Get Mystery Box with random crypto!

ደስታ እና ፍቅር

የቴሌግራም ቻናል አርማ desitanafiker — ደስታ እና ፍቅር
የቴሌግራም ቻናል አርማ desitanafiker — ደስታ እና ፍቅር
የሰርጥ አድራሻ: @desitanafiker
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.35K
የሰርጥ መግለጫ

For any promotion 👉 @Nabithapey

T
🏻@desitanafiker
. https://t.me/joinchat/AAAAAE3tCtdtJiTNZlMORg

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-13 07:23:31 #መስታወት_ልግዛልሽ
:
:
መቼስ በዚች ዓለም፤
አምናለው አልክድም፣
የሰው ፍፁም የለም።


ሰው ስህተት ይሰራል፤
ከዚያም ይታረማል፤
ከስ'ተቱ ይማራል።


ያንቺ ግን ፍቅርዬ መሳሳትሽ ወዛ፤
በ'ኔና አንቺ መሀል ደርሶ ሰው ሳይበዛ፤
እየው ዕድሜ ላንቺ ፍቅራችን ጠነዛ።


ከሰራሺው ስህተት ትማሪያለሽ ብዬ፣በተስፋ ስጠብቅ ወይ ዛሬ ወይ ነገ፤
እንኳን ልትማሪ ጥፋትሽ ስር ሰዶ፣ቅርንጫፍ አውጥቶ ይባሱን አደገ።


እናምልሽ ፍቅሬ...
ትናንት በመቅረዜ ድንግዝ ብርሃን ይዤ፤
ሁሉን ላ'ምላክ ጥዬ እሱን ተመርኩዤ፤
አጣጥቤ ልኬሽ ጨቅይተሽ ስትመጪ፤
ፍቅርሽ እንዳይርቀኝ ከልቤ እንዳትወጪ፤
መውደድ አስገድዶኝ ዳግም እንደገና፤
አምጥቼልሽ ነበር ውሀና ሳሙና።


ዛሬ ግን ታከተኝ ዛሬማ በቅቶኛል፤
ጭቃሽን ለማንፃት ውሀ ምቀዳበት ጉልበቴም ከድቶኛል።


እናም ካሁን ወዲህ ለኔም እንዲቀለኝ፣ላንቺም እንዲበጅሽ፤
በሳሙና ፈንታ ጭቃሽን እንድታይ፣መስታወት ልግዛልሽ።

@deaitanafiker
@dwaitanafiker
601 viewsNafii habesh, edited  04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 20:46:39 የደመናው እንባ

አጠፋህ ዝም አልኩኝ ካድከኝ ፊትህ ቆሜ
ፈልጌ እንዳልመረጥኩ ያኔ እጅህን ስሜ
ፍቅር ፍቅር እንዳላልክ ዛሬ ተለውጦ
ክብሬ ይሻለኛል የሚያኖር አብልጦ
ስትቀየር በሀብት መደበቅ ከበደኝ
ከቃላቴ በፊት እንባዬ ቀደመኝ
አሳዘንኩት መሰል ደመና አለቀሰ
ህመሜን ተረድቶ እንደውሀ ፈሰሰ
የደመናው እንባ ከእንባዬ ጋራ ገብቶ ሲቀላቀል
እንዳይከፍልህ ፈራው የበደልከኝ በደል የሰጠኸኝ ቁስል።

ሰላም (Selito)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@desitanafiker
384 viewsNafii habesh, edited  17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-07 22:04:47 #የኔ አዳም

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም ወዴት ነህ

@desitanafiker
@desitanafiker
420 viewsNafii habesh, edited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 10:36:39 . አንቺን ሳገኝሽ ነው!


ተራ ሰው ነበርኩኝ
ልክ አንቺን ሳገኝሽ
ከእድለኛ ተርታ ባንዴ ተሰለፍኩኝ

አንቺን ሳገኝሽ ነው
ዘንበል ያለ ጎኔ
የዘመመ አካሌ መስመር የያዘልኝ
አንቺን ሳገኝሽ ነው
ልፍስፍሱ ልቤ
ብኩኑ መንፈሴ በሳቅ የሞቀልኝ
አንቺን ሳገኝሽ ነው
የህይወትን ዳዴ በእርምጃ የጀመርኩት
አንቺን ሳገኝሽ ነው
ህይወት የሚባልን
የሰው ልጅን ማዕድ ልጎርስ የቆረስኩት

አንቺ መግበሽኝ
ህይወትን ቀመስኳት ጣፈጠችኝ በጣም
ለራሴው ማልኩለት
ቅዠት ቢመስል እንኳ ከዚ'ስ ህልም አልወጣም

አንቺን ሳላገኝሽ
ያባከንኩት እድሜ ሊቆጨኝ አሰኘው
ረጋ በል አልኩት
ረፈደ እንጂ አልቀረም እሰየው

ካንቺ ጋራ ያለምኩት
አምሯል ጎዳናየ ሂዱብኝ እያለ
ካይንሽ ያነበብኩት
ሰምሮልኛል መውደድ ናፍቆት እያከለ

መፈቀር ፀጋ ነው ያውም ባንቺ በኩል
....የሆንሽ የፍቅር እኩል

ፍቅር አፈቀረኝ ፍቅርን ወደድኩት
ናፍቆት አበደልኝ ናፍቆትን ናፈቅኩት
ስስት አሳሳሁት ስስቴም አሳሳኝ
ግሩምነት ውጦ ተራነት ተረሳኝ

ይሄ ሁሉ የሆነው
አንቺን ሳገኝሽ ነው!!!

N


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@desitanafiker
656 viewsNafii habesh, edited  07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-31 18:29:53 ሰዎች ምክንያት እየፈለጉ ጥፋተኛ ካደረጉህ ሊርቁህ እንደፈለጉ እየነገሩህ ነውና ከአንደበትህ አልፎ ውስጥህን የሚያዳምጥ አምላክ መቼም የትም እንዴትም ካንተ ጋር ነው።

በህይወት ውስጥ ፈተና ከበዛብህ አትዘን ታገስ...የጨረቃ ውበት የሚጨምረው ጨለማ በዙሪያዋ በጨመረ ቁጥር ነውና።

ወዳጄ ሆይ እራስህን ብዙም ግልፅ አታርግ ምክንያቱም ግልፀኝነትህን ተጠቅሞ ወዳጅህም ጠላትህ ይሆናልና!

ቀን ጠብቆ የወጋህን እሾክ ጊዜ ጠብቀህ እስክትነቅለው ድረስ ታገስ እንጂ አውጡልኝ ብለህ ቁስልህን ለሰው አሳልፈክ አትስጥ ምክንያቱም የባሰ ያቆስልሀልና!

. እንደ እኔ አንዴ እንደምትኖር አውቀህ ጊዜህንና ጉልበትህን በማይጠቅም ቦታና ማንነት ውስጥ አታባክን።

መቆጣጠር የምትችለው ስብዕናህን እንጂ የህይወት ክስተቶችህን እዳልሆነ ተረዳ ።

ሲጨልም ለራስህ ብርሃን ሁን ።
ሲበራ ራስህን ከህይወት ጨረር ጠብቅ ።

በፍላጎትህና በምትችለው መሀከል ያለውን ልዩነት የሚችል ስብዕና ይኑርህ ።

የሰዎች ሀሳብ ያንተን ማንነት አይገልፀውም ማንነትህ አንተ ውስጥ ነው ያለው ።

ሁሌም ቢሆን ለሰወች በጎ ነገር አድርግ ለበጎ ስራ ምላሽ ከፈጣሪ ነውና
በጎነት መልሶ ይከፍላል

* * * * * *
@desitanafiker
1.6K viewsNafii Habesh, 15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-28 05:09:30 አፍቃሪ ይትረፈው

በድህነቴ ወቅት ያቺን ሴት ሳፈቅር
ትዝ ይለኛል ያኔ ኪሴ ባዶ ነበር
መውደዴን ለመግለፅ ውብ ቃላት ደርድሬ
ላሳምናት ብጥር በአፍቃሪ ተግባሬ
አትምጣብኝ አለች አትድረስ ከበሬ
ነገሩ ልክ ናት እኔ አልፈርድባትም
ኪሴ ከጎደለ ፍቅረኛ አልሆናትም
የተትረፈረፈ ከሌለኝ እንጀራ
ሀብቴ ካልዘነበ ላፍታ ሳያባራ
ተቸግራ ልትኖር ልትልስ ፍቅፋቂ
ሴት ወደኔ አትመጣም ለሷ ነኝ ውዳቂ
ቅዳሜን ጠብቄ ክለብ ካልወሰድኳት
ሪዞርት ለሪዞርት ካላንሸራሸርኳት
በስጦታ ብዛት ካላጨናነኳት
እንዲሁ በባዶ አፈቀርኩሽ ብላት
በሉ እስቲ ፍረዱ ምን ፍቅረኛ ሆንኳት
እና ስነግራችሁ ያየሁትን እውነት
አፈቀርኩኝ ያለ ፍቅሩን እንዳያጣት
አስንቆ ሳይጥለው ያ ክፉ ድህነት
ፍቅር እቃ ሆኖ ገንዘብ ከሸመተው
ኪሱ ከቶ አይጉደል አፍቃሪ ይትረፈው



ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@desitanafiker
1.2K viewsNafii Habesh, edited  02:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-07 07:39:57
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሰን አደረሳቹ።

@desitanafiker
1.3K viewsNafii Habesh, edited  04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-08 04:29:16
ሁለት ሰዎች በአንድ ሆስፒታል ክፍል ውስጥ አልጋ ይዘው ተኝተዋል፡፡ ሁለቱም በጠና ታመው በአምላክ እጅ ተይዘዋል። አንደኛው ሳንባው የቋጠረውን ውሀ ለማድረቅ ሲባል ለሰአታት ያህል አልጋው ላይ ቁጭ እንዲል ይደረጋል ከመስኮት አጠገብ ነው።

ሌላኛው ህመምተኛ ደግሞ በተቃራኒው ለሰአታት በጀርባው እንዲተኛ ይደረጋል። እነዚህ ህሙማን በቆይታቸው ብዙ ተጨዋውተዋል። ስለ ቤተሰቦቻቸው፣ ስለ ኑሯቸው፣ በወታደር ቤት ስለሰጡት አገልግሎት፣ የእረፍት ጊዜያቸውን የት እንደሚያሳልፉ... ወዘተ አውርተዋል።

ከመስኮት አጠገብ ያለው ህመምተኛ ቁጭ በሚልበት ሰአት ወደ ውጭ እየተመለከተ ሁሉን ነገር በጀርባ ለተኛው:ሰው ይገልጽለታል። በሚያማምሩ ዛፎች የተከበበ ሀይቅ ይታየኛል ... በሀይቁ ላይ ዳኪዬዎች ይዋኛሉ...... ህጻናት ደግሞ ከወረቀት የሰሩትን መርከቦች በሀይቁ ዳርቻ በማስቀመጥ ይጫወታሉ... ፍቅረኛሞች በአንድ እጆቻቸው አበባ በሌላው ደግሞ ተቃቅፈው ሀይቁን ይዞራሉ .. ከሀይቁ ባሻገር ውብ የሆነ ከተማ ይታየኛል ህፃናቶችም በደስታ ይቦርቃሉ " በማለት ዘወትር የሚያየውን ሁሉ በሚያምር አገላለፅ ይተርክለታል! ...

በዚህ አይነት ሁኔታ ሳምንታት አለፉ
አንድ ማለዳ ነርስዋ ገላቸውን ልታጥብ ውሀ ይዛ መጣች። ከመስኮት አጠገብ ያለው የተቀመጠው በሽተኛ ግን በህይወት አልነበረም። በጣም ደነገጠች። ጓደኛውም እንዲሁ አዘነ። ነርስዋ አስከሬኑን በቶሎ እንዲያነሱ ሰዎች ሌሎች ነርሶችን ጠርታ አዘዘቻቸቸው!

ያ ብቻውን የቀረው በጀርባው የተኛው በሽተኛ አልጋውን ከመስኮቱ አጠገብ እንዲወስዱለት ጠየቀ። ወሰዱለት። ሟች የነገርውን በሙሉ በመስኮት ለማየት በጣም ቸኩሏል። ቀና ብሎ ወደ ውጭ ተመለከተ። ከመስኮቱ ባሻገር ያለው ጥቁር ቀለም የተቀባ ግድግዳ ብቻ ነው። ደነገጠ!!!

"ምን ሆንክ?" አለቸው ነርሰዋ።

"ሰዉዬው ብዙ አስደሳች ነገሮችን በዚህ መስኮት አሻግሮ ይመለከት ነበር" አላት።

"ኧረ ሰዉዬው ማየት የማይችል አይነስውር ነበር" ስትል በመገረም መለሰችለት፡፡

ልብ የሚነካ ነገር.. ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ። ለካስ እሱን ለማስደሰትና የመኖር ተስፋ ለመስጠት ነበር ያን ሁሉ ነገር ፈጥሮ የሚያወራው። አንዱን ለማጠንከር ወይም ለማበርታት የኛ ጥንካሬና ብርታት አስፈላጊ ነው። ለሰወች ደግ ነገር በማድርግ የተጨነቀ አምሮአቸውን እረፍት እንስጠው::

መልካም ምሽት!
1.8K viewsNafii Habesh, 01:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-27 06:14:04 ነፃና ብልህ መሆን

ነፃነትን በማግኘት በኩል ስላለው ችግር ልነግራችሁ እወዳለሁ። ችግሩ ጥልቅ ጥናትና ግንዛቤ የሚፈልግ በጣም ውስብስብ ነዉ። ስለነፃነት፣ ስለሃይማኖት ነፃነት እና ያሹትና ማድረግ ስለሚቻልበት ነፃነት ብዙ እንሰማለን። ምሁራን ይህን ርዕሰ ጉዳይ ይዘው ብዙ መፃህፍትን ፅፈዋል፡፡ ይሁን እንጂ ወደ እውነተኛው መፍትሄ በሚወስደን መልኩ በቀላሉና በቀጥታ ልንደርስበት እንደምንችል አስባለሁ፡፡

በምዕራብ አቅጣጫ ፀሃይዋ ልትጠልቅ ስትቃረብና ዓይናፋሯ ጨረቃ ከዛፎቹ በላይ ብቅ ስትል አስተውላችሁ ታውቃላችሁ? አብዛኛውን ጊዜ በዚያ ሰዓት ወንዞች በጣሙን ይረጋሉ፤ ሁሉም ነገር በላያቸው ላይ ይንፀባረቃል - ድልድዩ፣ በላዩ ላይ የሚያልፈው ባቡር፣ አስደናቂዋ ጨረቃ፣ በኋላ ላይ ብቅ የሚሉት ከዋክብት:: ኩነቱ እጅግ ውብ ነው። እንዲህ አይነቱን ውበት ለማስተዋል፣ ለመመልከት፣ በሙሉ ትኩረት ለማጤን አዕምሮ ነፃ መሆን አለበት፡፡ በችግሮች፣ በስጋቶች፣ በግምቶች መሞላት የለበትም። እንዲያ ሲሆን ብቻ ነው አዕምሮ ተረጋግቶ ማስተዋልና እጅግ ልዩ የሆነውን ውበት ማድነቅ የሚችለው።
ምናልባትም የነፃነት ችግራችን የሚፈታው በዚህ መልኩ ሳይሆን አይቀርም።

ነፃ መሆን ማለት ምን ማለት ነው? ነፃነት ማለት የሚፈልጉት ማድረግ፣ ወደፈለጉበት መሄድ፣ የፈቀዱትን ማሰብ ይሆን? ከጥገኝነት መላቀቅ ማለት ነፃነት ነውን? በዓለም ላይ ከጥገኝነት የተላቀቁ ብዙ ሰዎች አሉ፤ ነፃ የሆኑት ግን እጅግ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ነፃነት ትልቅ ብልህነትን ይፈልጋል ፤ ነፃ መሆን ማለት ብልህ መሆን ማለት ነው። ነገር ግን ነፃ መሆንን በመሻት ብቻ ብልህነት አይመጣም፡፡ ብልህነት የሚመጣው ጠቅላላ አካባቢያችሁን፣ ማህበራዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ቤተሰባዊና ባህላዊ ተፅዕኖዎቻችሁን መገንዘብ ስትጀምሩ ነው። የተለያዩ ተፅዕኖዎችን ምንነት ለመረዳት - የወላጆችን፣ የመንግስትን፣ የማህበረሰብን፣ የባህልን፣ የእምነትን፣ የአምልኮን፣ ሳያስቡ የገቡበትን ባህል ተፅዕኖዎች- እነዚህን ሁሉ ተገንዝቦ ከእነዚህ ነፃ ለመሆን ጥልቅ ምልከታ ያስፈልጋል፡፡ሆኖም በውስጣችሁ ፍርሃት ስላለ በቀላሉ አትላቀቋቸውም። በህይወታችሁ ትልቅ ስፍራ አናገኝ ይሆናል ብላችሁ ትፈራላችሁ፤ ካህኑ አንድ የሆነ ነገር ይሉናል ብላችሁ ትፈራላችሁ፤ ባህሉን አልተከተልን፣ ትክክለኛውን ነገር አልፈፀምን ይሆን ብላችሁ ትፈራላችሁ። ነፃነት ፍርሃት ወይም አስገዳጅ ነገር የሌለበት፣ የደህንነትና የዋስትና ጥያቄ የማይነሳበት አዕምሯዊ ሁኔታ ነው፡፡

አብዛኞቻችን ደህንነታችን እንዲጠበቅ አንፈልግምን? ሰዎች ስለ ውበታችን፣ ስለመልካችን ወይም ስለእውቀታችን - እንዲነግሩን አንፈልግምን? እንዲህ አይነት ነገሮች የእርግጠኝነት ስሜት፣ የተፈላጊነት ስሜት ይፈጥሩብናል። ሁላችንም ዝነኞች መሆን እንፈልጋለን፡፡ ይሁንና አንድ ነገር በሆንን ቅፅበት ነፃ መሆናችን ያቆማል።

የነፃነትን ችግር ለመገንዘብ እውነተኛው ፍንጭ ይህ ነውና ይህንን በአፅንኦት ተመልከቱት፡፡ በዚህ የፖለቲከኞች፣ የስልጣን፣ የማዕረግና የደረጃ ዓለምም ሆነ ደግ፣ ሩህሩህ፣ ቅዱስ ለመሆን በምትመኙበት መንፈሳዊ ዓለም አንድ የሆነ ሰው ለመሆን ባሰባችሁ ቅፅበት ነፃ መሆናችሁ ይቀራል፡፡ የእነዚህን ነገሮች አይረቤነት የተገነዘበ፣ ልቡ ንፁህ የሆነና አንድ ሰው ለመሆን ምኞት የሌለው ሰው ነፃ ነው፡፡ የነገሩን ቀላልነት ከተገነዘባችሁ እጅግ የተለየ ውበቱንና ጥልቀቱን ታያላችሁ::

በትምህርት ውስጥ የሚገኙ ፈተናዎች አላማም ይኸው ነው - አንድ ደረጃ መስጠት፣ አንድ የሆነ ሰው ማድረግ፡፡ ማዕረጎች፣ ደረጃዎችና ዕውቀት አንድ የሆነ ሰው እንድትሆኑ ያበረታቷችኋል። ወላጆቻችሁና መምህራኖቻችሁ በህይወታችሁ አንድ ቦታ ላይ እንድትደርሱ፣ እንደ አጎታችሁ ወይም እንደ አያታችሁ ስኬታማ እንድትሆኑ ነግረዋችሁ አያውቁም? ታድያ አንድን ጀግና ወይም አንድን መምህር ለማስመስል ስትሞክሩ ነፃ አይደላችሁም:: የአንድን መምህር ወይም ወዳጅ ምሳሌ ከተከተላችሁ ወይም አንድ የሆነ ባህልን የምትከተሉ ከሆነ በውስጣችሁ አንድ የሆነ ነገር እንድትሆኑ ያስገድዳችኋል፡፡ ይህን ሃቅ ከተገነዘባችሁ ብቻ ነፃ ትሆናላችሁ፡፡

የትምህርት ዓላማ ከልጅነታችሁ ጀምሮ ሌሎችን እንዳታስመስሉ፣ ሁልጊዜም ራሳችሁን እንድትሆኑ ማስተማር መሆን አለበት- ምክንያቱም አስቀያሚም ሆናችሁ ቆንጆ፣ የዋህም ሆናችሁ ቀናተኛ ራስን መሆን በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ራስን መሆን አስቸጋሪ የሆነበት ምክንያት አሁን ባላችሁበት ሁኔታ የማይረቡ እንደሆናችሁ ስለምታስቡ ነው፤ ራሳችሁን ስትለውጡ ብቻ የተሻላችሁ እንደምትሆኑ ታስባላችሁ፤ ነገር ግን ይህ አይከሰትም:: ይሁን እንጂ እውነተኛ ማንነታችሁን ከተመለከታችሁትና ከተገነዘባችሁት አንድ ለውጥ እንዳለ ማየት ትችላላችሁ። ስለዚህም ነፃነት የሚገኘው አንድ የተለየ ሰው ለመሆን በመጣር ወይም የሻቱትን ነገር በማድረግ ወይም የባህልን፣ የወላጆችን፣ የመምህርን ትዕዛዝ በመከተል ሳይሆን ከአንዱ ቅፅበት እስከ ቀጣዩ ቅፅበት ማንነትን በመረዳት ነው::

እርግጥ ያ ይህን እንድታደርጉ አልተማራችሁም፤ የእናንተ ትምህርት አንድ ነገር እንድትሆኑ ነው የሚያበረታታችሁ፡፡ ይህ ግን ራስን መገንዘብ አይደለም፡፡ የእናንተ «ማንነት» በጣም ውስብስብ የሆን ነገር ነው፡፡ ወደትምህርት ቤት የሚሄደው፣ የሚጣላው፣ ጨዋታ የሚጫወተው፣ የሚፈራው ይህ አካል አይደለም ፤ አንድ ሌላ የተደበቀ ግልፅ ያልሆነ ነገር አለ፡፡ የምታስቡት ነገር ብቻ ሳይሆን በአዕምሯችሁ ውስጥ የተቀመጠው ነገር በሙሉ በሌሎች ሰዎች፣ በመፃህፍት፣ በጋዜጦች፣ በመሪዎቻችሁ የገባ ነው፡፡ ይህንን የምትገነዘቡት አንድ የሆነን ሰው ለመሆን ሳትፈልጉ ስትቀሩ፣ ማስመሰላችሁን ስታቆሙ፣ መከተላችሁን ስትተው ማለትም አንድ የሆነ ነገር እንድትሆኑ የሚገፋፋችሁን ባህል በሙሉ ስትቃወሙ ብቻ ነው:: እጅግ ልዩ ወደሆነው ነፃነት የሚመራው አብዮት ብቻ እውነተኛ ነው፡፡ የትምህርት ዓላማም ይህን ነፃነት መኮትኮት መሆን አለበት፡፡

ወላጆቻችሁ፣ መምህሮቻችሁ እና የራሳችሁ ፍላጐቶች አንድ ልዩ ሰው እንድትሆኑ ወይም ደስተኛና አስተማማኝ እንድትሆኑ ይፈልጋሉ። ታድያ ብልህ ለመሆን እስረኞች እንድትሆኑና እንድትጠፉ ምክንያት የሚሆኑት ተፅዕኖዎች በሙሉ መጥፋት ያለባቸው አይመስላችሁምን?

የአዲሱ ዓለም የመምጣት ተስፋ ሃሰተኛውን ነገር ለይተው በቃላት ሳይሆን በተግባር መቃወም በሚጀምሩ ሰዎች እጅ ውስጥ ነው። ለዛም ነው ትክክለኛው ትምህርት የሚያስፈልጋችሁ፡፡ በነፃነት ስትበለፅጉ ብቻ በባህል ላይ ያልተመሰረተ ወይም በአንድ ፈላስፋ ወይም ሃሳባዊ አስተሳሰብ ያልተቀረፀ አዲስ ዓለም መፍጠር ትችላላችሁ፡፡ አንድን ሰው ለመሆን ስትፈልጉ ወይም አንድን ሰው እንደ አብነት ወስዳችሁ እሱን ለማስመሰል ስትሞክሩ ነፃነት አይኖርም፡፡

ምንጭ ፦ ውስጣዊን ማንነት ማወቅ
(ክሪሽና ሙርቲ)
ተርጓሚ ፦ Na

@desitanafiker
@desitanafiker
1.3K viewsNafii Habesh, 03:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-11-22 11:52:36 #እኔ_እራሴን_የሆንኩኝ_ለት



እኔ እራሴን አይደለሁም፣
እያለውኝ ግን የለሁም።
አጉል ጉራን ስቸረችር ማልበገር ሲመስላቸው፣
በሆዴ ውስጥ ብዬ አውቃለው ባረገልኝ እንደ አፋቸው።
ክንብንቤን ገፈው ጥለው ማንነቴን ቢያስተውሉ፣
የኔስ ሕይወት ድብብቆሽ ከራሴው ጋር አኩኩሉ።


አንደበቴም አንድ ብሎ ዋሾነትን ከለመደ፣
ፍቅር ልቤን ስልብ አድርጎት እሩቅ ትቶኝ ከነጎደ፣
እምጥ ሰዶ ተንሰራፍቶ ናፍቆት ሥሩን ከዘረጋ፣
ውሸት ጉራን እየነዛው ስንቴ መሽቶ ስንቴ ነጋ።


ለሰው እንጂ ማስመሰሌ ዳሩ ለኔ ምን ፋይዳ አለው፣
ባደባባይ የሚቃጣኝ ጀግና ኩሩ ልብ እንዳለው።
ድንቄም ኩሩ ድንቄም ጀግና፣
ለነገሩ ማን አውቆብኝ እኔ እራሴን መች ሆንኩና።


እውነቱማ
ቁርሾ ዘልቆ መሀላችን ስንራራቅ ስንለያይ፣
ካንጀት ፈልቆ የሚፈሰው ሳቄም ሆኑዋል ካንገት በላይ።
እህል ውሀው አራቀኝም ሆዴም ጠግቧል ልቤ እርቦት፣
በሞላ ሰው አንቺን ይላል ጀሌ ጅጊ አጀብ ከቦት።
ትከሻዬ ምን ቢሰፋ መንፈሴ ግን ተሰበረ፣
ትዝታሽም ከጫንቃዬ እንደ ቋጥኝ ተከመረ።
ለነገሩ ምን ፋይዳ አለው፣
መች ለማለው መች ሰማለው፣
እኔ እራሴን እኮ አይደለው።


ወደ ራሴው ተመልሼ፣
ማስመሰሌን ከቀበርኩት ላያዳግም መሬት ምሼ፣
እውነት እውነት ፣
እኔ ራሴን የሆንኩኝ ለት፣
እሺታሽም ታክሎበት፣
ድሪቶውን ወዲያ ጥዬ ሀቁን ላንቺው ብናገረው፣
የፍቅራችን ዳግም ውልደት ያኔ ነበር ሚከበረው።


ለነገሩ ምን ሊጠቅም፣
አልናገር አልጋገር እኔ እራሴን ሆኜ አላውቅም።
#N
@desitanafiker
1.1K viewsNafii Habesh, 08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ