል፡፡

- በእባብ የተነከሰውን የሰውነት ክፍል ከልብ ደረጃ በታች ማድረግ
- ከመሮጥ ወይም የበዛ የአካል እንቅስቃሴ ከማድረግ መቆጠብ ፤ ከተቻለ በመረጋጋት በጎን መተኛት
- ከቁስሉ ከፍ ብሎ ያለ የሰውነት ክፍልን ማሰር በራሱ ጉዳት ያለው ቢሆንም የህክምና እርዳታ ለማግኘት ከሦስት ሰዓት በላይ የሚፈጅ ከሆነ የመርዙን የስርጭት ፍጥነት ለመቀነስ ይጠቅማል፡፡

•ማናቸውም ጌጣጌጦች፣ ሰዓቶች እና ጥብቅ ልብሶች ማስወገድ የሚገባ ሲሆን ÷ ምክንያቱም እብጠት ከተከሰተ ቆዳን ሊቆርጡ ወይም የደም ዝውውርን ሊያቋርጥ ይችላሉ፡፡

•ሻይ፣ ቡና፣ አልኮል እና የህመም ማስታገሻዎችን አይውሰዱ!

•የእባቡን አይነት በማስተዋል የጤና ባለሙያዎች መርዛማ መሆኑን እና አለመሆኑን እንዲለዩ ማገዝ። ከመርዛማ እባብ ዋና መገለጫዎች ውስጥ የሶስት ማዕዘን ጭንቅላት እና ሞላላ የአይን ውስጥ ቅርፅ/pupil/ ዋናዎቹ ናቸው፡፡

•እነዚህ ሁሉ ጠቃሚ እርምጃዎች ቢሆኑም ለእባብ መርዝ ዋናው ሕክምና የእባብ መርዝ ማርከሻ በመሆኑ በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ይሂዱ።
289 views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 09:36:02 እንቅርት #

ታይሮይድ የተባለው አንገታችን መሀል አካባቢ በተፈጥሮ የሚገኘው ጠቃሚ እጢ(gland) ሲተልቅ እንቅርት (goiter ) ይባላል። ታይሮይድ የተባለው እጢ ከማንቁር(Adam's apple ) ትንሽ ዝቅ ብሎ የሚገኝ ሲሆን በኖርማል ሰው በእይታ አይታወቅም።
የታይሮይድ እጢ ታይሮክሲን የተባሉ ሆርሞኖችን ያመነጫል። እነዚ ሆርሞኖች በሰውነታችን በርካታ ስራዎችን ይሰራሉ። ከነዚህም መካከል የሙቀት ሁኔታ፣ ሙድ፣ ስሜታዊነት ፣የልብ ምትና የምግብ መፍጨት ስርአት ይገኙበታል።

የእንቅርት አይነቶች ምን ምን ናቸው?
1.ቀላል (Simple goiter )፦ ይህ ካንሰር ያልሆነና ሆሮሞንም በከፍተኛ የማያመነጭ ነው።
2.ኢንደሚክ (Endemic goiter)፦ ይህ የአዮዲን እጥረትን ተከትሎ የሚመጣ ሲሆን በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ ይገኛል። አዮዲን ታይሮይድ ሆርሞን ለመስራት አስፈላጊ ነው። የአዮዲን እጥረት ሲኖር የዚህ ዓይነት እንቅርት ይከሰታል። አዮዲን ያለው ጨው በመጠቀም መከላከል ይቻላል።
3.ሆርሞን የሚያመነጭ(Toxic goiter )፦ ይህ የሚከሰተው እባጩ ከፍተኛ ሆርሞን በማመንጨት በልብና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ጉዳት ሲያደርስ ነው።
4.ካንሰር ፦ አንዳንድ እንቅርት ከጅምሩ ካንሰር ሲሆን ሌላው ደሞ በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰር የተቀየረ እንቅርት ነው።በፍጥነት ማደግና የድምፅ መጎርነን የዚህ ዓይነት እንቅርት ምልክት ነው።

አጋላጭ ነገሮች ምንድን ናቸው?

1.እንደ ሊቲየም(ለኣእምሮ የሚታዘዝ ) ያሉ መድሀኒቶች
2.የአንገች ጨረር ህክምና( በተለይ በልጅነት የሚሰጥ)
3.የሴት ፆታ
4.እድሜ አርባ አመት አካባቢ መሆን
5.የታይሮይድ እጢ ብግነት
6.አውቶ አሚውን ዲዚዝ(ሰውነት ራሱን ሲያጠቃ) ዋናዎቹ ናቸው ።

ምልክቶች
1.አንገት ላይ እባጭ (እንቅርት )
2.ጉሮሮ የማነቅ ስሜት
3.የድምፅ መጎርነን
4.ለመተንፈስ መቸገር
5.ሳል
6.ለመዋጥ መቸገር
7.የልብ ምት መጨመር
8.ማላብ፦ምንም ሳይሰሩና ሙቀትም ሳይጨምር
9.የእጅ መንቀጥቀጥ
10.መጨነቅ
እነዚህ ምልክቶች በከፊል ወይም ሁሉም ሊኖሩ ይችላሉ።

ምርመራው

1.የሐኪም የሰውነት ምርመራ(physical exam)
2.የሆርሞን ምርመራ
3.አልትራሳውንድ
4.የናሙና ጥናት (ፓቶሎጂ)
5.የአንገት ሲቲ ስካን
6.ሌሎች መሰረታዊ የላቦራቶሪ ምርመራዎች

ህክምናው

1.ክትትል ብቻ፦ ከምርመራ በኋላ የሚወሰን ሲሆን ለትንሽና ለማያመነጭ እንቅርት።
2.መድሀኒት፦ በተለይ ከፍተኛ ሆርሞን የሚያመነጭ ከሆነ ግድ መወሰድ አለበት። ይህ ሰይደረግ ኦፕሬሽን ማድረግ አደገኛ ስለሆነ አይቻልም።
3.ኦፕሬሽን፦ ሆርሞን በመድሃኒት ከተስተካከለ በኋላ የሚደረግ ሲሆን እጢው በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ይወጣል።

መልክቱን ሼር ያድርጉ
319 views06:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 11:24:00 ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ የድንገተኛ ልብ ህመም ምልክቶች

ጭንቀት

ይህ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የልብ ህመም ምልክት ነው፡፡ ድንገተኛ የልብ ህመም ከመከሰቱ በፊት ፍርሀት ፍርሀት የማለት ስሜት ሊኖር ይችላለ፡፡

የደረት መጨምደድ

ደረት ላይ የመጨምደድ ስሜት እጅግ የተለመደ የልብ ህመም ምልክት ነው፡፡ ከልብ ህምም ጋር ያልተያያዘ የደረት መጨምደድ በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ቢሆንም በአብዛኛው የልብ ህመም መገለጫ ነው፡፡ ደረቶን በመጫን የመሸምቀቅ ወይም የመጨምደድ ሲሜት ሲሰማዎ ወደ ህክምና በመሄድ ሀኪምዎን ማማከር ተገቢ ነው፡፡

ሳል

የማያቆም ሳል ወይንም ሲሰርሲርታ የሚያስቸግሮ ከሆነ እንዲሁም በሚያስሉ ግዜ ደም የተቀላቀለበት አክታ ካሎት ወደ ህክምና ቦታ በመሄድ መመርመር ያስፈልጋል፡፡

ማዞር

ድንገተኛ የልብ ህመም የማዞር ስሜር እንዲኖር ያደርጋል ከዛም ባለፈ እራስን እስመሳት ሊደርስም ይችላል

ድካም

ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ የድካም ስሜት መሰማት በቀጣይ ቀናት ውስጥ ድንገተኛ የልብ ህመም ለመከሰት ምልክት ሊሆን ስለሚችል ሃኪሞን ማማከር ይኖርቦታል፡፡

ማቅለሽለሽ ወይንም የምግብ ፍላጎት መቀነስ –

ማቅለሽለሽ እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ አልፎ አልፎ የድንገተኛ የልብ ህመም መከሰት ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡

በሌሎች የሰውነት ክፍሎች ላይ የሚከሰት ህመም

ድንገተኛ ልብ ህመም ከመከሰቱ አስቀድሞ የህመም ስሜት የሚጀምረው ከደረት ከዛም ወደ ትከሻ(የግራ ትከሻ) ወደ ክንድ ፤ ጀርባ ፤ አንገት ፤ መንገጭላ አካባቢ ነው፡፡ ጨጓራ አካባቢ የማቃጠል ስሜትም ሊከሰት ይችላል፡፡

ትንፋሽ ማጠር

በቀላል አንቅስቃሴ ከፍተኛ የሆነ ትንፋሽ ማጠር የሚከሰት ከሆነ ከሳንባ ህመም በተጨማሪ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ችላ ሊባል አይገባም፡፡

ማላብ

በተቀመጡበት በላብ መስመጥ የድንገተኛ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ትኩረት ሊሰጡት ይገባል፡፡

የሰውነት እብጠት

የልብ ስራ በሚስተጓጎልበት ግዜ በሰውነታችን ውስጥ ፈሳሽ እንዲከማች ያደርጋል፡፡ ይህም የሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች እንዲያብጡ ያደርጋል (እግር ፣ ቁርጭምጭሚት እና ሆድ አካባቢ) ፡፡ ፈጣን የሆነ ሰውነት ክብደት መጨመርም እንዲታይ ያደደርጋል፡፡

የልብ ምት መጨመር ወይም የተዛባ የልብ ምት

የልብ ምት መጨመር ከማዞር ፣ የድካም ስሜት ከመሰማት እና ትንፋሽ ከማጠር ጋር ተያይዞ ከመጣ ድንገተኛ የልብ ህመም ምልክት ሊሆን ስለሚችል ወደ ሀኪም መሄድ ተገቢ ነው፡፡

ለልብ ህመም የሚያጋልጡ ምክንያቶች፦

እድሜ

ሲጋራ ማጨስ

የስኳር ህመም

ከፍተኛ የደም ግፊት

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ

ከመጠን በላይ የሆነ የሰውነት ውፍረት

የኩላሊት ህመም

ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት እና አደንዛዥ እፅ መጠቀም ይገኙበታል።

የልብ ህመምን ለመከላከል …?

የተስተካከለ እና የተመጣጣነ የአመጋገብ ስርዓት መከተል

በየእለቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት

በቂ እንቅልፍ መተኛት፤ በቀን ውስጥ ከ6 እስከ 8 ሰዓት ብንተኛ ይመከራል

በስኳር ህመም የተጠቃን ከሆነ ህመሙን ለመቆጣጣር አስፈላጊውን ህክምና በሙሉ ማድረግ

ሲጋራ ማጨስ ማቆም እንዲሁም የአልኮል አወሳሰዳችንን መመጠን

የደም ግፊታችንን እና በደማችን ውስጥ ያለን የኮሌስትሮል መጠን መቆጣጣር

በጣም ወፍራም ከሆንን የሰውነት ክብደታችን ለመቀነስ የሚረዱን ተግባራትን ማከናወን
350 views08:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-13 10:43:04 የጀርባ ሕመም (Back pain)

ዕድሜያቸው ከ30-40 ዓመት የሆኑ ሰዎች የሐኪም ፊት እንዲያዩ ከሚያስገድዳቸው ወይም ስራ ከሚቀሩባቸው ምክንያቶች አንዱ የጀርባ ሕመም ነው፡፡ በዚህ ዕድሜ የጀርባ ሕመም የተለመደ አለም አቀፍ የጤና ችግር ከመሆኑም በተጨማሪ ለአካል ጉዳት ከሚዳርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱም ነው፡፡ ሌላው አስደንጋጭ መረጃ ብዙ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው ቢያንስ አንዴ በጀርባ ሕመም መጠቃታቸው ነው፡፡ ይሁንና እንደመታደል ሆኖ የጀርባ ሕመምን ለመከላከለም ሆነ ሕመሙ ሲያጋጥም በፍጥነት ከሕመሙ ለመውጣት የሚያስችሉ የቤት ውስጥ ሕክምናዎችን ጨምሮ የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል በሳምንት ውስጥ ፈውስን የሚያስገኝ ቢሆንም ሕመሙ በወራት የዘለቀ እንደሆነ ግን ችግሩ ከበድ ያለና የተለያዩ የጤና ችግሮች ውጤትም ሊሆን ይችላል፡፡

በተደጋጋሚ ለጀርባ ሕመም የሚያጋልጡ ምክንያቶች
1. የጡንቻ ወይም የሊጋሜንቶች ውጥረት
2. ድንገተኛ የጡንቻ መኮማተር
3. የጡንቻ መሳሳብ ወይም ውጥረት
4. የዲስክ መጎዳት
5. አደጋዎች (ስብራት ወይም መውደቅ)
6. እርግዝና
7. በዕድሜ መግፋት
8. ከፍተኛ የሰውነት ክብደት
9. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ
10. ሲጋራ ማጨስ
11. ካንሰርና የአንጓ ብግነት
12. የኩላሊት ጠጠር ወይም ኢንፌክሽን
13. ድባቴና ጭንቀት እንዲሁም የህብለ ሰረሰር በቀላሉ መሳሳብና ቀዳዳ መፍጠር ናቸው፡፡

የጀርባ ሕመም አባባሽ ምክንያቶች
1. ያለ አግባቡ ዕቃዎችን ማነሳት (ተጠማዞ፣ተንጠራርቶ እና ወገባችንን እና እግራችንን ወጥሮ ማንሳት)
2. ከባድ ነገሮችን ያለ አግባቡ ማንሳት
3. ድንገተኛና የማይመች እንቅስቃሴ ማድረግ
4. ረጅም ጊዜ መቆም ወይም መቀመጥ
5. ረጅም ሰዓት ያለ እረፍት መንዳት
6. ወገባችንን ከመቀመጫ መደገፊያ ጋር ለጥፎ ከመቀመጥ ይልቅ ጎብጦ መቀመጥ ናቸው፡፡

የጀርባ ሕመም መኖሩን የሚጠቁሙ ምልክቶች
1 .የጡንቻ ሕመም
2. ጀርባችንን የመውጋት ስሜት
3. ሕመሙ ወደ እግራችን የዘለቀ እንደሆነ
4. በሚያጎነብሱበት፣ዕቃ በሚያነሱበት፣በሚቆሙበትና በሚራመዱበት ጊዜ ሕመም መሰማት
5. ጋደም በምንልበት ጊዜ የሕመም ሁኔታ መሻሻል ናቸው፡፡
221 viewsedited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 14:57:14 ችላ ሊባሉ የማይገባቸው የደም ግፊት ምልክቶች

ትክክለኛ የደም ግፊት የሚባለው የላይኛው ከ120 mm Hg በታች እና የታችኛው ከ80 mm Hg በታች ሲሆን ነው ። የላይኛው ከ120-129 እና የታችኛው ከ80 በታች ከሆነ ትንሽ ከፍ ያለ/elevated blood pressure ሲባል ነገርግን የላይኛው ከ130-139 እና የታችኛው 80-89 ከሆነ ደረጃ አንድ የደም ግፊት /stage 1 hypertension ይባላል ።የላይኛው 140 እና ከዚያ በላይ ወይም የታችኛው 90 እና ከዚያ በላይ ከሆነ ደረጃ 2/stage 2 hypertension ይባላል ።

የሚከተሉት 10 ምልክቶች ፈፅሞ ችላ የማይባሉ የደም ግፊት ምልክቶች ስለሆኑ ሁሉም ሰው ሊያውቃቸው ይገባል

1ኛ፦ ራስ ምታት ፡ ይህ የሚሆነው የአንጎል አርተሪዎች/ደም ቅዳዎች በግፊት ሲወጠሩና የጭንቅላት ወስጥ ግፊት ሲጨምር ነው ።አንዳንዴም የግፊት ምቱ በጆሮ ሁሉ ሊያስተውቅ ይችላል ።

2ኛ፦የአይን ብዥብዥ ማለት ፡የዚህ ክስተት መነሻው ለረጅም ጊዜ የቆየ የደም ግፊት በአይናችን ውስጥ ባሉ ቀጫጭን የደም ስሮች ላይ ጉዳት ሲያደርስ/ hypertensive retinopathy አሊያም የጭንቅላት ውስጥ ግፊት በመጨመሩ ምከንያት ነው ።

3ኛ፦በቀላሉ የመድከም ስሜት/fatigue ፡ ይህም የሚመጣው የደም ግፊት በልብ ፣ በሳንባና በነርቭ ላይ ጫና ስለሚያሳድር ነው።

4ኛ፦የደረት ህመም ፦ የደም ግፊት ቀዳሚው የልብ ድካም /myocardial infarction ምክንያት ነው። የህም ጭምድድ አርጎ የሚይዝ የደረት ህመም ሊያመጣ ይችላል

5ኛ፦የሰውነት ክፍል መስነፍ/weakness ፦የደም ግፊት ዋነኛ የስትሮክ መንሴ ሲሆን በጭንቅላት ውስጥ ባሉ የደም ስሮች ጉዳት በማድረስ የሰውነት ክፍል አልታዘዝ እንዲል/ፓራላይዝ ሊያደርግ ይችላል።

6ኛ፦ማቅለሽለሽ /ማስመለስ ፡ ይህ የደም ግፊት የጭንቅላት ውስጥ ግፊትን ከፍ በማድረግ የሚፈጠር ነው።

7ኛ፦የትንፋሽ ማጠር ፡የደም ግፊት የልብ ድካም አስከትሎ የትንፋሽ ማጠር ሊያመጣ ይችላል ።

8ኛ፦የጀርባ ህመም ፡ ይህ የሚሆነው የደም ግፊት ትልቁን ደም ቅዳ/Aorta የተባለውን የደም ስር ሊጎዳ ስለሚችል ነው ። ይህም የሚሆነው ደም ወደ ትልቁ የደም ቅዳ ግድግዳ ሰንጥቆ እንዲፈስ/ Aortic dissection በማስከተል ነው

9ኛ፦ነስር/የአፍንጫ መድማት ፡ ከፍተኛ የደም ግፊት ቀጫጭን አፍንጫ ውስጥ ያሉ የደም ስሮችን በመጉዳት ነስር ሊያስከትል ይችላል ።

10ኛ፦ምንም ዓይነት ምልክት አለማሳየት ፡በጣም በሚገርም ሁኔታ አንድ ሰው እጅግ ከፍተኛ የደም ግፊት ኖሮት ምንም ዓይነት ምልክት ላያሳይ አለመቻሉ ነው። አብዛኛው የደም ግፊት ምንም ምልክት ሳያሳይ ጉዳት ያደርሳል ። ለዚህም ነው ዝምተኛው ገዳይ /silent killer በመባል የሚታወቀው ።

ግፊታችንን በመለካት አኗኗራችንን እናስቸካክል መልእክቴን ነው ።
መልክቱን ሼር ፔጁን ላይክ በማድረግ ተከታታይ ትምህርቶችን ያግኙ ።
316 views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 10:32:13 ደም ማነስ ?

ደም ኦክስጅን ፣ሆርሞኖች አና ሌሎች ለሰውነታችን አስፈላጊ የሆኑ ንጥረነገሮችን ወደተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ያደርሳል እንዲሁም ለሰውነታችን ጎጅ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ወደ ጉበት፣ኩላሊት እና ሳምባ ያደርሳል። ነጭ የደም ህዋስ በሽታዎችን ይከላከላል ፣ ፕላትሌት የሚባለው ህዋስ ደግሞ ደም እንዳይረጋ አና አንዳይቀጥን ትክክለኛ ቪስኮሲቲ እንዲኖር ያደርጋል።

*ከተወለድን በኋላ 100% በ አጥንት መቅን ይመረታል
*ቀይ የደም ህዋስ እድሜው 120ቀን ብቻ ነው።
*አንድ ሰው በየ3 ወሩ ደም መለገስ ይችላል ።

#የደም ማነስ እሚያመጡ ምክንያት
የሚከተሉት በሽታዎች እንደ በሽታዎች ፅናት( severity of mentioned diseases) ደም ማነስ ያመጣሉ።
-የምግብ እጥረት ፣ ትክክል ያልሆነ የአመጋገብ ስርአት ምሳሌ አትክልት ብቻ መመገብ(vegetarians)።በኢትዮጵያ እንዲሁም በአብዛኛው አለም የ አይረን እጥረት(iron deficiency )በዋናነት የደም ማነስ ምክንያት ነው
- በተለያዩ ምክንያቶች ደም መፍሰስ ምሳ. አደጋ፣ በወሊድ ሰአት፣ ጨጓራ በሽታ ፣የጉበት በሽታ ..።
-ካንሰር ፣ ወባ
-በእባብ መነደፍ
-ከዚህ በፊት የጨጓራ እና ቀጭን አንጀት ቀዶ ጥገና ከነበረ።
- የካንሰር እና የሚጥል በሽታ መድኃኒቶች (chemotherapy and anticonvulsant drugs)
.

#የደም ማነስ ምልክት
የደም ማነስ ምክንያት ደም መፍሰስ ከሆነ ምልክቱ ደም መፍሰስ እና አደጋ ወይም ምጥ ይሆል። ነገር ግን የደም ማነስ ምክንያት የቆየ ከሆነ ምልክቶች እንደሚከተለው ይሆናል
1.ድካም ስሜት ከዚህ በፊት በቀላሉ ስትሰራው/ሪወ የነበረን ስራ ለመስራት መቸገር፣ እራስ ማዞር፣ ጆሮ መጮህ የልብ ትርታ መጨመር፣ የሰገራ ቀለም ወደ ጥቁር መቀየር።
2.የእጅ መዳፍ እና የአይን ልባስ ነጭ መሆን፣

#ደም ማነስ መኖሩን እንዴት ማወቅ ይቻላል
፩ ሙሉ የደም ምርመራ ማድረግ
፪ የአጥንት መቅን ምርመራ
#ህክምና
የደም ማነስ ህክምና እንደ መንስኤዎች እና እንደ በሽታው ክበደት ይለያያል።
1. ደም መፍሰስ ካለ የደሙን ፍሰት ማቆም እና ደም መስጠት (platelet , FFP ,whole blood)
ከለጋሾች የተገኘን ደም ለታካሚዎች መስጠት የመጀመሪያ እና ህይወት አድን ህክምና ነው። ሀኪም አስፈላጊ ነው ብሎ ከወሰነ
2. ቯይታሚነ B12፣ አይረት(Fe) አና ፎሌት መስጠት
3.ካንሰር ከሆነ የካንሰር መድኃኒት ፣ የጨረር ህክምና አና ቀዶ ጥና

#ደም ማነስን እንዴት እንከላከላለን
1. በእርግዝና ወቅት ክትትል ማድረግ በሀኪም የታዘዘ አይረን እና ፎሌት መወሰድ።
2. የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
3. አደጋን መከላከል
201 views07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 15:20:12 የሽንትዎ ቀለም ስለሰውነትዎ ጤና ምን ይነግርዎታል?

ሽንት ኩላሊት ደምን አጣርቶ የሚያስወጣው ክፍል ሲሆን 95% ውሀ 5% ኤሌክትሮላይቶች እና ቆሻሻዎች ናቸው ።
ጤናማ እና በቂ ፈሳሽ በሚዎስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ብዙ የጎላ ቀለም በሌለው እና ነጣ ያለ ቢጫ ቀለም መካከል ነው፡፡በቂ ፈሳሾችን በማይወስዱበት ጊዜ ሽንትዎ ይበልጥ የተከማቸ ሲሆን ወደ ጠቆር ያለ ቢጫ ወይም የዓምበር ቀለም ይለወጣል ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሽንት ቀለም እና መጠን እየዎሰዱ ያሉትን የውሀ መጠን ፣ ምግብ ፣ ቫይታሚን ጠቋሚ ነው።
የተወሰኑ ምግቦች ፣ አንቲባዮቲኮች ፣ የህክምና ሁኔታዎች እና ቀለሞች እንዲሁ ለጊዜው የሽንት ቀለም ይቀይራሉ ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ የተለያዩ የሽንት ቀለም አይነቶች እና ምክንያቶች እናያለን ።

1. በጣም ነጭ ከሆነ ከመጠን በላይ ውሀ እየጠጡ እንደሆነ ያመለክታል ። ይህም የተለያዩ በደም ውስጥ የሚገኙ ንጥረ ነገሮችን በተለይም ፓታሽየም እና ሶድየም መጠናቸው እንዲያንስ ያደርጋል ይህም የልብ ጡንቻን ይጎዳል ።

2. ጥቁር ቢጫ - ይህም በቂ ውሀ እየወሰዱ እንዳልሆነ ወይም ኬቶን በሽንት ውስጥ መኖር ሊሆን ይችላል ። በቂ ውሀ አለመውሰድ ደግሞ ለኩላሊት ጠጠር ፣ የሰውነት ፈሳሽ መቀነስ ፣ የኤሌክትሮላይት መዛባት ያስከትላል ። ኬቶን የሚፈጠረው በቂ የሆነ ስኳር (glucose ) ሳያገኝ ሲቀር እና ቅባት (fat) ለሴሎች ጉልበት ሲጠቀም ነው ። ይህም በሽንት መልክ ይወጣል ። ከፍተኛ የኬቶን መጠን አደገኛ የስኳር በሽታ ጉዳትን (DKA) ተከትሎ ሊመጣ ይችላል ። አነስተኛ መጠን ከሆነ ለረጅም ጊዜ ካልተመገብን ሊከሰት ይችላል ።

3. ደማቅ ቢጫ - ከበቂ በላይ ሰው ሰራሽ ቫይተሚን ቢ እየወሰዱ ከሆነ

4. ቀይ- ይህ የሚፈጠረው ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ነው ። ይህም በኩላሊት ጠጠር ፣ የኩላሊት እና የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፣ የፕሮስቴት እጢ ካንሰር ፣ የኩላሊት ካንሰር ፣ ከባድ ስፓርት

5. ጥቁር ብርቱካናማ / ቡናማ - የጉበት ችግር ያመለክታል ። የጉበት ፣ የሀሞት ቀረጢትና የቱቦዎች ችግር ተከትሎ የቢሊሩቢን በደም ውስጥ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚከሰት ነው።

6. ሀምራዊ - አነስተኛ ደም በሽንት ውስጥ ሲኖር ወይም ቀይ ስር ከበላን

7. ሰማያዊ - የካልስየም መብዛት /hypercalcemia

7. አረፋ ካለ - ፕሮቲን በሽንት ውስጥ መኖር ፤ ይህም የኩላሊት ቁስለት ፣ የኩላሊት ጠጠር ፣ የልብ እና የኩላሊት መድከም ፣ የተለያዩ የካንሰር አይነቶች

8. ብዙ የሚሸኑ ከሆነ - በሽንት ውስጥ የስኳር መኖር ነው ፤ ይህም የስኳር በሽታ ያመለክታል ።
205 views12:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-11 07:48:35 የእንቅልፍ እጦት (insomnia)

ይህ በሽታ በተለምዶ የእንቅልፍ እጦት እያልን የምንጠራው ሲሆን ለመተኛት በቂ ጊዜ አግኝቶ ነገር ግን ለመተኛት መቸገር፣ ተኝተው መነሳት፣ ወደ እንቅልፍ ተመልሶ አለመሄድ ችግር ነው:: ይህ እክል የቀን ውሎን ከማሰናከሉም በላይ አዕምሮ በትክክል እንዳይሰራ ያደርጋል ።

የእንቅልፍ እጦት የአጭር ጊዜና ስር ሰደድ በመባል ይከፈላሉ::

1. የአጭር ጊዜ፦ የምንለው ከሶስት ወር ያላለፈ እና አብዛኛውን ጊዜ ከጭንቀት ጋር የተገናኘ ነው

2. ስር የሰደድ የእንቅልፍ እጦት፦ ከሶስት ወር በላይ የቆየ እና ቢያንስ በሳምንት ውስጥ ለሶስት ምሽቶች መከሰት አለበት::

የእንቅልፍ እጦት በሽታ ምልክቶቹ ምንድናቸው?
> ለመተኛት መቸገር
> አልጋ ላይ ሆኖ እንቅልፍ አለመውሰድ
> ቀን ላይ መድከም እና እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት
> ነገሮችን በተገቢው ሁኔታ ለማሰብ መቸገር
> ብስጭት
> ጉልበት ማጣት
> ስለነገሩ ለወደፊት መጨነቅ
> የእለት ተእለት ተግባርን ለማከናወን መቸገር

ጥሩ እንቅልፍ እንዳንተኛ የሚያደርጉ ምክንያቶች
× የልብ ድካም
× የሳንባ በስታ፦ አስም
× የአዕምሮ ጭንቀት፣ ድብርት
× የተለያዩ ሱሶች፦ ጫት፣ አልኮል፣ ቡና
× የስራ ጫና፣ የማታ ተረኛ መሆን
× የተለያዩ መድኃኒቶች
× ተፈጥሯዊና ለአጭር ጊዜ የሚቆዩ ሁኔታዎች፦ የፈተና ሰሞን፣ ከፍቅረኛ ጋር መጣላት/መለያየት፣ የቤተ-ዘመድ ሞት

ምን እናድርግ?
× ቋሚ የመተኛ ሰዓት መመደብ
× ቋሚ የመነሻ ሰዓት መመደብ
× የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
× እራት ከመኝታ ከ3-4 ሰዓት ቀድሞ መመገብ
× መኝታ ክፍልን ብርሃን ያልበዛበት፣ ጸጥተኛና ቀዝቀዝ ያለ ማድረግ
× አልጋን ለመኝታ ብቻ መጠቀም(አልጋ ላይ ሆኖ አለማንበብ፡ ቴሌቪዥን አለማየት)
× ሊተኙ አካባቢ የሚያበሳጭ፡ የሚያናድድ ነገርን በተቻለ መጠን ማስወገድ፤ አልኮል፡ ቡና እንዲሁም ጫትን ከመጠቀም መቆጠብ
× በሽታ ካለ መታከም፡ ሱስ ካለ ማቆም

ሐኪምዎን ያማክሩ
> ከላይ የተጠቀሱትን ተግባራዊ አድርገው ለውጥ ከሌለ
> ከእንቅልፍ ችግሩ በተጨማሪ ጭንቀትና ድብርት ካለ
> የእንቅልፍ ችግሩ በስራዎና በማህበራዊ ህይዎትዎ ላይ ተጽእኖ ካመጣ
193 views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-10 09:51:49 የጨጓራ ህመም

የጨጓራ ህመም ጨጓራን እና የላይኛውን የቀጭን አንጀት ክፍል የሚያጠቃ በሽታ ነው።
ይህ በሽታ ዋና ምልክቱ የላይኛው የሆድ ክፍል ህመም ነው።
ይሀ ህመም ምንም አይነት የሚታይ የጨጓራ ችግር ከሌለው እስከ ውስጠኛው የጨጓራ ንጣፍ እና ጡንቻ የሚደርስ ጠባሳ እና ቁስል ሊደርስ ይችላል ።
የሚከሰተው ምግብ ለመፍጨት የሚጠቅመን የጨጓራ አሲድ እና አሲዱ ጉዳት እንዳያደርስ የሚከላከሉ የተለያዩ መንገዶች ሳይመጣጠኑ ሲቀሩ ነው።

የጨጓራ ህመም ምልክቶች
• የላይኛው የሆድ ህመም ከቀላል እስከ ከባድ
• ከተመገቡ በኋላ የማፍሸግና የማቃጠል ስሜት መኖር
• የጨጓራ መጮህ
• ቅባት የበዛበት ምግብ አለመቋቋም
• ማስመለስ

አሳሳቢ የጨጓራ ህመም ምልክቶች
• የደም ማነስ
• ምልክቱ ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ ሰዎች ሲከሰት
• ተደጋጋሚ ማስመለስ
• ለመዋጥ መቸገር
• ደም ማስመለስ
• ክብደት መቀነስ
• ትንሽ በልቶ የመጥገብ ስሜት መኖር
• በቤተሰብ የጨጓራ ካንሰር ታሪክ መኖር
እነዚህ ምልክቶች ህመሙ ከጨጓራ ካንሰር ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ናቸው ።

ለጨጓራ ህመም የሚያጋልጡ ነገሮች
• ኤች ፓይሎሪ ባክቴሪያ
• መድሀኒቶች ለምሳሌ ፦ አይቦፕሮፊን፣ ዳይክሎፌናክ ፣ አስፕሪን
• አኗኗር ዘዴ ፦ አልኮል መጠጥ ፣ ሲጋራ ማጨስ
• በዘር የሚተላለፍ

ምርመራ
• ቀላል ምልክቶች ከሆኑ ፣ አሳሳቢ ምልክቶች ከሌሉ እንዲሁም ተደጋጋሚ ካልተከሰተ ብዙ የላብራቶሪ ምርመራ አያስፈልግም
• ነገር ግን ህመሙ በጣም አስቸጋሪ ከሆነ ፣ አሳሳቢ ምልክቶች ካሉ እና ተደጋጋሚ ከሆነ የሚከተሉት ምርመራዎች ያስፈልጋሉ

• የኤች ፓይሎሪ ባክቴሪያ ምርመራ ፦ የመጀመሪያ ምርመራ ከሆነ ከደም የሚወሰድ የአንቲቦዲ ምርመራ ማድረግ የሚቻል ሲሆን የሰገራ ምርመራ የአንቲጅን ምርመራ የተሻለ ነው።
• ዩሪያ ብሪዝ ምርመራ ሌላው የኤች ፓይሎሪ ባክቴሪያ ምርመራ ነው
• የላይኛው አንጀት ኢንዶስኮፒ ፦ ይህ ምርመራ የውስጠኛው አንጀት ቁስለት ካለ ለማየት ፣ ለመለካት ፣ ህክምና ለማድረግ እና የመድማት ሁኔታ ካለ ለማቆም ተመራጩ መንገድ ነው
• የራጅ ምርመራ
• ከቁስለቱ የሚወሰድ የናሙና ምርመራ

ለድንገተኛ ህክምና የሚያስፈልጉ ላብራቶሪዎች
• ሙሉ የደም ምርመራ እና የደም አይነት ምርመራ
• የጉበት እና የኩላሊት ምርመራ
• የደም ንጥረ ነገሮች ምርመራ

የጨጓራ በሽታ የሚያስከትላቸው ችግሮች
• የጨጓራ መድማት
• የጨጓራ ጫፍ ጥበት
• የጨጓራ መቦርቦር እና ባክቴሪያዎች ወደተለያዩ የሰውነት ክፍል መሰራጨት
• የጨጓራ ካንሰር

ህክምና
• ህመሙን የሚቀሰቅሱ ነገሮችን ማቆም
• የመጀመሪያ እና ቀለል ላለ ህመም የጨጓራ አሲድ መመረት የሚቀንሱ መድሀኒቶች
• የአንጀት የውስጠኛውን ክፍል ከአሲድ የሚከላከሉ መድሀኒቶች
• የፀረ ተህዋሲ መድሀኒት ለኤች ፓይሎሪ ባክቴሪያ ህክምና
• ኢንዶስኮፒ
• ኦፕራሲዮን እንደ ቫጎቶሚ፣ አንትረክቶሚ እና ፓይለሮፕላስቲ

ጥንቃቄ
• የአልኮል መጠጥ ማቆም ወይም መቀነስ
• የጨጓራ ህመም የሚያመጡ የማስታገሻ መድሀኒቶች በተደጋጋሚ አለመውሰድ
• ሲጋራ ማጨስን ማቆም
• ካፊን የበዛባቸው መጠጦች እንደ ቡና፣ሻይ፣ ለስላሳ መጠጥ መቀነስ
• ለእያንዳንዱ ሰው የተለያየ የምግብ አይነት ህመሙን ሊያስነሳበት ስለሚችል ለይቶ በማወቅ ማቆም ያስፈልጋል።
204 views06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 08:58:37
የማህፀን ፈሳሽ

• የማህፀን ፈሳሽ ሴቶች ወደህክምና ተቋማት እንዲሄዱ ከሚያደርጉ ምክንያቶች አንዱ ነው።
• የማህፀን ፈሳሽ ጤናማ የሆነ ና ጤናማ ያልሆነ ብለን ልንከፍለው እንችላለን።
ጤናማ የማህፀን ፈሳሽ ብዛት የሌለው በቀን ከ 2-4 ሚሊ ሊትር የሚደርስ ነፃ ያለ ፣ ሽታ የሌለው ነው።
• መጠኑ ፣ከለሩና ውፍረቱ ከ ሴት ሴት ሊለያይ ይችላል።

መጠኑ እንዲጨምር ከሚያደርጉ ጤናማ ምክንያቶች መካከል
• እርግዝና
• የእርግዝና መከላከያ እንክብል (ፒልስ) መጠቀም
• የወር አበባ ከታየ በኋላ በ14ኛው ቀን አካባቢ እና የወር አበባ ሊመጣ ሳምንት ሲቀረው ይገኙበታል።
ጤናማ ያልሆነ የምንለው የሚከተሉት ተያያዥ ምልክቶች ሲኖሩ ነው
• ማሳከክ
• ማህፀን አካባቢ መቅላት፣ማቃጠል እና እብጠት
• አረፋ የመሰለ አረንጓዴ /ቢጫ ፈሳሽ
• መጥፎ ጠረን ካለው
• ደም ከቀላቀለ
• በግንኙነት ወቅት ህመም ካለ
እነዚህ ተያያዥ ምልክቶች ካሉ የጤና ባለሙያ ማማከር ተገቢ ነው።

• በተለያየ ባህላዊ መንገድ ወይም በራስ ተነሳሽነት ለማከም መሞከር ሁኔታውን ሊያባብስ ስለሚችል አይመከርም።

ጤናማ ያልሆነ ፈሳሽ እንዳይከሰት ምን ማድረግ ይቻላል?
• በንፁህ ውሀ ወይም ሽታ የሌለው ሳሙና በመጠቀም የውጨኛው የብልት ክፍል መታጠብ ( የገላ መታሻ ወይም ጓንት መጠቀም አያስፈልግም)
• ብልትን ወደ ውስጥ ገብቶ አለመታጠብ
• ለብልት ንፅህና መጠበቂያ ተብለው የሚመረቱ ስፕሬይ ፣ፓውደር ወይም ፈሳሽ ምርቶችን አለመጠቀም
• ከጥጥ የ ተሰራ ፓንት መጠቀም
• ከተፀዳዱ በኋላ በውሀ መታጠብ ሶፍት ወይም ዋይፕስ(baby wipes ) አለመጠቀም
211 viewsedited  05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ