Get Mystery Box with random crypto!

.የታፈነ እውነት... ከቃል አፋ ተፋትቶ፣በዝምታ ምርኳዝ፣ ለነግህ ተቋጥሮ፣በስሌት የሚጓዝ፣ በአንደ | ♣ .ከግጥም አለም በደሱ..🌹🌹🌹

.የታፈነ እውነት...
ከቃል አፋ ተፋትቶ፣በዝምታ ምርኳዝ፣
ለነግህ ተቋጥሮ፣በስሌት የሚጓዝ፣
በአንደበት ተቀብሮ፣ደጃዝማች የራቀው፣
በደሳሳ ጎጆ፣
በነተበ ገላ፣
ህያው ሁኖ ሊኖር፣ከታይታ መንፍቆ፣
ክብር ላለማጉደፍ፣ከጢሻ ያልወጣ እራሱን ደብቆ፣
አለ ድንቅ እውነት፣
በበሳል አይምሮ፣ተንጋሎ ያደረ፣
ከሽንገላ ጩኸት፣
በአርምሞ ፀበል፣አለሙን ያሰረ፣
ለእርግማን ሲጠሩት፣ጎልቶ ያልከበረ፣
ከነ ቡትት ጓዙ፣ከውሸት ተጣልቶ ጮራን የሚናፍቅ፣
አለም ስትጨልም፦
ይወጣል በክብር፣
ከነ አስፈሪ ግርማው፣
አድማሱን በሞላ ከውሸት ሊያስለቅቅ።
ተፃፈ ደሱ ለተጨማሪ መሳጭ ግጥሞችና አባባሎች

https://t.me/Desupome/764
https://t.me/Desupome/764