Get Mystery Box with random crypto!

Belay Bekele weya

የቴሌግራም ቻናል አርማ donbililiti — Belay Bekele weya B
የቴሌግራም ቻናል አርማ donbililiti — Belay Bekele weya
የሰርጥ አድራሻ: @donbililiti
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 9.25K
የሰርጥ መግለጫ

ቤት አልባ ገጣሚ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-09 22:24:24
አንዱ ካንዱ ረጋጭ ፣ ነጥቆ የሚይዘን
ኳስ ህዝቦች ነን እኛ!
ሁሉም ለራሱ ግብ ፣ በ'ግሩ ሚጠልዘን!!

።።።
13.2K views19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 20:07:05
አፋኞችን ጠልቶ ፣ መጥቶ በፍቅር ስም
አስም ሆነ ዘመኑ ፣ አያስተነፍስም !
12.5K views17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 19:42:02
ምን አይነት ቄስ ናቸው ፣ አሽሙር የለመዱ
እኔ "አባት ይፍቱኝ" ስል
"አብይ ይፍታህ" ብለው ፣ አሳልመውኝ ሔዱ
10.9K views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 22:41:18
ይሔ አበበ ህዝብ
ሚበላው በሶ አጥቶ ፣ መከራ ሲበላ
ስናይፐር ይዟል ፣ ጩቤ ጥሎ ጫላ።
ጣሳ ማጠብ ትቶ ፣ ጨቡዴ ኪስ ያጥባል
ሀገር ስትበለፅግ
ይባስ ይጨልማል ፣ ሊነጋ ነው ሲባል
14.6K views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 18:50:01 ማመን እና ማወቅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ
ያወኩትን እውነት ...
ማመን ቢቸግረኝ ፣
"ትመጣለች " እያልኩ ፣ እጠብቅሻለሁ፡፡
"አትመጣም" እያለ...
ለሚነግረኝ ሁሉ ፣ መቅረትሽን አውቆ
"የቀረበት እንጂ ...
የመጣለትማ ፣ አያውቅም ጠብቆ"
ስል እመለሳለሁ
በቃ ትመጫለሽ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ!!!
12.9K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-19 14:14:26
የፌስቡክ አካውንቴ በሪፖርት አቃጣሪዎች ምክንያት ላተወሰነ ወር ታግቷል። ወዳጅ ጠላቶቻችሁን ወደዚህ ቴሌግራም ቻናሌ እንዲያፈገፍጉ ታስተዋውቁልኝ ዘንድ እጠይቃለሁ።
12.3K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 22:07:12 ተራ የሚመስል ከባድ ቃል "መታገስ መፍራት አይደለም!!!"
15.2K views19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-29 18:10:11
1,422,950.00 ብር ደርሰናል።

እናመሰግናለን

1,577,050.00 ይቀረናል።

ውዲቷ አገራችን በእኛው በልጆቿ ምክንያት የገባችበት መከራ በጣም የሚያሳዝን ነው። አሁን አሁን ብዙኃኑን ይቅርና የአንድ ግለሰብ ሕይወት እንኳን ለማትረፍ ትኩረታችንን የሚነጥቅ ጭንቅ ውስጥ መሆናችን ማሰብ በእጅጉ ሀዘን ውስጥ ከቶኛል።

ምነው ሰላማችን በተመለሰለን።

ቸር አምላክ በረዳንና ሁላችንም ምነው ልባችን በገራ!!

እናንተ የአንዲት ምስኪንን ወጣት ነፍስ ለማዳን የተረባረባችሁ ንጹሐን ቸር አምላክ ከበረከቱ ሁሉ ያድላችሁ። የምትወዷትን አገራችሁን ሰላም አድርጎ ይካሳችሁ።

አሁንም ለእህታችን ነቢያት ሰዒድ ሕይወት ድረሱልን።

አስተያየት መጻፍ ላይክ ማድረግና ሼር ማድረግ የዚህን መልዕክት ተደራሽነት ይጨምረዋልና። በምርቃትም ጭምር አብራችሁን ሁኑ።

ክብረት ይስጥልኝ።

የሒሳብ ቁጥር
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ፋጡማ ሰኢድ
1000441500665

ለበለጠ መረጃ ስልክ
+251934461899
+251901085189

እባካችሁን ገንዘቡን እንዳስገባችሁ ስሊፑን መላክ አትርሱ።

ውለታ መላሽ ያድርገኝ
ወንድማችሁ ያሬድ ሹመቴ
15.6K views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ