Get Mystery Box with random crypto!

የወይዘሮ ስሂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 928 ተማሪዎች በልዩ ልዩ ሙያና ቴክኒክ ዘርፎች አስመረቀ፡፡ | ደሴ ታይምስ®️ - ወሎ

የወይዘሮ ስሂን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 928 ተማሪዎች በልዩ ልዩ ሙያና ቴክኒክ ዘርፎች አስመረቀ፡፡
*******
ሌጁ ዲን አቶ ሰለሞን ይመር እንደገለጹት በስልጠና አመቱ በቀንና በማታ ፕሮግራም 928 ተማሪወች የተመረቁ ሲሆን በደረጃ ሶስት 238 በደረጃ አራት 606 በደረጃ አምስት 84 ናቸው፡፡

ከነዚህ ተማሪዎች መካከል 428ቱ ሴቶች ናቸው፡፡

የወይዘሮ ስሂን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአካባቢውን የልማት ኮሪደርና ገበያው የሚፈልገውን የሠለጠነ የሠው ሀይል ለማፍራት በ59 የሙያ ደረጃዎች ስልጠናን እየሠጠ ይገኛል፡፡

ከደረጃ አንድ እስከ አምስት በቀንና በማታ ፕሮግራም 2ሽህ 120 ተማሪዎች በስልጠና አመቱ እያሰለጠነ ይገኛል፡፡

መደበኛ ባልሆኑ አጫጭር ስልጠና በስራ ፈጠራና በቴክኒክ ክህሎት 5ሽህ 90 ሠልጣኞችን አሰልጥኗል፡፡

ኮሌጁ በወረራ ምክንያት 103ሚሊየን 917ሽህ 228 ብር ዋጋ ያላቸው ማሽኖች ወድመውበታል፡፡

ይህንን ውድመት ተቋቁሞ ሰልጣኞች በቂ ክህሎት ኖሯቸው እንዲመረቁ ጥረት ያደረጉ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል

ደሴ ታይምስ> @DessieCity

ፌስቡክ ፔጅ http://www.facebook.com/DesieTimes