Get Mystery Box with random crypto!

ማስጠንቀቂያ ልጆቻችንን እንዴት ነው የምናሳድገው? ምን እያልናቸው፣ ምን እውቀት እያስገበየናቸው | የሰናፍጭ ቅንጣት 🤓🧐😎

ማስጠንቀቂያ

ልጆቻችንን እንዴት ነው የምናሳድገው?
ምን እያልናቸው፣
ምን እውቀት እያስገበየናቸው፣
ምን እየፈቀድን፣
ምን እየከለከልን፣  ነው የምናሳድጋቸው?

በመሠረቱ ልጆች መጠየቅ ይወዳሉ፤ ጠይቀው አይጨርሱም። ጠይቀው አይረኩም፣ በጥያቄ ላይ ጥያቄ ያከታትላሉ።

እኛም ምላሽ ከመስጠት ይልቅ መከልከል ይቀናናል፤ ምላሻችንም ክልከላ/ማስጠንቀቂያ ይበዛዋል።

ተው፣
አትንካ፣
እረፍ፣
ትወድቃለህ፣

የምላሾቻችን ድምር ውጤት በልጆቻችን ሥነ ልቡና ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል። አስተዳደጋቸውን እና ነገአቸውን ያመላክታል።

እኛ ለምን ፈሪ ሆንን?
በራስ መተማመን ለምን ጎደለን?
በአደባባይ ለምን መናገር ተሳነን?
ለምን አንሞክርም?
ለምን አንፈጥርም?
የምናስበውኝ የምንመኘውን ለምን አናደርግም?

ሌላ አዲስ ነገር የለውም ትናንት ከወላጆቻችን፣ ከአሳዳጊዎቻችን፣ ከአከባቢው ፣ ከማህበረሰቡ የሰማናቸው ቃላቶች፣ ያየናቸው ተግሳጾች፣ የተመከርነው ምክሮች፣ የስህተታችን ግብረ መልሶች ውጤት ስሪቶች ነን።

እኛስ ልጆቻችን እንዴት አይነት ልጆች እንዲሆኑ ነው የምንፈልገው?

በእርግጠኝነት እኛን መስለው እኛን አክለው እንዲያድጉ አንፈልግም።
ነገር ግን እንዴት እንዲሆኑ ነው እያሳደግናቸው ያለነው?

ሰው የዘራውን ያንኑ ያጭዳልና ልጆቻችንን እንዲያፈሩ የምንፈልገውን ዓይነት ዘር እንዝራባቸው።

ማስጠንቀቂያ ከበዛበት ምክርና ተግሳጽ ይልቅ ምሳሌነት ያለው ተግባር እና የሚያንጹ የሚያስተምሩ ቃላቶችን እንናገር።

ለቃላቶቻችን እና ለድርጊቶቻችን ጥንቃቄ እናድርግ። መልዕክቴ ነው።

መልካም ቀን።
ደረሰ ረታ

https://t.me/deressereta