Get Mystery Box with random crypto!

ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች

የቴሌግራም ቻናል አርማ doctorfasil — ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች
ርዕሶች ከሰርጥ:
Kids
Subscribe
የቴሌግራም ቻናል አርማ doctorfasil — ብሩህkids - ዶ/ር ፋሲል መንበረ (የህፃናት ሕክምና ስፔሻሊስት እና ረዳት ፕሮፌሰር) - የህፃናት ጤና እና ስነ ምግብ ምክሮች
ርዕሶች ከሰርጥ:
Kids
Subscribe
የሰርጥ አድራሻ: @doctorfasil
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 36.48K
የሰርጥ መግለጫ

በዝህ የቴሌግራም ቻናል
👉 ስለ ህፃናት የጤና ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው
👉 ስለ ጨቅላ ህፃናት እና ታዳጊ ህፃናት እንክብካቤ
👉 ስለ ህፃናት አመጋገብ
👉 ስለ ህፃናት አስተዳደግ ወሳኝ ወሳኝ መረጃዎች ይቀርባሉ
❤️ ማንኛዉም አይነት የህፃናት ሕክምና(የቆዳ፣ የአይን፣ የነርቭ ፣የአንገት በላይ እና ሙሉ የህፃናት የዉስጥ ደዌ ሕክምና ቀጠሮ ለማስያዝ ይደውሉ::
👉 0984650912

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-13 15:47:23 #ህፃናት ምግብ መራጭ/ #picky eater/ እንዳይሆኑ ምን ማድረግ አለብን





ሙሉ መረጃውን youtube ቻናልችን ላይ ያገኛሉ

#ብሩህkids - youtube ቻናልችን አዳዲስ መረጃዎችን ዘውትር ማክሰኞ ሐሙስ እና ቅዳሜ 7:30 ላይ እንቀርባለን #subscribe ያድርጉ

ለሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927

ባሉበት ሆነው ማማከር ከፈለጉ 9394 ወይም 0964686464 ይደውሉ
14.6K viewsDr.Fasil, edited  12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-10 07:21:43
ዒድ ሙባረክ
13.2K viewsDr.Fasil, edited  04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-09 19:31:03 #እርጉዝ #እናት በፍፁም መመገብ የሌለባት 7 ምግቦች




#ብሩህkids - youtube ቻናልችን አዳዲስ መረጃዎችን ዘውትር ማክሰኞ ሐሙስ እና ቅዳሜ 7:30 ላይ እንቀርባለን #subscribe ያድርጉ

ለሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927

ባሉበት ሆነው ማማከር ከፈለጉ 9394 ወይም 0964686464 ይደውሉ
13.2K viewsDr.Fasil, edited  16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 09:48:16 ኦቲዝም እና ዳውን ሲንድረም ልዩነታቸው ምንድነው ሙሉ መረጃውን youtube ቻናልችን ላይ ያገኙታል




#ብሩህkids - youtube ቻናልችን አዳዲስ መረጃዎችን ዘውትር ማክሰኞ ሐሙስ እና ቅዳሜ 7:30 ላይ እንቀርባለን #subscribe ያድርጉ

ለሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927

ባሉበት ሆነው ማማከር ከፈለጉ 9394 ወይም 0964686464 ይደውሉ
14.4K viewsDr.Fasil, edited  06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 15:54:37 ዛሬ መጋቢት 24 አለምአቀፍ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው!

ስለ የኦቲዝም ምን ያህል ያውቃሉ

ከ60 ልጆች አንዱ ኦቲዝም ሊኖርበት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

CDC አሁን ባወጣው መረጃ መሰረት አሜሪካ ውስጥ ከ 35 ህፃናት አንዱ ላይ ኦትዝም እየተገኘ እንደሆነ አሳውቁዋል

ወላጆች ልጃቸው ኦቲዝም እንዳለበት ሲነገራቸው ወላጆች ብዙ አይነት ስሜቶች ይሰማቸዋል። ዜናው የወላጆችን ህይወት በእጅጉ የሚለውጥ ዜና ነው። ወላጆች ለልጃቸው ያላቸው ፍቅር እንዳለ ሆኖ ሀዘን፣ ንዴት፣ ጭንቀት ሊሰማቸው ይችላል።

ጫናው የበለጠ እናቶች ላይ ያይላል። ልጃቸውን ለመንከባከብ ብለው ብዙ እናቶች ስራቸውን ትተዋል። ብዙ እናቶች ከማህበራዊ ህይወት ተገልለዋል። ብዙ እናቶች ለራሳቸው ጊዜ ሰጥተው ተዝናንተው አያውቁም። ብዙ ትዳሮችም ጫና ውስጥ ይገባሉ።

ወላጆች ማድረግ ያለባቸው የመጀመሪያ ነገር ስለኦቲዝም በደንብ ማወቅ ነው። ይሄ ግራ መጋባቱን ወደ እቅድ፣ ሀዘኑን ወደ ተግባራዊ እገዛ፣ ጭንቀቱን ወደ አዎንታዊ ስሜት ይለውጠዋል።

በመቀጠል  ልዩ  ድጋፍ የሚፈልጉ ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ እገዛ ማድረግ ነው። እነዚህን ለማድረግ የአእምሮ ሀኪም ወይም የስነ ልቦና ባለሞያ እንዲሁም የልዩ ፍላጎት አስተማሪዎች ማማከር ጥሩ ነው።

ህክምናውን የካቲት 12 ሆስፒታል በሚገኘው የህፃናት የአእምሮ ህክምና ወይም የግል የአእምሮ ህክምና ተቋማት ይገኛል።

በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች እንድናውቅላቸው የሚፈልጓቸው 10 ነገሮች፦

1. ካለብኝ ኦቲዝም ይልቅ ትኩረታችሁ እንደማንኛውም ልጅ/ሰው መሆኔ ላይ ይሁን።

2. በስሜት ህዋሳት አማካኝነት የማገኛቸው መረጃዎች ከአብዛኛዎቻችሁ በተለየ ሊረብሹኝ ይችላሉ።

3. አንዳንድ ነገሮች እንደተነገሩኝ ወዲያውኑ ላልረዳቸው እና ምላሽ ላልሰጥ እችላለሁ።

4. በየእለቱ በድግግሞሽ የሚደረጉ ነገሮችን መረዳት ይቀለኛል። ድግግሞሽ የምማርበት መንገድ መሆኑን እወቁልኝ።

5. ከሌሎች ልጆች ጋር አታነፃፅሩኝ።

6. እጃችሁን እየጎተትኩ የምፈልገውን የማሳያችሁ በቃላት ሀሳብን እንዴት እንደምገልፅ ስለማላውቅ ነው።

7. ስታስተምሩኝ በቃላት ብቻ ከምትነግሩኝ ይልቅ ብታሳዩኝ እና ብታስነኩኝ በቀላሉ ነገሮችን መረዳት እችላለሁ።

8. ከሚያቅተኝ ነገር ይልቅ የምችለው ላይ አተኩሩ።

9. ከሌሎች ጋር መሆን እፈልጋለሁ ግን እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ አስተምሩኝ።

10. ያለምክንያት ውደዱኝ ይገባኛልና።
ያለ አዕምሮ ጤና ፤ጤና የለም

#April2  World Autism Awareness Day!

በመአዛ መንክር -ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

ስለ የኦቲዝም ምልክቶች ሙሉ መረጃ ነገ እናቀርባለን በyoutube እና በዝህ ቴሌግራም ይከታተሉን ከታች ያለውን ሊንክ ይከፈቱ

Youtube : https://www.youtube.com/@DrFasilPediatrician

ማንኛዉም አይነት የህፃናት ሕክምና ማድረግ ካሰቡ በዝህ ስልክ ደውለው ቀጠሮ ያስይዙ
0984650912
12.9K viewsDr.Fasil, edited  12:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 17:29:41 #ተደጋጋሚ #ቶንስል #ህመም 5 ምክንያቶች




#ብሩህkids - youtube ቻናልችን አዳዲስ መረጃዎችን ዘውትር ማክሰኞ ሐሙስ እና ቅዳሜ 7:30 ላይ እንቀርባለን #subscribe ያድርጉ

ለሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927

ባሉበት ሆነው ማማከር ከፈለጉ 9394 ወይም 0964686464 ይደውሉ
13.5K viewsDr.Fasil, edited  14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 12:45:53 የእናት #ጡት #ወተት መጠንን ለመጨመር የሚረዱ 10 መፍትሄዎች





#ብሩህkids - youtube ቻናልችን አዳዲስ መረጃዎችን ዘውትር ማክሰኞ ሐሙስ እና ቅዳሜ 7:30 ላይ እንቀርባለን #subscribe ያድርጉ

ለሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927

ባሉበት ሆነው ማማከር ከፈለጉ 9394 ወይም 0964686464 ይደውሉ
13.6K viewsDr.Fasil, edited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-27 15:28:26 በእርግዝና ወቅት የማይመከሩ መድሃኒቶች

በእርግዝና ወቅት እናት የምትወስዳቸው አብዛኞቹ መድሀኒቶች ወደ እንግዴ ልጅ የማለፍ እድል ይኖራቸዋል(መጠኑ ቢለያይም)

ከመድሀኒቶች ዉስጥ ስሪታቸዉ ተለቅ ያሉ ንጥረ ነገር ያላቸዉ እንደ ሂፓሪን(የደም ማቅጠኛ )እና ኢንሱሊን (ለስኳር ህመም)የሚወሰዱት ወደፅንስ የማለፋቸዉ እድላቸዉ አነስተኛ ነዉ።
በአብዛኛዉ የአፈጣጠር ችግሮች (65%)መንስኤዎች አይታወቅም።የተቀሩት 25% የሚከሰቱት የዘረመል (genetics )ችግሮች ሲሆኑ ከመድሃኒቶች ከመዉሰድ የሚፈጠሩ የፅንስ የአፈጣጠር ችግሮች ከ2-3% ይሆናሉ።

በእርግዝና ወቅት የሚወሰዱ መድሀኒቶች በፅንሱ ላይ ችግር የመፍጠራቸዉ እድል የሚወሰነዉ በእርግዝናዉ የጊዜ ወቅት፣ በሚወሰደዉ የመድሀኒት አይነትና በመድሀኒቱ በሚወሰደዉ መጠኑ ይወሰናል።

1. እርግዝና ከተከሰተ ከ31ቀን ባነሰ የሚወሰዱ በእርግዝና ወቅት የተከለከሉ መድሀኒቶች አንዲት እርጉዝ ብትወስድ የሚፈጠረዉ ሙሉለሙሉ ችግር መፍጠር ፅንሱ አለማደግ፣ የፅንሱ መቋረጥ አለበለዚያም ምንም ችግር አለመፍጠር ነዉ።

-ጤነኛ ፅንስ ሆኖ መቀጠል ሊያጋጥም ይችላል(all or none effects )

2-በእርግዝና ወቅት ለመድሀኒት መዉሰድ ከባድ ጊዜ የሚባለዉ የመጨረሻ የወር አበባ ከታየበት ወቅት ከ 31ቀን ጀምሮ እስከ 71ቀን (ከ5ሳምንታት እስከ 10ሳምንት ያለዉ ) ሲሆን ይህም የሆነበት ምከንያት የፅንሱ አብዛኛው የሰዉነት ክፍል የሚሰራበት ወቅት ስለሆነ ነዉ።

በዚህ ወቅት በተለይ በመጀመሪያዎቹ (ከ5 ሳምንት ጀምሮ)ባሉት ወቅቶች የልብ የአእምሮና ህብለሠረሰር የሚሰሩበት ወቅት ሲሆን የተከለከሉ መድሀኒቶች ከተወሰዱ በነዚህ የፅንሱ ክፍሎች ላይ ችግር ሲፈጥሩ ወደመጨረሻዎቹ (9-10ሳምንታት)የእርግዝና ወቅት ከተወሰዱ የአፍ ዉስጥ የላንቃ ክፍት በጆሮ ላይ የአፈጣጠር ችግሮች...ይፈጥራሉ።

በእርግዝና ወቅት የተከለከሉ መድሀኒቶች (ከብዙ በጥቂት....)

1-ለሚጥልበሽታ የሚወሰዱ መድሀኒቶች(aniepileptics drug)

በዛ ያሉ መድሀኒቶች ቢኖሩም ቫልፖሪክ አሲድ (valporic acid ) እና ካርባማዜፒን (carbamazipine)የተባሉት መድሀኒቶች በፅንሱ ላይ የልብ ችግር፣ የላንቃ መሰንጠቅ፣ የህብለሰረሰር ችግር ተጨማሪ የጣት ቁጥርና ሌሎችንም ችግሮች ያመጣሉ።

በአገራችን በብዛት ከሚወሰዱት መድሀኒቶች መካከልም ፊንቶይን(phenytoin) በእናትየዉ ዉስጥ ያለዉን ፎሌት (folate )ስለሚቀንሰዉ ከፎሌት ማነስ ጋር የሚፈጠሩ የተለያዩ የአእምሮ እድገትን የሚገቱ ችግሮችን ያመጣሉ።

2-ለደም መርጋት የሚወሰዱ መድሀኒቶች -anticoagulants

በተለይ ዋርፋሪን የተባለዉ መድሀኒት በተለያየ የእድገት ደረጃ ላይ በዛ ያሉ ችግሮችን ይፈጥራል። ከነዚህም ዉስጥ የአፍንጫ አጥንት ማነስ የአይን የማየት ችግሮችን (bilateral optic atropy) የአእምሮ ዝግመትንና ሌሎች የአፈጣጠር ችግሮችን ያመጣል

3-ለስነእምሮ ችግር የሚወሰዱ
መድሀኒቶች-antipsychotic and antidepressants drugs

ሊትየም (lithium) ለስነአእምሮ ችግር ከሚወሰድ መድሀኒት አንዱ ሲሆን በፅንስ ላይ የተለያዩ ችግሮችን በማምጣት ይታወቃል። ከነዚህም ዉስጥ የልብና የደምስር ችግሮችን በፅንስ ላይ የእንሽር ዉሃ መብዛት....የመሳሰሉ ችግሮችን የመጣል።

ለድባቴ ከሚወሰዱ መድሀኒቶች ኢሜፕራሚን (imipramine)የተባለዉም በተለይ በመጀመሪያዉ የፅንስ የማደግ ወቅት ጊዜ ከተወሰደ የተለያዩ ችግሮችን ያመጣል።

4-ለታይሮይድ ችግር የሚወሰዱ መድሀኒቶች-antithyroid

ፕሮፒልታዮራስል እና ሜታሚዞል (ptropylthiouracil and methimazol) ለታይሮይድ ሆርሞን መብዛት የሚታዘዙ ሲሆን በፅንሱ ላይ እንቅርት ሊያመጡ ይችላሉ

5-ለደምግፉት የሚወሰዱ መድሀኒቶች-antihypertensive drugs

በተለይ enlapril captopril and valsartan የተባሉት መድሀኒቶች የፅንስ የኩላሊት ችግር በማህፀን ዉስጥ የመቀንጨር የዉሃ ሽንት የመቀነስ በዚህም የተነሳ በእግርና በእጅ የአፈጣጠር ችግሮችን ያመጣሉ።

ከላይ የተጠቀሱት ከብዙ በጥቂት ሲሆኑ አንዲት እርጉዝ ማንኛዉንም መድሀኒት ከመዉሰዷ በፊት በሃኪም ብቻ የታዘዘላትን መድሀነት እንድትወስድ ይመከራል።

ዶ/ር ዘለቀ ከበደ (ፅንስና የማህፀን ሀኪምና የህብረተሠብ ጤና አጠባበቅ ባለሙያ)
12.8K viewsDr.Fasil, 12:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 10:25:08 #MMR #ክትባት #ኦቲዝም ያመጣል ወይስ አያመጣም ሙሉ ማብራሪያውን youtube ቻናላችን ላይ ያገኙታል::





#ብሩህkids - youtube ቻናልችን አዳዲስ መረጃዎችን ዘውትር ማክሰኞ ሐሙስ እና ቅዳሜ 7:30 ላይ እንቀርባለን #subscribe ያድርጉ

ለሕክምና የቀጠሮ ስልክ : 0984650912 ወይም 0939602927
13.2K viewsDr.Fasil, edited  07:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-19 15:05:27 #የጨቅላ ህፃናት #ቢጫነት ካልታከም የሚያመጣቸው የነርቭ ጉዳቶች



12.6K viewsDr.Fasil, 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ