Get Mystery Box with random crypto!

' የሚፈልገዉ አንድ እድል ማግኘት ብቻ ነዉ እራሴን በሚገባ ማሳየት እችላለሁ '........... | Dessie City Football Club

" የሚፈልገዉ አንድ እድል ማግኘት ብቻ ነዉ እራሴን በሚገባ ማሳየት እችላለሁ "...........

ኤርሚያስ ሞገስ ይባላል ገና ወጣት ነዉ ፤ በብዙ ዉድድሮች ላይ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ ከመሆንም አልፎ ዉድድሮች ላይ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ መመረጥ ችሏል።

ፌድሬሽኑ በሚያዘጋጀዉ የክልል ሻምፒዮና ላይ አማራ ክልልን በመወከል ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እና የዉድድሩ ኮከብ ተጫዋች ነበር ፤ ደሴ ከነማ ወደ ከፍተኛ ሊግ ሲያድግ ደግሞ የቡድኑ አባል ነበር።

ባለፈዉ በሀዋሳ በተደረገዉ የክለቦች ሻምፒዮና ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን በመወከል ክለቡን ለሁለት አመታት በአምበልነት በመምራት መልካም የሚባል እንቅስቃሴን ማድረግ ችሎ ነበር ፤ በዚህም የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌድሬሽን የዉድድሩ ኮከብ በማለትም ሸልሞት ነበር።

ኤርሚያስ ከአጥቂ ጀርባ የአጥቂ አማካይ እና የተከላካይ አማካይ በመሆን መጫወት የሚችል ሲሆን ኳስን መሰረት አድርጎ ለሚጫወት ቡድን በመሃል ስፍራዉ ትልቅ እርዳታን እንደሚያደርግ ያምናል።

በመሆኑም በከፍተኛ ሊግ እንዲሁም በፕሪሚየር ሊጉ ከፈለጋችሁ በቀጥታ እንዲሁም በራሱ መተማመን ስላለዉ በሙከራም መፈረም ይችላል።

በመሃል ስፍራዉ ስለሚጠቅማችሁ ይህንን ወጣት ተጠቀሙት።

ሌላም ይቀጥላል.........
@dessiecityfootballclub