Get Mystery Box with random crypto!

የውሙ ዓረፋ የዙልሒጃህ ዘጠነኛው ቀን የውሙ ዓረፋህ(የዓረፋው ዕለት) በመባል ይታወቃል።በዚህ ዕለ | ድንህ ህይወትህ ነው

የውሙ ዓረፋ

የዙልሒጃህ ዘጠነኛው ቀን የውሙ ዓረፋህ(የዓረፋው ዕለት) በመባል ይታወቃል።በዚህ ዕለት ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሐጅና ዑምራህ የመጡ ሰዎች በዓረፋህ ተራራህ ተሰብስበው አላህን ሲለምኑ የሚውሉበት ዕለት ሲሆን፤ ሐጅ ማድረግ ያልቻሉና ለሐጅ ያልሄዱ አማኝ ሙስሊሞች ይህን ቀን በመፆምና በኢባዳህ ያሳልፉታል። ዓረፋህ ከሌሎች ቀናቶች የተለየ ፈድል(ደረጃ) ከአላህ ዘንድ አለው።ከዚህም ውስጥ አሏህ ሱብሃነሁ ወታዓላህ ሁልጊዜም በየ ዕለቱ የሌሊቱ አንድ ሶስተኛው ሲቀር ወደ ቅርቧ ሰማይ በመውረድ ማነው ምህረትን የሚጠይቅ የምምረው፣ማነው የሚለምነኝ የምሰጠው እያለ እንደሚናገር መልዕክተኛው ነግረውናል።የዓረፋው ዕለት ግን አሏህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ለክብሩ በሚገባው መልኩ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ወደ ቅርቢቷ ሰማይ የሚወርድበት ዕለት ነው ።በዚህ ቀን ዱዓእ በማድረግ፣ፆምን በመፆም፣ተውበትና እስቲግፋር በማብዛት፣ዚክርን በማለት በቻልንው ቢዚ ልንሆን ይገባል።

የዓረፋውን ፆም መጾም የሁለት ዓመት ወንጀልን ያሳብሳል(ያስምራል)።እናም ላልሰሙት በማሰማት እንበርታታ።
Ibnu Seid
t.me/dinhhiwothnew