Get Mystery Box with random crypto!

'ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡ ም | 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤

"ወዳጄ ሆይ! ክርስቲያን ነህን? እንኪያስ በፍጹም ወንድምህን አትናቀው፡፡ እኅትህን አትናቃት፡፡ ምንም ይኹን ምን ሰውን አትናቅ፡፡ ይህ የምትንቀው ወንድም በተለይ ክርስቲያን ከኾነ ክርስቶስን እየሰደብከው እንደኾነ አስተውል። እንዴት? ያልከኝ እንደኾነ ይህ የምትንቀው ወንድምህ የክርስቶስ ሕዋስ (ብልት) ኾኗል፡፡ የክርስቶስ ሕዋስ ከኾነ ደግሞ እርሱን ናቅኸው ማለት ክርስቶስን ናቅኸው ማለት ነውና ወንድምህን የምትንቅ ከኾነ በጲላጦስ አደባባይ ጌታን ከገረፉት፣ ዕራቁቱን ከሰቀሉት፣ሐሞትን ቀላቅለው ካጠጡት፣ በፊቱ ላይ ከተፉበት ሰዎች በምንም አትተናነስም፡፡ ስለዚህ ወንድምህን እኅትህን ከመናቅ ተጠንቀቅ፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ "ሰማዕትነት አያምልጣችሁ"

ቀናችንን የፍቅር የመዋደድ እናድርገው! መልካም ለሊት ይሁንላችሁ!

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh