Get Mystery Box with random crypto!

+ የጴጥሮስ ጥላ + አንድ አባት በተመስጦ ሆኖ እየጸለየ ነው:: ድንገት ሌላ አባት መጣና በቁጣ | ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile

+ የጴጥሮስ ጥላ +

አንድ አባት በተመስጦ ሆኖ እየጸለየ ነው:: ድንገት ሌላ አባት መጣና በቁጣ ጸሎቱን አስቆመው::
"አንተ ደፋር እንዴት ወደ ፀሐይ መውጫ (ምሥራቅ) ሳትዞር ትጸልያለህ?" አለው
ያ አባት መለሰ
"አንተ ፀሐይህን ፈልግ:: የኔ ፀሐይ ክርስቶስ መውጫ መግቢያ የለውም"::

በእውነትም ክርስቶስ በነቢዩ ሚልክያስ እንደተነገረለት ለሚፈሩት የሚወጣ እውነተኛ ፀሐይ ነው:: ወደ ፀሐይ ዞረን ስንጸልይም አባ ጊዮርጊስ እንዳለው ወደ ፀሐይ ሳይሆን ፀሐይን ወደሚያወጣው እንጸልያለን:: (አኮ ዘንጼሊ በቅድመ ፀሐይ አላ ለዘያሠርቆ ለፀሐይ")

ክርስቶስ ፀሐይ ነው:: አናት የሚበሳ ኃይል የሚያደክም ለሕመም የሚዳርግ ሳይሆን ኃይል ፈውስ የሚሠጥ ፀሐይ ነው::

@diyakonhenokhaile
ቅዱስ ጴጥሮስ በሐዋርያት ሥራ እንደተጻፈልን ሕሙማንን በጥላው ይፈውስ ነበር:: በዚህ ምክንያት በሽተኞችን በሚያልፍበት መንገድ አሰልፈው ጥላውን ብቻ እንዲያሳርፍ ያደርጉ ነበር::
የሰው ጥላ ጥሩ አይደለም ለበሽታ ይዳርጋል በሚል ማኅበረሰብ ውስጥ ሆነን ይህን ስንሰማ ምን እንል ይሆን? የጴጥሮስ ጥላ ግን ይፈውስ ነበር::

የጴጥሮስ ጥላ ምን የተለየ ነገር አለው? ምንም የለውም:: እንዲያውም በአሣ አጥማጅነቱ ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር በቀን ዓሣ ሲያጠምዱ ጥላቸው በውኃው ላይ አርፎ አሣ እንዳያሸሽባቸው በሌሊት ማጥመድ ይመርጡ ነበር:: አሁን ግን ዓሣ የሚያሸሸው የጴጥሮስ ጥላ መድኃኒት ሆኖ ከዓሣ አልፎ ምእመናን ማጥመድ ጀመረ::

@diyakonhenokhaile
የጴጥሮስ ጥላ ከቀድሞው ጥላው በምንም አይለይም::
ያንን ሁሉ በሽተኛ መፈወስ የቻለው ጥላው ተቀይሮ ሳይሆን ያረፈበት ፀሐይ ተቀይሮ ነው:: ፈዋሹ ጥላ የተፈጠረው እውነተኛው ፀሐይ ክርስቶስ በጴጥሮስ ላይ ስላረፈ ነው:: እውነተኛው ፀሐይ በእኛ ላይ ሲያርፍ እኛ ተፈውሰን ሌላ እንፈውሳለን:: የእርሱ ብርሃንና ሙቀት ሲያርፍብህ የኃጢአት ቆፈን ቀስ በቀስ ይለቅህና ትፍታታለህ:: ከዚያም ሐሙስ ማታ ብርድ ፈርተህ እሳት ለመሞቅ ሦስቴ የካድከውን ፀሐይ ስትሞቀው ሦስት ሺህ ሰው ፊት ትመሰክርለታለህ:: እሱን ሞቀህ በጥላህ ደግሞ ለሌሎች ትተርፋለህ::
ክርስቶስ እንዴት ያለ ፀሐይ ነው? ፀሐይን ያጨለመ ፀሐይ! ፈረቃ የማያውቅ ፀሐይ! ፀሐይ ራስዋ የምትሞቀው ፀሐይ እርሱ ክርስቶስ ነው::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#Share
@diyakonhenokhaile
#Share
@diyakonhenokhaile