Get Mystery Box with random crypto!

ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile

የቴሌግራም ቻናል አርማ diyakonhenokhaile — ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile
የቴሌግራም ቻናል አርማ diyakonhenokhaile — ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile
የሰርጥ አድራሻ: @diyakonhenokhaile
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.31K
የሰርጥ መግለጫ

Henok Haile
Author
https://l.instagram.com/?u=https://youtu.be/5R-pjvDeX4g&e=ATO0XVudOWg66a06guzC75IANTb2l2egLzkeGbr9wETcTg3FHuOHdrmPR4b2eOQb-H_knzwrLS0r1E7ACWyHbw&s=1

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-01-12 15:18:32 https://youtube.com/channel/UCDzpObi4CUKjnLIgmdqpIEg
15.6K views𝖒𝖎𝖈𝖐𝖞, 12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 15:13:27 Share!! Share!! Share!!
Share!!
Share!!



15.1K views𝖒𝖎𝖈𝖐𝖞, edited  12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 14:55:19 ይህንን በማድረግ ፈንታ ቢያንስ ከዋዜማው ጀምሮ እንኳን ቤተ ክርስቲያን አደባባዩን መጠቀም መቻል አለባት፡፡ ዓለምን ያስደመሙት የኢትዮጵያ መስቀል ዓይነቶች ለሀገር ውስጥና ለውጪ ጎብኚዎች በዐውደ ርእይ የሚታዩበትና ለሽያጭ የሚቀርቡበት ፣ የኢትዮጵያ የመስቀል ዐውደ ጥናት የሚካሔድበትና በዘርፉ ላይ ጥናት የሠሩ ባለሙያዎች ጥናት የሚያቀርቡበት ፣ የቤተ ክርስቲያንዋ የያሬዳዊ ዜማ ሀብታት በአደባባይ የሚታዩበት ፣ በዕለቱ ተካልበው የሚያልፉት የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በዋዜማው ምሽት አደባባዩን ሞልተው ዋዜማውን በዝማሬ የሚያሳልፉበት ፣ በዕለቱ የሚቀርበውም ትርዒት የተመጥነና ለሕዝቡ ትደራሽ እንዲሆን በባለሙያዎች የታገዘ ቢሆን ፣ ቤተ ክርስቲያንዋ በበዓሉ ላይ ለሚገኘው ሕዝብ አንዳንድ የገቢ ማሰባሰቢያ ሥራዎችን የምትሠራበት ሁኔታ ቢመቻች መስቀል አደባባይ እውነትም መስቀል አደባባይ መሆን ይችላል፡፡

3. ግንቦት ልደታ
በመስቀል አደባባይ ሊከናወን የሚገባውና ከይዘቱ አንጻር ተገቢ የሆነው ሌላው የአደባባይ በዓል የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት የሆነው የግንቦት ልደታ በዓል ነው፡፡ ግንቦት ልደታ በቤተ ክርስቲያንዋ ከቤት ውጪ በምሽት በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ይህንን በዓል በውጪ እንዲከበር ያደረገው ድንግል ማርያም የተወለደችው በቤት ውስጥ ሳይሆን በተራራ ላይ የነበረ መሆኑን ለማስታወስ ነው፡፡ ይህንን በማስመልከት ኦርቶዶክሳዊያን ምእመናን ከቤታቸው ውጪ ሆነው በዓሉን ያከብራሉ፡፡

ከዓመታት በፊት በግንቦት ልደታ በዓል ታሪክ ዙሪያ አነስተኛ ጥናታዊ ጽሑፍ በማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ትእዛዝ በሠራሁና ባቀረብሁበት ወቅት ለመገንዘብ እንደቻልሁት ግንቦት ልደታ በኢትዮጵያውያን ዘንድ እንደየ ብሔር ብሔረሰቡ የተለያየ ቅርፅ ያለው ቢሆንም ትልቅ ቦታ ሊሠጠው የሚችልና ለቱሪስት መስሕብ ለመሆን የሚችል እምቅ እሴት የያዘ ሀገራዊ ቅርስ ነው፡፡
ይህ እጅግ ድንቅ የሆነ በዓል በመስቀል አደባባይ የመከበሩን ተገቢነት ድንግል ማርያምን ከመስቀል ጋር በሚያስተሳስሩ ጸሎቶችዋና ዜማዎችዋ የምትታወቀው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የሚደግፈው ነው፡፡ በብዙ ሀገራት በብሔራዊ በዓል ደረጃ የሚከበረው ይህ በዓል በቤተ ክርስቲያን ደረጃም ቢሆን በሚመጥነው ክብር ቢከበር በቤተ ክርስቲያኒቱ ተልእኮና በሀገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ የሚፈጥረው በጎ ተጽዕኖ ቀላል አይደለም፡፡

4. የጥምቀተ ባሕር ሜዳዎች

ቤተ ክርስቲያናችን ጥምቀተ ባሕር ላይ ሰፋፊ ሥራዎችን ለመሥራት ዕቅድ እንደያዘችና ሥራ እንደ ጀመረች ብፁዕ አቡነ ያሬድ ይፋ ያደረጉት የጃን ሜዳ ፕሮጀክትና ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በመግለጫቸው የዳሰሱአቸው ርእሰ ጉዳዮች ምስክሮች ናቸው:: ቤተ ክርስቲያናችን እነዚህን ቅዳሴ የሚደረግባቸው ክቡራት ሥፍራዎች ደረጃቸውን የጠበቁ ፓርኮች ሆነው መገንባት: የሕፃናት ማጫወቻዎችና ስፖርት ማዘውተሪያዎች : ከሱስ ማገገሚያ ማእከላት ሊሆኑም ይችላሉ::

በተጨማሪም በዓላት በደረሱ ቁጥር ልዩ ልዩ ባዛሮችና መንፈሳዊ ዐውደ ርእዮች ከጉባኤያት ጋር ቢካሔዱባቸው በዓልን በስካርና ጭፈራ ከማክበር ብዙኃንን ማዳን ይቻላል:: የግንቦት ልደታ በዓልም ከመስቀል አደባባይ በተጨማሪ በጥምቀተ ባሕር የሚካሔድ መሆን ሲችል ደብረ ታቦርና የእመቤታችን ትንሣኤ (አሸንዳም) እንዲሁ ጥምቀተ ባሕር ላይ መከበር ይችላል:: እጃችን ላይ ያሉ በጎ ዕድሎችን በአግባቡ ከተጠቀምን እጃችን ላይ የሌሉትንም እንጨምራለን::

"ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች" ዮሐ. 9:4

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥር 4 2014 ዓ.ም.

"ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ!!
14.8K views𝖒𝖎𝖈𝖐𝖞, 11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 14:54:52 + መስቀል አደባባይና ቤተ ክርስቲያን +

ከሁለት ወራት በፊት "የጥምቀተ ባሕር ቦታዎችንና የአደባባይ በዓላትን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ልትጠቀምባቸው ትችላለች?" በሚል ርእስ የተለያዩ ባለሙያዎችን አስተያየት ያካተተ አንድ ጥናታዊ ጽሑፍ በማዘጋጀት ላይ ነበርሁ፡ ጽሑፉ እንደ ተጠናቀቀ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በዝርዝር ውይይት አደረግን፡፡ ጉዳዩን ለብፁዓን አበው ለማቅረብና ወደ ይፋ ውይይት ለመግባትም ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ነበርን፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ነገሮችን የሚገለባብጥና ስሜት የሚነካ የሰሞኑ አሳዛኝ ክስተት ተፈጠረ::

በተለይ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን በምእመናን ላይ የተደረገው አሳዛኝ ሁኔታ ፣ ከዚያ በፊትና በኋላ ሲደረጉ የነበሩት ልብ የሚያቆስሉ ስድድቦች እጅግ የሚያሳዝኑ ነበሩ:: አሁን በዚህ ዘመን ችግር ያነሰን ይመስል ሌላ ችግር መጨመር ነበረብን? ወይ የሚያሰኝ ሆነ፡፡

በስሜት የምንናገራቸውና የምናደርጋቸው ነገሮች ቁጣን ከማብረድና ሥራ የሠራን ያህል እርካታ እንዲሰማን ከማድረግ ያለፈ ውጤት እንደማያመጡ የታወቀ ነው:: በሌላው ተመልካች ዘንድም ‘ልማዳቸውን ነው ይጩኹ’ የሚል ንቀት ከማትረፍ ውጪ ምንም አያመጣም፡፡ ስለዚህ በየአቅጣጫው መፍትሔ የምንለውን ብንጠቁምና ቤተ ክርስቲያናችንን ብናግዝ የተሻለ ስለሚሆን እኔም በምክረ ሃሳቡ ላይ የተካተቱ አንዳንድ ሃሳቦችን ጨምሬ የተሻለ ነው የምለውን መፍትሔ ለመጻፍ ግድ ሆነብኝ፡፡

1. የመስቀል አደባባይ ሕጋዊ ይዞታ ጉዳይ

ቤተ ክርስቲያን ካሏት ነገሮች በተጨማሪ ብዙ ነገሮችን ከሀገሪቱ ልትጠይቅ የሚገባት ብዙ ሚሊዮኖችን የያዘች ሕጋዊ ማንነት ያላት ተቋም ናት፡፡ በዚህ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን በአግባቡ ከተጠቀመች አንዱን የመስቀል አደባባይ ብቻ ሳይሆን ብዙ መስቀል አደባባዮችን ገንብታ አሁን የመወያያ ርእስ የሆነውን የመስቀል አደባባይ የትኩረት ማእከልነቱን እስከ ማሳጣት ድረስ አቅም ያላት ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ከከተማው ስፋትና ከምእመናን ብዛት አንጻር በየክፍለ ከተማው አንድ አንድ መስቀል አደባባዮች እንዲኖሩ ማድረግ የማትችልበትም ምክንያት የለም፡፡

ሆኖም አሁን እንኳን ሌላ ሊጨመር ያለውም የባለቤትነት ጥያቄው አደጋ ላይ ነው፡፡ አደባባዩ የብዙኃን ዓይን ያረፈበትም በከተማው ቦታ ጠፍቶ ሳይሆን ሥፍራው በኦርቶዶክሳውያን ልብ ውስጥ ያለውን የምልክትነት ሥፍራ በመረዳት መሆኑ ግልፅ ነው:: "ሜዳው ሰፊ ነው : ፈረሶቹ ሁለት ናቸው ግን አሳልፈኝ አሳልፈኝ ይባባላሉ" እንደሚባለው ብሂል ነው::

ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ላይ የምታቀርበው በቂ የሰነድ ማስረጃና ታሪካዊ እውነት እንዳላት ግልጽ ነው፡፡ ‘እውነት ነፃ ያወጣችኋል’ የሚል አምላክን እስካመነች ድረስም የተሻለውና ዋጋ ቢከፈልለትም የማያስቆጨው አካሔድ ይኼው ነው፡፡

ቤተ ክርስቲያን መብትዋን የምታስከብረውም ታሪካዊ ሰነዶችን ፎቶ እያነሱ በማኅበራዊ ድረገጽ በመለጠፍ ወይንም ጊዜያዊ ትኩሳትን ተንፈስ በሚያደርጉ መግለጫዎች ብቻ ሳይሆን የሕግ ሰዎችን ፣ የመሬት ሰነዶች ላይ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ፣ የዘርፉ ኤክስፐርቶች የሆኑ ልጆችዋን ያቀፈ አካልን እንዲወክላት በማድረግ ጉዳዩን በተገቢው ትኩረት እንዲፈታ በማድረግ ነው፡፡ ይህንን በማድረግ ችግሮችን ሌላ ተጨማሪ ችግር ሳይፈጥሩ መፍታት ይቻላል፡፡ ከዚያ ውጪ ግን ችግሩን ብቻ ማውሳት ምእመናን የተጠቂነት ስሜት ውስጥ እንዲገቡ ከማድረኛ ቤተ ክርስቲያንዋንም ክብር ከማሳጣት ያለፈ ጥቅም የለውም፡፡

2. መስቀል አደባባይን ‘የመስቀል አደባባይ’ ማድረግ

እንደሚታወቀው መስቀል የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ በዓልዋ መሆኑ የታመነ ነው፡፡ ሆኖም የመስቀል በዓል ከመንፈሳዊ በዓልነቱ ይልቅ ፌስቲቫላዊ ቅርፁ በጣም የሚያይል አከባበር ያለው በዓል ነው፡፡

እንደሚታወቀው በበዓሉ ዕለት ቤተ ክርስቲያን ከምትጠቀምበት ሰዓት ይልቅ የተለያዩ የፖለቲካ ሰዎችና ተጋባዥ እንግዶች ርዝመቱ የማይገመት ንግግር የሚያደርጉበት ሰዓት ይበዛል፡፡ የቤተ ክርስቲያንዋም አካላትም ከመንፈሳዊ ስብከት ይልቅ መንግሥትንና ተጋባዥ ዲፕሎማቶችን ማእከል ያደረገ ‘የተከበሩ አቶ እገሌ’ የሚበዛው ንግግር ሲያደርጉበት ይስተዋላል፡፡ በዓለ መስቀልም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ለመዳሰስ ሰበብ ሆኖ ያገለግላል እንጂ ወደ አደባባዩ መጥቶ ስለ ጌታችን መስቀል ምንም ዓይነት ነገር ሰምቶ የሚሔድ ምእመን የለም፡፡ በደርግ ዘመን እንኳን ከብዙ ችግር ጋር እነ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሰበኩት ‘ዮም መስቀል ተሰብሐ’ የሚል ስብከት ተጠቃሽ ነበር፡፡ ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ ግን መስቀል አደባባይ ላይ የሚተላለፉ መልእክቶች እንዴት በዓሉን ከወቅታዊ ትኩሳት ጋር እናስተሳስረው በሚለው ላይ ብቻ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ከዚያ ውጪ መስቀል አደባባይ በአግባቡ ምሕላ እንኳን ደርሶበት አያውቅም፡፡ ሐቁን ለመናገር እንደ መስቀል በዓል አከባበርም መስቀሉን የሚቀብር ተራራ የለም፡፡

የምእመናን በዓል እንደመሆኑ ከውጪ የሚመጡ እንግዶች ሕዝቡ በዓሉን ሲያከብር መመልከት ሲገባቸው በመስቀል አደባባይ ግን ሕዝቡ የውጪ እንግዶች በዓሉን ሲያከብሩ ከሩቅ ሆኖ ይመለከታል፡፡ ነፋስ የሚያማታውን የስፒከር ድምፅ እየተከተለ ጭብጨባ ሲሰማ ያጨበጭባል፡፡ የአደባባዩ መርሐ ግብር አስተዋዋቂ አሁን እንዲህ እየተከናወነ ነው ሲል እየሰማ ሥፍራው ላይ ያለው ሕዝብ በቤቱ በቴሌቪዥን ከሚመለከተው ሰው ያነሰ መረጃ ኖሮት ተደናብሮ ይመለሳል፡፡ አንዳንዴም ደመራው ቶሎ አልበራ ሲለው በፉጨትና በጭብጨባ ፍጠኑ ይልና ሕዝቡ ራሱ ጧፍ በመለኮስ በዓሉን ያስጀምራል፡፡
አንድ ስብከት ሳይሰበክ ፣ አንድ መዝሙር በወጉ ሳይሰማ ሊቃውንቱ ፣ መዘምራኑ የኦሎምፒክ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት እንደሚታዩት አትሌቶች ምንም ሰዓት ሳያገኙ በጥድፊያ አልፈው እንዲያልፉ ይደረጋል፡፡ አብዛኛው የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣትና የማኅበራት መዘምራን መስቀል ሲመጣ እንደ ትልቅ አገልግሎት የሚያዩት ከበዓሉ ዕለት ይልቅ ለበዓሉ ሲዘጋጁ የሚያቀርቡትን ዝማሬና ወደ አደባባዩ እስከሚደርሱ ድረስ በመንገድ ላይ የሚዘምሩትን ዝማሬ ነው፡፡ የልዩ ልዩ ሚዲያ ጋዜጠኞችም መስቀሉን መቅበራቸው የተለመደ ነው፡፡ ‘የዘንድሮን የመስቀል በዓል ካለፈው ዓመት የተለየ የሚያደርገው ግድቡ በተገባደደበት ማግስት ላይ በመሆናችን ሲሆን’ የሚል ዘገባ ያቀርባሉ፡፡

አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶችን ለቃለ መጠይቅ ያቀርቡና ‘መስቀል ከሃይማኖታዊነቱ ባሻገር ለሀገር የሚያበረክታቸው እሴቶች ምን ምን ናቸው?’ ‘የመስቀል በዓል በዩኔስኮ መመዝገቡ ያለው ጠቀሜታ ምንድን ነው?’ የሚሉ በየዓመቱ እንደ ችቦው የማይቀሩ ችክ ምንችክ ያሉ ጥያቄዎችን ያቀርባሉ፡፡ በማግስቱም የመንግሥት ሚዲያዎች ስለ ክትፎ አሠራርና ስለ ቆጮ አዘገጃጀት ቀኑን ሙሉ ሲያብራሩና ዘፈን ሲጋብዙ ይውላሉ፡፡ ታሪኩን የማያውቅ ሰው ንግሥት እሌኒን የጉራጌ ንግሥት ፣ መስቀሉም ከክትፎ ውስጥ ተቆፍሮ የተገኘ ሊመስለው ይችላል፡፡

ብቻ በአጭሩ መስቀልን ሲያስታውስ አንድ ነገር ጨበጥሁ የሚል ሰው ማግኘት እጅግ አስቸጋሪ ነው፡፡ ደመራው የሚለኮስበት ውብ ሰዓት ላይ ብቻ ሕዝቡ በእልልታና በጧፍ እያጀበ ሰውነትን የሚነዝር ዝማሬ ያቀርባል፡፡ አሁን አሁን ቀረ እንጂ ደመራው የወደቀበትን አቅጣጫ እንደ ሀገሪቱ ፖለቲካ ኮምፓስ ቆጥሮ ወዴት ወደቀ ብሎ በጭንቀት የሚጠይቅም ብዙ ሰው አለ፡፡ ከዚያ በኋላ መስቀል አደባባይ ለሰዓታት ብቻ መስቀሉን አክብሮ አገልግሎቱ ያበቃል፡፡
12.7K views𝖒𝖎𝖈𝖐𝖞, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-12 14:54:52
10.0K views𝖒𝖎𝖈𝖐𝖞, 11:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-08 22:56:25
12.9K views𝖒𝖎𝖈𝖐𝖞, 19:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-19 14:38:49 Channel name was changed to «ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ | Henok Haile»
11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 10:36:44 ፍቅር ቊስል ነው

እውነቱ ይህ ነው ፣ ፍቅር የሚለካው በልባችን ላይ በተወው ቊስል ልክ ነው።
እጅግ የምንወዳቸው ሰዎች አሳምመውን ይሆናል።
እኛም እጅግ የሚወዱንን ሰዎች አሳምመን ይሆናል።
ምክንያቱም ፍቅር የሚታየው በታገስነው ቊስል ውስጥ ነው
#Share
@diyakon_henok_haile
ፍቅር የሚታወቀው የተለዋወጥናቸውን ቃላት ሳይሆን በምንታገሠው ቊስል ፣ በተሰማን የውስጥ ሕመም ፣ በከፈልነውን መሥዋዕትነትና በተካፈልነውን ብርሃን ነው።

ከትንሣኤው በኋላ በሐዋርያቱ ፊት የተገለጠው ክርስቶስ እርሱ የሚወዱት ጌታ እንደሆነ ለማስረዳት ያሳያቸው የትንሣኤው ድል ማብሠሪያ መለከት አይደለም ፣ የፍቅሩ ማስረጃ ቊስሉ ነበር።

@diyakon_henok_haile
"ወደ እኔ ኑ ቊስሌን ዳስሱ ፣ እጃችሁንም ስለ እናንተ ፍቀር በቆሰልሁት ቊስል አስገቡ" ነበር ያላቸው።
አታስታውሱኝም? አላወቃችሁኝም? እስከ ሞት ድረስ የወደድኳችሁ እኔ ነኝ። ለፍቅሬ ማረስጃ እንዲሆናችሁ ደግሞ ቊስሌን ተመልከቱ! ነው ያላቸው።
ፍቅር ቊስል ነው።
በእግዚአብሔር መንግሥት ክብርና ምስጋና የምናገኘውም በምድር ሳለን በነበሩ ስኬቶቻችንና ባስገኘናቸው ውጤቶቻችን ሳይሆን በታገሥናቸው መከራዎችና በተሰቃየንባቸው ሕመሞች ልክ ነው።

ለዚህም ነው በአበው መጽሐፍ አንድ ቅዱስ አባት ለረጅም ዓመት በሰውነትዋ ላይ ቆስሎ የምትሰቃይን ሴት ሊጠይቁ ሲሔዱ
"እዩት ቊስሌን አጎንብሰው ቢያዩት አጥንቴ ይታይዎታል" አለቻቸው።
እርሳቸውም ጎንበስ ብለው "ብዙ ዓመት በታገስሽው በቊስልሽ ውስጥ የሚታየኝ አጥንት ሳይሆን ገነት ነው" አሏት።

ጸሐፊ: Fr Haralambos Libyos Papadopoulos
ተርጓሚ: ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
አዲስ አበባ
#Share
@diyakonhenokhaile
15.7K viewsᴍɪᴄᴋʏ, edited  07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 10:36:36
12.2K viewsᴍɪᴄᴋʏ, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-13 10:36:34
11.8K viewsᴍɪᴄᴋʏ, 07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ