Get Mystery Box with random crypto!

አበው ሚዲያ

የቴሌግራም ቻናል አርማ dhhftyyg — አበው ሚዲያ
የቴሌግራም ቻናል አርማ dhhftyyg — አበው ሚዲያ
የሰርጥ አድራሻ: @dhhftyyg
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 8.80K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-01-13 17:59:19 ጾሙስ አበቃ.....?
(#በአባ_ገብረ_ኪዳን)

ጾሙስ አበቃ የነፍስ ረሃባችን መቼ ያበቃ ይሆን? ነፍሳችን ሥጋውን ደሙን እስከመቼ ነው የምትጾመው? ጾሙስ ተደመደመ። የእኛ በደል መቼ ይሆን የሚቋጨው? ስግብግብነታችን መቼ ነው ዳር የሚደርሰው? በዚህ ጾም መጨረሻ የአብ አንድያ ልጁ ተወልዶ መለያየት ተወገደ ሰውና መላእክት አንድ ሆኑ፤ መቼ ይሆን ጎጠኝነታችን የሚጠፋው? መቼ ይሆን ሰማያዊ ዘመድ የምናበጀው። ጾም ተፈጽሟልና ለሥጋ ሥጋ ተገዛለት። ለዚህ ጾሞ ፋሲካ ለነፍስ ምን ቅመም ተቀመመላት? ምን ንብረት ተመደበላት? ምን ሙክት ተገዛላት? ምን ወይን ተጠመቀላት? ምን ልብስ ተሠራላት? ምን ድግሥ ተደገሠላት? እነማንን ድግሥ ጠራንላት? አጋንንትን ወይስ መላእክትን? ዛሬ ዛሬ የጾም መግቢያና መውጫ ይገርማል። የጾም መግቢያ ሥጋ ይበላል የጾም ፍጻሜ ሥጋ ይበላል። በሥጋ ጀምረን በሥጋ መጨረስን ተያይዘነዋል! ሥጋው በደል ሆኖ አይደለም መጀመሪያችን መፈጸሚያችን የሥጋ ብቻ መሆኑ ግን የነፍስ ያለህ ያሰኛል!

አንዳንድ ሰው የዘንድሮው በዓል ልዩ የሚያደርገው ዓመቱ መሆኑ ይመስለዋል። ልዩ የሚያደርገው ከአምናው በተለየ ነፍስ ያገኘችው ነገር ሲኖር ነው። ለሥጋ ተበድሮ ሳይቀር ይደገሳል። ቢያንስ ድኃ ቢያጣ ያለችውን አጥቦ ለብሶ ከጎረቤት ሥጋ እየሸተተው ይውላል። ነፍሳችንስ ቢያንስ የሚቆርቡትን እያየች የክርስቶስ መዐዛ ቢናፍቃትም ባይሆን ተናዝዘን ታጥበን ብንውል ምን አለ?

የጸሎት ረሀብ መቼ ነው የምንፈስከው? የንጽሕና ረሀብ መቼ ነው የምንገድፈው? መፈሰክ ማለት መሻገር ነው? ዝሙትን የተሻገርን ዕለት ያን ጊዜ ነበር ፋሲካ!

ሱባኤው ደረሠ ቀጠሮው ተፈጸመ ጌታ ተወለደ። የእኛ ቀጠሮ መቼ ነው የሚደርሰው? በዚህን ጊዜ...ን አደርጋለሁ ብቻ! ጸሎቱ ቀጠሮ ጾሙ ቀጠሮ ትጋቱ ቀጠሮ አሥራቱ ቀጠሮ ኑዛዜው ቀጠሮ መታረቁ ቀጠሮ ቁርባኑ ቀጠሮ ሁሉ ቀጠሮ!ማን አለ የእኛስ ቀጠሮ ቢደርስ ምን አለ ጽኑዕ ቀጠሯችን ሳይደርስ እኛ የቀጠርነውን ጽድቅ ብንጀምረው! ምን አለ የእኛም ሱባኤ አብቅቶ የእግዚአብሔርና የቅዱሳን ልጆች ሆነን በምግር ብንወለድ!

የጾመ ነቢያት ፍጻሜ ጌታ ተወለደ። እኛም ከንስሐ ማኅፀን እንድንወለድ ይርዳን። ከጾሙ መጨረሻ ክርስቶስ ከእነርሱ በሥጋ መጣ። ከጾማችን ፍጻሜ ጌታ በሰውነቴችን እንዲያድር ንስሐ ብንገባ ይህ ነው የጾም ፍጻሜ። ጌታ ሲወለድ አሮጌው ዘመን አበቃ። ሐዲስ ሕይወት፡ተወጠነ። እኛም ኃጢአታችን በንስሐ አልቆ አዲስ ከዘንድሮው ልደት ጀምሮ አዲስ ሕይወት ለመኖር ያብቃን። ኃጢአታችን ይለቅልን!
1.8K views14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ