Get Mystery Box with random crypto!

ሰዎች ምክንያት እየፈለጉ ጥፋተኛ ካደረጉህ ሊርቁህ እንደፈለጉ እየነገሩህ ነውና ከአንደበትህ አልፎ | ደስታ እና ፍቅር

ሰዎች ምክንያት እየፈለጉ ጥፋተኛ ካደረጉህ ሊርቁህ እንደፈለጉ እየነገሩህ ነውና ከአንደበትህ አልፎ ውስጥህን የሚያዳምጥ አምላክ መቼም የትም እንዴትም ካንተ ጋር ነው።

በህይወት ውስጥ ፈተና ከበዛብህ አትዘን ታገስ...የጨረቃ ውበት የሚጨምረው ጨለማ በዙሪያዋ በጨመረ ቁጥር ነውና።

ወዳጄ ሆይ እራስህን ብዙም ግልፅ አታርግ ምክንያቱም ግልፀኝነትህን ተጠቅሞ ወዳጅህም ጠላትህ ይሆናልና!

ቀን ጠብቆ የወጋህን እሾክ ጊዜ ጠብቀህ እስክትነቅለው ድረስ ታገስ እንጂ አውጡልኝ ብለህ ቁስልህን ለሰው አሳልፈክ አትስጥ ምክንያቱም የባሰ ያቆስልሀልና!

. እንደ እኔ አንዴ እንደምትኖር አውቀህ ጊዜህንና ጉልበትህን በማይጠቅም ቦታና ማንነት ውስጥ አታባክን።

መቆጣጠር የምትችለው ስብዕናህን እንጂ የህይወት ክስተቶችህን እዳልሆነ ተረዳ ።

ሲጨልም ለራስህ ብርሃን ሁን ።
ሲበራ ራስህን ከህይወት ጨረር ጠብቅ ።

በፍላጎትህና በምትችለው መሀከል ያለውን ልዩነት የሚችል ስብዕና ይኑርህ ።

የሰዎች ሀሳብ ያንተን ማንነት አይገልፀውም ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ።

ሁሌም ቢሆን ለሰወች በጎ ነገር አድርግ ለበጎ ስራ ምላሽ ከፈጣሪ ነውና
በጎነት መልሶ ይከፍላል

* * * * * *
@desitanafiker