Get Mystery Box with random crypto!

ርግብ፡- የመንፈስ ቅዱስ (ማቴ 3፥16) ፤ የእመቤታችን (ዘፍ 8፥8-11) ምሳሌ ሆና በመጽሐ | 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤

ርግብ፡-

የመንፈስ ቅዱስ (ማቴ 3፥16) ፤

የእመቤታችን (ዘፍ 8፥8-11) ምሳሌ ሆና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተጽፋ እናገኛለን፡፡

ርግብ በአንድ ባል ጸንታ የምትኖር ባሏ የሞተ እንደሆነም ምላሷን ሰንጥቃ በብቸኝነት ትኖራለች፡፡

ሌላ ወንድ የመጣባት እንደሆነ የተሰነጠቀ ምላሷን በማሳየት ትመልሰዋለች፡፡

በርግቦች ዘንድ ድጋሜ ሌላ ወንድ ማግባት ነውር ነው፡፡

ትንሣኤ ሙታን ያለን እኛስ? አስቡት እንኳን የትዳር አጋራችን ሞቶብን ቀርቶ በሕይወት እያሉ በላያቸው ላይ የምንነግድባቸው ቀላል ነን እንዴ?

ርግብን ማስተዋል ከቻልን በሥጋና ደሙ ጋብቻችንን መሥርተን በአንድ ጸንተን በመተሳሰብ፣ በመረዳዳትና በመፈቃቀር የምንኖር እንሆናለን፡፡

ምናልባት በሞት የምንለያይ ከሆነና ብቻን ለመኖር አስቸጋሪ ሆኖ ከተገኘ በድጋሜ በሥጋና ደሙ ማግባት ይቻላል፡፡

ይህ ሥርዓት የሚፈጸመው ለምዕመናን ሦስት ጊዜ ለካህን ሁለት ጊዜ (ክሕነቱ ፈርሶ) ከዚህ የዘለለ ጋብቻ ግን ከዝሙት ይቆጠራል፡፡

ስለዚህ ከርግብ በመማር ለትዳራችን ታማኝ በመሆን እግዚአብሔርን በመፍራት ልንኖር ይገባናል፡፡