Get Mystery Box with random crypto!

#ለከተማችን_ነዋሪዎች_በሙሉ እያደረኩት ባለው ጥብቅ የፍተሻ ስራ 2 ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር | Dessie City Football Club

#ለከተማችን_ነዋሪዎች_በሙሉ
እያደረኩት ባለው ጥብቅ የፍተሻ ስራ 2 ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር አውያለሁአለ የደሴ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ።

ደሴ-- ነሀሴ 24/2014 አ.ም መምሪው በሀሰት መረጃ አከባቢያቸውን የለቀቁ የህብረተሰብ ክፍሎችንም ወደ ቀያቸው እየመለስኩ ነው ብሏል።
የመምሪያው ዋና ሀላፊ ኮማንደር አሳምነው ሙላት ለፍና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት ተፈናቃይ መስለው ወደ ከተማው ሊገቡ የነበሩ ስረጎ ገቦችን መያዛቸውን ተናግረዎል።

ከተማ አሰተዳደሩ በሽብር ቡድኑ ወዥንብር አከባቢያቸውን ለቀው ወደ ከተማዋ
ገብተው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸው የመመለስ ስራ እየስራ
መሆኑንም ሀላፌው ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ በሚነዛው የሀስት መረጃና አከባቢውን ማህበረሰቡ መመልቀቅ
የለበትም ያሉት ሀላፌው በተለይም ለቡድኑ መንቀሳቀሻ መጠቀሚያነት በብዛት
ሊያገለግሉት ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች ሊሆኑ ሰለሚችሉ መምሪያው እነዚህ ተሽከርካሪዎች አከባቢያቸውም ሰላም የሆኑትን ወደ ቀያቸው የመላክየቀሩትን ደግሞ እንዲቆሙ የማድረግ ስራ እየተሰራ መሆኑን ኮማንደር አሳምነው ለጣቢያችን ተናግረዎል።

ከተማ አሰተዳደሩ ያወጣቸውን የክልከላ ህጎች ለማስከበር በትኩረት እየተሰራ
መሆኑን የገለጸው መምሪያው በከተማዋ በሁሉም አቅጣጫዎች ጥብቅ ፍተሻ
እየተደረገ እንደሆነና ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ነገሮችን ሲመለከት ለጸጥታ አካል
እንዲሳውቅ ጥሪ አቅርቦ የጠላት መሳሪያ ከሆነው የሀሰተኛ መረጃ ራሱን
ሊጠብቅ እነደሚገባ መምሪያው ገልጿል።
ከደሴ FM
#በከድር መሀመድ

@dessiecityfootballclub