Get Mystery Box with random crypto!

የሞባይል ስልካችን #ዳታ_ኮኔክሽን እየጠፋ ወይም ሲግናሉ ደካማ እየሆነ ሲያስቸግረን ምን ማድረግ እ | Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹

የሞባይል ስልካችን #ዳታ_ኮኔክሽን እየጠፋ ወይም ሲግናሉ ደካማ እየሆነ ሲያስቸግረን ምን ማድረግ እንችላለን!!

ኢንተርኔት እየተጠቀምን የሞባይል ዳታ ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ እንቸገራለን፡፡አንዳንዴ አስቸካይ ስራ ለምስራት ፈልገን የኢንተርኔት ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ ወይም ጭራሽ እየጠፋ መስራት የምንፈልገውን ስራ ለመስራት እንቸገራለን፡፡

የዳታ ኮኔክሽናችን እየተንቀራፈፈ ወይም እየጠፋ በሚያስቸግረን ሰዓት ኮኔክሽናችን እንዲሻሻል(BOOST) ለማድረግ የሚያስችሉ 3 ቲፖችን ላካፍላችሁ፦

1ኛ፡- የሞባይላችሁ Airplane Modeን “ON” ማድረግና “OFF” ማድረግ፦
Airplane Modeን “ON” ካደረጋችሁ በሃላ ቢያንስ 30 ሰከንድ ጠብቃችሁ Airplane Modeን “OFF” አድርጉት፡፡አሁን ዳታ ኮኔክሽናችሁ የተሻለ ይሆናል፡፡

2ኛ፡- ሞባይል ስልካችንን (#Restart) ማድረግ፦
ሞባይል ስልኮች miniature computers በመሆናቸው ማለትም ባህሪያቸው እንደኮምፒውተር በመሆኑ አንዳንድ ችግሮች ሲገጥሙን ስልካችንን አጥፍተን ስናበራ የገጠሙን ችግሮች ይስተካከላሉ፡፡ የኮኔክሽን ችግር ሲገጥመንም ስልካችንን #ሪስታርት ስናረገው ኮኔክሽናችን ይሻሻላል፡፡

3ኛ፡- ሲም ካርዳችን ከስልካችን ማውጣት(Remove your SIM card)፡
ሞባይል ስልካችንን #ሳናጠፋ ሲምካርዳችንን አውጥተን መልሰን ማስገባት፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን በማድረግ ኮኔክሽንናችን እንዲሻሻል ማድረግ እንችላለን።

የፌስቡክ ገፄን ተቀላቀሉ ፦
https://www.facebook.com/Tvdotcomshow?mibextid=ZbWKwL