Get Mystery Box with random crypto!

ጌታችን በስምዖን ቤት እያለ 300 ዲናር የሚያወጣ ሽቱ ይዛ ለመጣችውና ጠርሙሱን ሰብራ ላፈሰሰችው | ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile

ጌታችን በስምዖን ቤት እያለ 300 ዲናር የሚያወጣ ሽቱ ይዛ ለመጣችውና ጠርሙሱን ሰብራ ላፈሰሰችው ባለ ሽቱዋ ማርያም ሲመሰክር

"መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱን ለምን ታደክሙአታላችሁ? ...እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ወንጌል በዓለም ሁሉ በማናቸውም ስፍራ በሚሰበክበት እርስዋ ያደረገችው ደግሞ ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን ይነገራል" ብሎ ነበር:: (ማቴ 26:10-11)

ለክርስቶስ በአንዲት ምሽት መልካም ሥራ የሠራችን ሴት ሊንቁ የሞከሩትን ሰዎች ክርስቶስ ከገሠፃቸው ሕይወትዋን ሙሉ በመልካም ሥራ የደከመችዋን ቅድስት አርሴማን [St. Hripsime] የማያከብር ምንኛ ተግሣፅ ይገባው ይሆን?

ባለ ሽቱዋ ማርያም በዝሙት ስትሠቃይ ኖራ በመጨረሻ ዕንባዋን ከሽቱ ቀላቅላ ከጌታ እግር ሥር የወደቀች ናት:: ቅድስት አርሴማ ግን በድንግልና ለመኖር ብላ በነገሥታትና ገዢዎች ብዙ መከራን የተቀበለች ውድ ሽቱን ንቃ በክርስቶስ በፍቅሩ መዓዛ ያጌጠች ነበረች::
ክርስቶስ ባለ ሽቱዋ ማርያም ያደረገችው ለእርስዋ መታሰቢያ እንዲሆን በዓለም ሁሉ ይነገራል አለ::
ባለ ሽቱዋ ማርያም ስለ ክርስቶስ ፍቅር የሰበረችው ጠርሙስ ነው ያፈሰሰችው ሽቱ ነው::
ቅድስት አርሴማ ግን የሰበረችው አንገትዋን ነው:: ያፈሰሰችው ደሟን ነው:: ስለዚህ በዓለም ሁሉ ስለ እርስዋ ይነገራል:: አርሴማ አርሴማ አርሴማ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#Share
@diyakon_henok_haile

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ጸልዩ! በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
#Share
@diyakonhenokhaile