Get Mystery Box with random crypto!

Doctor Adugnaw

የቴሌግራም ቻናል አርማ dradugna — Doctor Adugnaw D
የቴሌግራም ቻናል አርማ dradugna — Doctor Adugnaw
የሰርጥ አድራሻ: @dradugna
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.83K
የሰርጥ መግለጫ

የጤና መረጃዎችንና ምክሮችን የሚያገኙበት ቻናል ነው ። ቤተሰብ ይሁኑና ስለጤናዎ በማወቅ ጤናዎን ይጠብቁ !

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-21 09:40:41

724 views06:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:58:55 የእርግዝና ወቅት ስኳር ምንድነው?

የስኳር ህመም ከቋሚ ህመሞች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን የኢንሱሊን ሆርሞን እጥረት ወይም በትክክል አለመስራት ምክንያት የሚከሰት ነው። የአይን ፣ የኩላሊት ፣የ ልብና የነርቭ ችግሮች የሚያስከትል ህመም ነው።

ስኳር በአራት ዋናዋና አይነቶች ያሉት ሲሆን የእርግዝና ወቅት ስኳር አራተኛው አይነት ስኳር በመባል ይታወቃል።

የእርግዝና ወቅት ስኳር (GDM) ምንድነው?

የእርግዝና ወቅት ስኳር በእርግዝና ሰዓት የሚከሰት የስኳር አይነት ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ በእርግዝና ወቅት የምርመራ የሚገኝ ነው።

በአብዛኛው ከ28 ሳምንት እስከ ወሊድ ብሎም ስድስት ሳምንት ድህረወሊድ ድረስ ይቆያል።
በእርግዝና ሰዓት ከሚገኙት የስኳር አይነቶች 90% የሚሆነው የስኳር አይነት ሲሆን ከእርግዝና በኋላ የሚጠፋ አይነት ነው።

በአብዛኛው የሚታዩ ምልክቶች ባይኖሩትም ከፍተኛ ተጋላጭነት ካለ በምርመራ ሊታወቅ ይችላል።

ምልክቶቹስ?

• የውሃ ጥም
• የሽንት መብዛት
• የምግብ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር
• የልጅ መፋፋት
• የእንሽርት ውሃ መብዛት
• የፅንስ ያፈጣጠር ችግር

አጋላጭ ሁነቶች (risk factors)

• የቤተሰብ የስኳር ህመም
• ያለቅጥ ውፍረት
• የበፊት እርግዝና ስኳር
• የደም ግፊት
• የኮሌስትሮል መብዛት
• በርግዝና ወቅት ያላግባብ ክብደት መጨመር እና ወዘተ...

እንዴት ይታወቃል?

ሃኪሞችሽ አጋላጭ ሁነቶችሽ ካዪ በኋላ ከ24-28 ሳምንት የስኳር ምርመራ ያደርጉልሻል። ይህም ጣፋጭ ስኳር (40% glucose) በአፍሽ ከወሰድሽ በኋላ በየአንድ ሰዓት ልዪነት የደም ስኳር መጠንሽ በመለካት የእርግዝና ስኳር እንዳለ እና እንደሌለ ይነግሩሻል።

በሌላ የምርመራ ዘዴ (HgA1C) በመመርመርም ማወቅ ይቻላል።

ባደጉ አህጉራት ማንኛውም ነፍሰጡር እናት ለስኳር ምርመራና ልየታ የምታደርግ ሲሆን በታዳጊ አገራት የተወሰኑ ነፍሰጡሮች አጋላጭ ባህሪያቸው ታይቶ የሚመረመር ይሆናል

ምክንያቱ ምንድነው?

• የእርግዝና ወቅት ስኳር ለምን እንደሚከሰት በትክክል ምክነያቱ ባይታወቅም ብዙ ሳይንሳዊ ሠላምቶች አሉ።

• የሆርሞን አለመመጣጠን በእርግዝና ወቅት የእንግደልጅ እጅግ በጣም ብዙ ሆርሞኖችን የሚያመነጭ ሲሆን ከእነዚህም PLG (plasental lactogen )አንዱ ነው። ይህም ሆርሞን ኢንሱሊን በህዋሳት ወስጥ እንዳይሰራ በማደናቀፍ የደም ውስጥ ስኳር እንዲጨምር ያደርጋል። ስቴሮይድ ሆርሞን እና የእድገት ሆርሞን እንደዚሁ በተመሳሳይ የኢንሱሊን ስራን በማስተጓጎል እንደ ምክነያት ይነሳሉ።

• አካባቢያዊ ተፅኖ በእርግዝና ወቅት የክብደት መጨመር ህዋሳቶች ለኢንሱሊን ሆርሞን እንዳይታዘዙ ሊያደርግ ይችላል የሚል ሌላ መላምትም አለ።

ለመጀመሪያ ጊዜ በርግዝና ወቅት የታወቀ ስኳር የቆየ መሆኑ አለመሆኑ እንዴት ይታወቃል?

• ከሃያ ሳምንት በፊት የተከሰተ ስኳር
• HgA1C ከ7% በላይ ከሆነ
• የረጅም ጊዜ የስኳር ህመም ውስብስ ችግሮች ካሉ ለምሳሌ የአይን ችግሮች ፣ የኩላሊት ህመም የመሳሰሉት
• የልጅ የአፈጣጠር ችግር ካለ
የቆየ ስኳር አመላካቾች ስለሆኑ በድህረ ወሊድ ጊዜ በድጋሚ ክትትል ያሻል።

ውስብስብ ችግሮች

የእረግዝና ወቅት ስኳር በእናትና በፅንስ ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል

እናት ላይ
• ፅንሱ በመመፋፋቱ ምክንያት ለኦፕራሲዮንና ለመሳሪያ ወሊድ መጋለጥ
• የምጥ መርዘም
• ለልብ ችግር ተጋላጭነት መጨመር
• በወሊድ ወቅት ደም መፍሰስ
• የእንግደ ልጅ መቅደም

ፅንሱ ላይ
• የፅንስ መፋፋት
• ያለጊዜ መወለድ እና የአተነፋፈስ ችግር
• የስኳር ማነስ (hypoglycemia)
• የፅንስ መታፈን
• ሆድውስጥ መጥፋት
• ተደጋጋሚ ውርጃ
• የጨቅላ ቢጫነት
• የጨቅላ ሙቅት መውረድ (hypothermia)

ህክምናውስ?

• የአኗኗር ዘዬ መቀየቀር ፦ ማለትም በእርግዝና ወቅት የሚፈቀዱ መጠነኛ እንቅስቃሴዎችን መድረግ፣ ጣፋጭ ምግቦችን በመተው አልያም በመቀነስ የደም ስኳርን መቆጣጠር ይቻላል።

• መድሃኒት፦ የአኗኗር ዘዴ በመቀየር ካልተስተካከለ ወይም በሃኪምሽ ከታመነበት መርፌ (insulin) ወይም ኪኒን (oral hypoglycemic agent) በመጠቀም የደም ስኳርሽ ማስተካከል ይቻላል።

• የስኳር ህመም ውስብስብ ጉዳቶች እንዳይከሰቱ ቁርስ ከመብላትሽ በፊትና በማንኛውም ጊዜ ምግብ ከበላሽ ከሁለት ሰዓት በኋላ የስኳር መጠንሽን መለካት አትርሺ

• መለካት ብቻ በቂ ስላልሆነ የለካሽውን በመመዝገብ በክትትልሽ ወቅት ለሃኪሞችሽ በማሳየት የመድሃኒትሽ መጠን ለማስተካከል ይረዳል።

• ከፍተኛ የስኳር መጠን ካለሽ ደግሞ ሆስፒታል ተኝተሽ ጥብቅ የፅንስ ክትትል እና የስኳር ልኬት ሊደረግልሽ ይችላል።

እንዴት መከላከል ይቻላል?

አጋላጭ ሁነቶችን በመቀየር ማለትም ከእርግዝና በፊት ክብደት ማስተካከል፣ ጤነኛ የአኗኗር ዘዴን መከተል ፣ ስፓርት እንቅስቃሴ መስራት ፣ ጭንቀት ማስወገድ ፣ አደገኛ አመጋገብ በማስቀረት (ጣፋጭ ፣ አልኮሆል፣ ጮማ እና ጨው) በመተው ፣ በቂ ውሃ በመጠጣት እና በቂ እረፍት በማድረግ) ስኳር እና ሌሎች ቋሚ ህመሞችን መከላከል ይቻላል።

በወቅቱ የእርግዝና ክትትል በማድረግ የስኳር ምርመራ በማድረግ በወቅቱ መታከም።

የወደፊት እጣፈንታውስ?

• የእርግዝና ወቅት ስኳር በአብዛኛው ከወሊድ በኋላ የሚጠፋ ሲሆን የተወሰነው ግን ወደሁለተኛው የስኳር አይነት ሆኖ ሊቀጥል ይችላል።

• የወደፊት የስኳር ህመም ፣ የደም ግፊት እና የልብ ህመሞች ተጋላጭነትን ይጨምራል።

• የወደፊት የእርግዝና ወቅት ስኳር እና አለቅጥ ውፍረትን ያጋልጣል።

• ስለዚህ ድህረ ወሊድ ከስድስት ሳምንት በኋላ የስኳር መጠን በመለካት እና በየ ጊዜው በመመርመር ቋሚ የስኳር ህመም እንደሌለሽ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ዶ/ር ነጋልኝ መቻል ፤ የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት

@HakimEthio
3.4K views18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-27 12:37:52 የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን

የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን (Septic Arthritis) በመገጣጠሚያዎች ዉስጥ የሚፈጠር ኢንፌክሽን ሲሆን ይህም ከሌላ የሰውነትዎ ክፍል ወደ ደምዎ ውስጥ በሚጓዙ ጀርሞች ሊመጣ ይችላል።

ጨቅላ ህጻናት እና አዛውንቶች ብዙውን ጊዜ በመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን የመያዝ እድላቸዉ ከፈ ያለ ነዉ።

የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን ሲኖርብውት የሚከተሉትን ምልክቶች ያሳያሉ ፡ የመገጣጠሚያ እብጠት ፣ የእንቅስቃሴ መገደብ ፣ መቅላት ፣ ህመም እና ትኩሳት የተውሰኑት ናቸዉ።

የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን ድንገተኛ ህመም ስለሆነና ብዙውን ጊዜ ህጻናት ላይ ስለሚከሰት አፍጣኝ ህክምና ያስፈልገዋል።

ሕክምናውም መገጣጠሚያውን በመርፌ ወይም በቀዶ ጥገና ከፍቶ በማጠብ ውስጡ የተጠራቀመዉን ፈሳሽ ወይም መግል ማፍሰስ እንድሁም አንቲባዮቲክ መድሀኒት መስጠት ያስፈልጋል።

ይህ ካልሆነ ግን መገጣጠሚያው ሙሉ በሙሉ ሊጎዳ እና ወደፊት የማይቀለበስ ከፍተኛ ችግር ሊያመጣ ይችላል። ስለዚሀ ከላይ የተዘረዘሩትን ምልክቶች ካዩ ቶሎ ብለው የአጥንት ስፔሻሊስት ያለበት ሆስፒታል መሄድ እንዳይዘነጉ።

ዶ/ር ቃልኪዳን አያሌው ፤ የአጥንትና ድንገተኛ አደጋ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት

@Dradugna

ለበለጠ መረጃ

www.YouTube.com/DoctorAdugnaw

www.dradugnaw.com

#ሼር #ያድርጉ
6.6K views09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 20:12:09 የደም ዓይነትን ማወቅ ለምን ይጠቅማል?
በቅንነት ሼር ያድርጉ

የደም ዓይነትን ማወቅ በርካታ ጥቅሞች አሉት። ከእነዚህ ጥቅሞች መካከል:-

ደም በድንገት በሚያስፈልግ ጊዜ፣ በአደጋ፣ በወሊድ እና በኦፕሬሽን ደም ሊሰጥ ስለሚችል የደም አይነት ማወቅ ጠቃሚ ነው።

የደም ዓይነትን ማወቅ በእርግዝና ጊዜ የሚፈጠርን ችግር ለመከላከል ይረዳል። እናት የደም አይነቷ አር ኤች ፖዘቲቭ ሆኖ የልጁ አር ኤች ነጋቲቭ ከሆነ ያለመጣጣም ችግር ይፈጠራል። ይህም ቀድሞ ከታወቀ መከላከል ይቻላል።

የደም አይነት ስርጭት ለማወቅ ይረዳል። ኦ ፖዘቲቭ በብዛት ያለና በቀላሉ የሚገኝ ሲሆን ኤ ቢ ኔጌቲቭ በጣም በዝቅተኛ ደረጃ ስላለ ለማግኘት ያስቸግራል።

ደም ለመለገስ ይረዳል። ማንኛውም የደም አይነት ያለው ሰው ደም መለገስ ቢችልም አንዳንድ አደጋ በሚከሰትበት ጊዜ የተለየ የደም አይነት በብዛት ሊፈለግ ይችላል። ለምሳሌ:- ኦ ኔጌቲቭ ደም በብዛት ሊፈለግ ይችላል።

አንዳንድ ጥናቶች የደም አይነትን ከተለያዩ በሽታዎች ሲያያዝ ያሳያሉ።

ለበለጠ መረጃ
http://t.me/Dradugna

www.YouTube.com/DoctorAdugnaw

www.dradugnaw.com

#ሼር #ያድርጉ
4.3K views17:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-26 15:41:49 የልብ ህመም የማስጠንቀቂያ ምልክቶች

ለልብ ህመም አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በጣም ብዙ ነገሮች አሉ ከነዚህም መካከል፦

※ ዕድሜ
※ የዘር ሃረግ
※ ከፍተኛ የደም ግፊት
※ ከፍተኛ የኮሌስትሮል መጠን
※ ከመጠን ያለፈ የሰውነት ክብደት
※ የተመጣጠነ ምግብ አለመውሰድ
※ አልኮል መውሰድ
※ ጭንቀት
※ እንቅስቃሴ አለማድረግ ለልብ ህመም በሽታ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

የልብ ህመምን በጊዜ ወይም በፍጥነት ለማወቅ የሚከተሉትን ጠቃሚ ምልክቶች ይማሩ ወይም ይወቁ፦

1. የድካም ስሜት እና የትንፋሽ ማጠር።
2. ላብ ማላብ፦ ቀን እና ሌሊት።
3. የምግብ አለመፈጨት፣ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ።
4. የደረት ህመም፣ ግፊትና ምቾት ማጣት።
5. በመላው ሰውነት ላይ የሚከሰት ህመም።

ለበለጠ መረጃ
http://t.me/Dradugna

www.YouTube.com/DoctorAdugnaw

www.dradugnaw.com
3.3K views12:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 16:04:41 #ፊታችሁን ፈፅሞ ማስነካት የሌለባችሁ #አምስት ነገሮች!

1. #ሎሚ : ሎሚ ፊት ላይ ማድረግ አደገኛ ነው ምክንያቱም ሎሚ ውስጥ ያለው ሲትሪክ አሲድ የአሲድ መጠኑ ደረጃ ከ2-3 ሲሆን የቆዳችን የኬሚካል አሰራር ደግሞ የአሲድ መጠኑ ከ4-4.5 ነው ። ስለዚህ የሰውነት ቆዳ ሎሚ ከተቀባ ሊጎዳ ይችላል በተለይም ተቀብቶ ወደፀሀይ ከወጡ ቆዳዎን ሊያቃጥለውና ጠባሳ ሊፈጥር ይችላል ። ሎሚ የሚጠቀሙ ከሆነ የሚከተሉትን ማድረግ የተሻለ ነው ።
1. ማቅጠን አለብዎት በንፁህ ውሀ
2. አድስ (fresh) ሎሚ ይጠቀሙ
3. ከተጠቀሙት በኋላ ሳይታጠቡ ለፀሀይ አይጋለጡ።

2. #ቫዝሊን ( Vaseline ) - በጣም ሀይለኛ የሆነ ቅባት (fat) ያለውና በሰውነት ቆዳ ላይ ያሉ ባክቴሪያዎችን እና ፈንገሶችን በመሸፈን ከመጠን በላይ እንዲራቡና የተለያዩ በሽታዎች ቡግርን ጨምሮ እንዲያመጡ ሊያደርግ ይችላል ። ከዚህም በተጨማሪ የሰውነት ቆዳ ቀዳዳዎችን እንዲደፈኑ በማድረግ ብዙ የቆዳ እብጠቶች ያመጣል ። በተለይም ለቡግር ተጋላጭና ቀላ ያለ የቆዳ እብጠት ካለ ቫዝሊንን መጠቀም ያቁሙ ።

3. #የመጋገሪያ_እርሾ ( baking soda ) እና ዱቄት ሳሙናዎች (washing soda) _ እነዚህ ሁለቱ ከsodium carbonate የሚሰሩ ሲሆን በውሀ በሚሟሙበት ጊዜ ደካማ የአልካላይን ኬሚካል ናቸው ። ቆዳ ደግሞ የደካማ አሲድ ኬሚካል ፀባይ ነው ያለው ። ስለዚህ ይህን የሚጠቀሙ ከሆነ የሰውነት ቆዳ የኬሚካል አሰራር ሁኔታ እየቀየሩ ነው ማለት ነው። የሰውነት ቆዳ የኬሚካል ለውጥ ካለው ደግሞ ለተለያዩ በሽታዎች ይጋለጣል ።

4. #የጥርስ_ሳሙና (toothpaste )- የጥርስ ሳሙና ቆዳን irritate የሚያደርግ ፣ የሚቧጥጥና የሚያቀላና የቆዳ መቆጣት የሚያመጡ የተለያዩ ኬሚካሌች አሉት ። በተጨማሪም የቆዳ ድርቀትን በማምጣት ወዝ የሚያመርቱ ሴሎችን ከመጠን በላይ ወዝ እንዲያመርቱ ሊያደርጋቸው ይችላል ።

5. #አልኮል_ያላቸው_ቅባቶች- አልኮል ያለቸው ቅባቶችና የፊት መጥረጊያዎችን መጠቀም የቆዳ ድርቀት ያመጣል ። በተደጋጋሚ የሚጠቀሙ ከሆነ የቆዳ ድርቀትን ለመከላከል ሲል ወዝ የሚያመርቱ ሴሎች ከፍተኛ የሆነ ወዝ እያመረቱ ይመጣሉ ይህም ከፍተኛ የሆነ ወዝ በሰውነት ላይ እንዲመረት በማድረግ ሊረብሽ ይችላል ።

ለበለጠ መረጃ
http://t.me/Dradugna

www.YouTube.com/DoctorAdugnaw

www.dradugnaw.com
3.4K views13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-25 10:18:24 የፊንጢጣ_ላይ_ኪንታሮት

የፊንጢጣ ኪንታሮት(hemorrhoid) የምንለው በፊንጢጣ ውስጥ ወይም በፊንጢጣ ዙሪያ የሚገኝ የደም ቱቦ (veins) በውስጣቸው ደም አከማችተው ሲለጠጡና ሲሰፉ የሚፈጠር ችግር ሲሆን ይህ የተጠራቀመው የደም ሲል ደግሞ የራሱን እድገት በመጠንና በቁመት ሲጨምር ነው።

በብዙ ሰዎች ላይ የሚፈጠርና መጥፎ ስሜትን የሚፈጥር ችግር ነው።

ሁለት አይነት ኪንታሮቶች አሉ

ውጫዊ ኪንታሮትና
ውስጣዊ ኪንታሮት

ውጫዊ ኪንታሮት የምንለው በፊንጢጣ ዙርያ የሚፈጠር ሲሆን በቆዳ የተሸፈነ ነው። ምልክቶቹም በፊንጢጣ ዙሪያ ማቃጠል፣ማሳከክ፣ህመም ስሜት፣ዙሪያውን ማበጥና መድማት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ውስጣዊ ኪንታሮት
የማይዳሰስ እና ብዙ የህመም ስሜትም የለውም በመፀዳዳት ወቅት ብቻ የማቃጠልና ሰገራን የመዝጋት ቀጥሎም ደመቅ ያለ ደም መፍሰስ ሊታይ ይችላል።

ኪንታሮት እንዲፈጠር የሚያደርጉ ምክንያቶች
የደም ቱቦዎች መለጠጥ
ሰገራን ለማስወገድ ማማጥ
ሽንት ቤት ውስጥ ለብዙ ጊዜ መቆየት
የሰገራ ተደጋጋሚ መድረቅ
ውፍረት
እርጉዝ መሆን
የዕፅዋት ተዋፅኦዎችን አለመመገብ
ከባድ ነገሮችን በተደጋጋሚ ማንሳት

መከላከያ መንገዶች
ጥራጥሬ፣ፍራፍሬና ቅጠላ ቅጠልን መመገብ
በቂ ውሃ መጠጣት
ብዙ አለማማጥ
ሰገራን አለመያዝ/በጊዜው መፀዳዳት
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ
አንድ ቦታ ላይ ለረጅም ሰዓት መቀመጥን ማስወገድ
ሽንት ቤት የመቀመጥ ቆይታን መቀነስ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ኪንታሮትን በቀላሉ መከላከል እንደሚቻል ሁሉ በቀላሉ መታከም ይቻላል። ለዚህም የሚቀቡ መድሀኒቶች ያሉ ሲሆን እነሱን ተጠቅመን መሻሻል ካላሳየ ሀኪም ጋር ሄዶ መታየት ይኖርብናል።

http://t.me/Dradugna

www.YouTube.com/DoctorAdugnaw

www.dradugnaw.com
3.0K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 08:57:46 ይታሚን ዲ
የፀሀይ ብርሀን ቫይታሚን ዲ ኖሮት አያውቅም፣ የፀሀይ ብርሀን የሚይዘው እንደስሙ በአይን የሚታይ እና የማይታይ UVA, UVB, UVC, Infrared , etc እየተባሉ የሚጠሩ የብርሀን ሞገዶችን ነው።

ቨይታሚን ዲ የሚሰራው በጉበታችን ውስጥ፣ ኮሌስትሮልን ወደ ቅድመ ቫይታሚን ዲ በመቀየር ነው።

ነገር ግን ጉበታችን ውስጥ የተሰራው ቅድመ ቫይታሚን ዲ፣ ሙሉ ለሙሉ ቫይታሚን ዲ ሆኖ ስራላይ ለመዋል፣ ጤናማ የኩላሊት ስራ እና የፀሀይ ብርሀንን በዋነኝነት ይፈልጋል።

ማለትም ቫይታሚንየምግብ እጥረት፣ ከፍተኛ የኩላሊት ወይም የጉበት ድክመት ያለበት ሰው፣ የፀሀይ ብርሀን ቢያገኝ እንኳን፣ ለቫይታሚን ዲ እጥረት ይጋለጣል ማለት ነው።

የዚህ ቪታሚን ፣ዋነኛ ጥቅም ለአጥንት ጥንካሬ የሚጠቅሙትን ካልሲየም እና ፎስፈረስ የተባሉ ንጥረ ነገሮችን ፣ከአንጀት ወደሰውነት ማስገባት ነው።

በደም ውስጥ ያለው መጠን ካነሰ፣ በህፃናት ላይ
የአጥንት ልምሻ፣

በትላልቆች ላይ ደሞ ፣

ስር ሰደድ የጡንቻ ህመም
የአጥንት ህመም እና መሳሳት እና
የፀጉር መሳሳትን ሊያስከትል ይችላል።

የፀሀይ ብርሀን ማነስ እና የምግብ እጥረት ካለ፣
ከ6 ሳምንት በላይ ለረጅም ግዜ የሚቆይ ተቅማጥ መኖር፣
ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የኩላሊት እና የ ጉበት ድክመት መኖር፣ በሰውነት ላይ የ ቪታሚን ዲ እጥረት እንዲኖር የሚጋብዙ
ምክኒያቶች ናቸው።

ህክምናው በጣም ቀላል ነው፣ ለተጓዳኝ ችግሮች ህክምና መስጠት እና፣ እንደየ እድሜ ክልሉ ፣ከ400 እስከ 50,000 iU የሚሆን መጠን ያለው ቪታሚን ዲ ከ 6 እስከ 8 ሳምንት በሀኪም ትእዛዝ ይሰጣል።

ይህ ቫይታሚን ዲ ያለ ሀኪም ትእዛዝ ከልክ በላይ ከተወሰደ ግን

ከፍተኛ ራስ ምታት እና ድካም
ማቅለሽለሽ እና ማስታወክ
ውሀ ጥም እና ቶሎ ቶሎ መሽናት የመሳሰሉ ምልክቶች ይታያሉ።

http://t.me/Dradugna

www.YouTube.com/c/DoctorAdugnaw
2.3K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 15:06:38 በጨጓራዎ ውስጥ የሚመነጨውን ከመጠን በላይ አሲድ (Hyperacidity) በቀላሉ በማስወገድ የቃር ችግሮን በነዚህ ምክሮች ያስወግዱ ብሏቹሃል ሀኪሙ!

ምግብን እንዲፈጭ የሚያደርግ ከጨጓራ የሚመነጭ ፈሳሽ ጋስትሪክ ጁስ ይባላል፡፡ የሚመነጨው አሲድ ማለትም ሐይድሮክሎሪክ አሲድ የበዛ እንደሆነ ሐይፐርአሲዲቲ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ይህ ነው በጨጓራ ላይ ቁስል የሚያስከትለው፡፡ ከመጠን በላይ አሲድ በጨጓራችን ውስጥ መከሰቱን የሚሳብቁ #ምልክቶች:

1. የሚያቃጥል የሕመም ስሜት ከጨጓራ ተነስቶ እስከ ደረት አልፎም ጉሮሮ ጋር የሚደርስ ቃር፡፡
2. መራራ አሲድ ወደ ጉሮሮ ወይም አፍ መድረስ፡፡
3. ሆድ መነፋት፡፡
4. ደም ወይም ጥቁር ነገር የቀላቀለ አይነምድር፡፡
5. ደም የተቀላቀለ ትውኪያ፡፡
6. ማግሳት፡፡
7. ምግብ ያለመፈጨት ችግር፡፡
8. ስቅታ፡፡
9. ማቅለሽለሽ፡፡
10. ያለምንም ምክንያት ክብደት መቀነስ፡፡
11. ደረቅ ወይም ፉጨት ያለው ሳል ወይም ዘላቂ የጉሮሮ ቁስል፡፡
12. የጆሮ ሕመም፡፡

ከመጠን በላይ አሲድ በጨጓራችን ውስጥ እንዲከሰት የሚያደርጉ አባባሽ #ምክንያቶች:
1. ብዙ ምግብ መመገብ ወይም ከተመገቡ በኃላ ወዲያውኑ ጋደም ማለት፡፡
2. ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት፡፡
3. ከባድ ምግብ ተመግበው በጀርባ መተኛት ወይም ወዲያውኑ አጎንብሰው ስራዎችን መስራት፡፡
4. በመኝታ ጊዜ ምግብ መመገብ፡፡
5. የአዕምሮ ውጥረት
6. አሲድ ያላቸው እንደ ብርቱካንና ሎሚ ፍራፍሬዎችን መመገብ፣ ከዚህ በተጨማሪ ቲማቲም፣ ቸኮሌት፣ ነጭና ቀይ ሽንኩርት ወይም ቅመም ወይም ቅባት ያላቸውን ምግቦች መመገብ፡፡
7. የአልኮል፣ የለስላሳና ካፊን ያለባቸው ቡናና ሻይ ምግብዎችን መመገብ፡፡
8. ሲጋራ ማጨስ
9. ነፍሰጡር መሆን
10. አንዳንድ መድኃኒቶች እንደ አስፕሪን፣ አይቢፕሮፍን፣ አንዳንድ የጡንቻ ማፍታቻ ወይም የደም ግፊት ሕክምና መድኃኒቶችን መውሰድ፡፡

#መፍትሔው:
1. ቅመም የገባበትና ማጣፈጫ ያለበትን ወይም የተጠበሰ ምግብ አይብሉ፡፡
2. አልኮል መጠጦችን ያስወግዱ፡፡
3. ወተት፣ ክሬም፣ ቅቤ ይመገቡ፡፡
4. ሙዝ፣ ማንጎ፣ ሐብሐብና ቴምር የዘውትሩ፡፡
5. ምግብዎን ቶሎ ቶሎ አይመገቡ፡፡ በደንብ አኝከው ይዋጡ፡፡
6. በቀን ቢያንስ 8 ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ፡፡
7. ጣፋጭ ፣ቆምጣጣና ከፊኖ ዱቄት የተዘጋጁ ምግብዎችን አይመገቡ፡፡
8. ጠዋት ፍራፍሬ፣ምሳ የተቀቀለ አትክልት መብላት ያሻል ከምግብ በፊት ሁል ጊዜ አንድ ኩባያ አጥሚት ይጠጡ፡፡
9. በእግር መሄድ ያዘውትሩ ፡፤
10. በተቻለ መጠን ደስተኛ ይሁኑ፡፡
11. ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ፀረ- አሲድ መድኃኒት በመግዛት በመድኃኒት ባለሙያ ምክር ይውሰዱ፡፡
በዶ/ር ሶፎኒያስ ኤርሚያስ

http://t.me/Dradugna

www.YouTube.com/c/DoctorAdugnaw
2.4K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 09:16:05 አለርጂክ ምንድነው?

አለርጂ የሰውነት የመከላከያ ስርአት ከሰውነት ወጪ ባእድ ለሆኑ ነገሮች የሚሰጠው ምላሽ ነው።እነዚህ ባእድ ነገሮችም(Allergens) በተፈጥሮ ጉዳት የማያደርሱ ሲሆኑ አንዳንድ የምግብ ዓይነቶች፣ ለማዳ እንሰሳት ፣የአበባ ፖለንና ፍግ የመሳሰሉ ሊሆኑ ይችላሉ ።

የሰውነት የመከላከያ ስርአት ሚናው ሰውነትን ሊጎዱ የሚችሉ ባእድ ነገሮችን መዋጋት ነው። ይህን የሚያደርግው ጎጂን ከማይጎዳ ነገር በመለየት ነው። አለርጂ ያለበት ሰው ግን የማይጎዳን ባእድ ነገር እንደ ጎጂ አድርጎ በመተርጎም ምላሽ ይሰጣል።በዚህ ባልተገባ ምላሽም አለርጂ ያለበት ሰው ይታመማል ።

#የአይን የአለርጂ ምልክቶች ፨፨፨
*የአፍንጫ መዘጋት ኮንጀስሽን
*ውሃ አይነት ፈሳሽ ከአፍንጫ መውጣት
*የአይን ማበጥና ማሳከክ
*ማስነጠስ
*የቆዳ ሽፍታና ማሳከክ
*የጉሮሮ ህመም

#አለርጂን የሚቀሰቅሱ ነገሮች ፨፨፨
*የቤት እንሰሳት፣በረሮ፣ጉንዳን ፣ፋንዲያ
*መድኃኒት፦ በተለይ ፔንሲሊንና ሰልፋ መድኃኒቶች
*ምግቦች ፦ወተት ፣ለውዝ አሳ የመሳሳሉ
*በነፍሳት መነደፍ ፥ ንብ፣ተርብ ፣ቢንቢ
*የአበባ ብናኝ
*ግላቭና ኮንዶም ውስጥ ያሉ ኬሚካሎች
እነዚህን ነገሮች አውቆ ራስን መከላከል አስፈላጊ ሲሆን ከታመሙ በኋላ ግን የህክምና አማራጮች አሉ።

#የህክምና አማራጮች
*አንቲሂስታሚን መድሀኒቶች፦ ዳይፌነሃይድራሚን፣ሲትሪዚንሎራቲዲን
*ስቴሮይድ የተባሉ የተለያዩ መድኃኒቶች
*ኢሚኖቴራፒ
*ኢፒኔፍሪን
*ሌሎችም

አለርጂ አንዳንድ ጊዜ የትንፋሽ ማጠር፣ ሾክ ውስጥ መግባት ፣ራስ መሳትን በማስከተል ለህይወት አስጊ ደረጃ ሊደርስ ይችላል ። ይህ በሚከሰትበት ጊዜ ፈጥኖ ጤና ተቋም መሄድ ያስፈልጋል።

http://t.me/Dradugna

www.YouTube.com/c/DoctorAdugnaw
2.4K views06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ