Get Mystery Box with random crypto!

+ ያደረግሽው ምንድን ነው? + አዳም ዕፀ በለስን በበላና ክብሩን ባጣ ጊዜ እግዚአብሔር ሲጠይቀው | ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ Henok Haile

+ ያደረግሽው ምንድን ነው? +

አዳም ዕፀ በለስን በበላና ክብሩን ባጣ ጊዜ እግዚአብሔር ሲጠይቀው እንዲህ አለ :- ከእኔ ጋር እንድትሆን የሠጠኸኝ ሴት ከዛፉ ሠጠችኝና በላሁ::

ከዚያ በኁዋላ ግን እግዚአብሔር ለሔዋን :- ለምን ዛፉን ብላ ብለሽ ሠጠሽው? አላላትም:: የተናገረ አንድ ዐረፍተ ነገር ነው - "ያደረግሽው ምንድነው" ብቻ አላት::

@diyakon_henok_haile
እርሱ በሰዎች አስተያየት አይፈርድም:: ሌላው ስለ አንተ የሚለውን ትቶ አንተን ለብቻህ ይጠይቅሃል:: የሰዎችን ግምገማ አይሰማም:: እንደ ሃናንያ "ኸረ ጌታ ሆይ ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ነበረኮ" ቢሉትም ቸል ብሎ ምርጥ ዕቃው ያደርግሃል:: በድንጋይ ልትወገር ይገባታል ሲሉት እየሰማ ክሱን ትቶ ከሳሾችዋን ሊከስስ መሬት ላይ ይጽፋል:: ዐሥርቱ ትእዛዛትን በጻፉ ጣቶቹ ዘማዊትዋን ሴት ነጻ ሊያወጣ አፈር ይጭራል::

#Share
@diyakon_henok_haile

ሰው ጨካኝ ፈራጅ እንደሆነ ያውቃልና በአዳም አስተያየት ሔዋን ላይ አይፈርድም:: ምንም ብታጠፋም "ያደረግሽው ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቃት::

እግዚአብሔር ዛሬም ነፍሳችንን ይጠይቃታል::

ያደረግሽው ምንድን ነው? የአዳምን ክስ ሰምቻለሁ! ሰዎች ስለ አንቺ የሚሉትን አዳምጫለሁ:: አንቺ ግን ንገሪኝ:: ግራውን ሰምቼ አልፈርድም:: ምናልባት ቀኙን ብሰማ ይሻላል የሚል ርኅሩኅ አምላክ ነው::
እኛ የምንፈርድባቸው ሰዎች ሁሉ ቢጠየቁ የሚናገሩት የየራሳቸው የታሪክ ማዕዘን (side of the story) አላቸው::
ስለዚህ እግዚአብሔር አዳምን ሰምቶ አልፈረደም ሔዋንን ጠርቶ ጠየቃት
"ያደረግሽው ምንድን ነው?"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#Share
@diyakon_henok_haile