Get Mystery Box with random crypto!

ከሁሉም ፈሰስ ፈሰስ ኢስላሚክ የእውቀት ግብይት ማግኛ

የቴሌግራም ቻናል አርማ delilsuleyman — ከሁሉም ፈሰስ ፈሰስ ኢስላሚክ የእውቀት ግብይት ማግኛ
የቴሌግራም ቻናል አርማ delilsuleyman — ከሁሉም ፈሰስ ፈሰስ ኢስላሚክ የእውቀት ግብይት ማግኛ
የሰርጥ አድራሻ: @delilsuleyman
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 461
የሰርጥ መግለጫ

أَلَمْ يَكُ نُطْفَةً مِّن مَّنِيٍّ يُمْنَىٰ

የሚፈስ ከኾነ የፍትወት ጠብታ አልነበረምን?
ثُمَّ كَانَ عَلَقَةً فَخَلَقَ فَسَوَّىٰ

فَجَعَلَ مِنْهُ الزَّوْجَيْنِ الذَّكَرَ وَالْأُنثَىٰ

ከእርሱም ሁለት ዓይነቶችን ወንድና ሴትን አደረገ፡፡
ከዚያም የረጋ ደም ኾነ (አላህ ሰው አድርጎ) ፈጠረውም፡፡ አስተካከለውም፡፡

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-18 21:52:59
የዛሬው እለት በሀምሌ ወርና በሀምሌ 11 ቀን መካሄዱ እለቱን ልዩ ያደርገዋል።ምክንያቱም ሀምሌ ወር በዘመነ ኢህአዴግ ለድምፃችን ይሰማ ንቅናቄ መነሻ ሰበብ የሆነው የአሕባሽ ግዳጅ ጠመቃ የተጀመረበት እለት ሀምሌ 6 ቀን 2003 ነበር።

«የአህባሽ ግዳጅ ጠመቃ ይቁምና መሪዎቻችንን መንግስት ሳይሆን እኛው እንምረጥ» በሚል በአወሊያ ተቃውሞ ሲያደርጉና ለሀምሌ 8 የሰደቃና አንድነት ዝግጅት ሲያደርጉ በአወሊያ ባደሩት ሙስሊሞች ላይ ሌሊት ጥቃት የተፈፀበትና መስዋእትነት የተከፈለበት ሀምሌ 6 ቀን 2004 ነበር።

እንዲሁም «እምቢ ለመብቴ» ያሉትን ሙስሊሞችንና ተወካዮችን በሽብር በመወንጀል በይፋ ማሰር የተጀመረበትም ሀምሌ 12 ቀን 2004 ነበር። በተለይ ደግሞ ልክ በዛሬው እለት ሀምሌ 11 ቀን 2006 በሕዝበ ሙስሊሙ ላይ የጥቁር ሽብር ጥቃት የተፈጸመበት እለት ላይ የዛሬው የመጅሊስ ምርጫ መደረጉ እለቱን ታሪካዊ አድርጎታል።
አህመዲን ጀበል
59 viewsላተህዘን, 18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:47:26 @delil12
57 viewsላተህዘን, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:00:00 እስቲ የተሰማቹህን ስሜት አጋሩኝ
61 viewsላተህዘን, 18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 20:59:59 『«የብስራት ዜና ተሰማ » ብሎ ህዝቤ ከተላቀሰ በኃላ የሆነውን ያየ ሰው ዳግመኛ በትንሽ ድል አይፈነጥዝም..
ግለሰቦችንም ነገ ሲያጠፉ መኮነን እስኪከብደው አይሰቅልም ..አያሞግስምም። ሰዎች ይመጣሉ ይሄዳሉ.. ይሾማሉ ይሻራሉ ትልቁ ነጥብ እርሱ ሳይሆን ሰርተው ሚያልፉት ነገር ነው.. የኛ ትኩረት መሆን ያለበት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማገዙና መገፋፋቱ ላይ ነው..
.. ያገኘን መልካም ነገር ከአላህ እንጂ በኛ ኃይልም ሆነ ብልሃት አለመሆኑን አውቀን በደስታ መጦዙንና መበሻሸቁንም እንተው.. ደሞ ያገር ጉድ የሚጠብቀን ተቆጥሮ የማያልቅ የቤት ስራ ያለብን ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች መሆናችንንም አንርሳ ባረከላሁ ፊኩም!
«በጨረስክም ግዜ ልፋ (ቀጥል)። ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል» አል-ሸርሕ 7-8』


: ኢማን
63 viewsላተህዘን, 17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:04:22
ቦሄቃር ግቦ
ቦሄቃር ግቦ
ቦሄቃር ግቦ
67 viewsላተህዘን, 16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:01:35
የአህባሻዊ መጅሊስ ፍፃሜ

ነብያችን ሰዐወ ግዜ የነበረው እስልምና ዛሬ ላይ አህባሽ ነባሩ እስልምና በሚል ሽፋን ገደል ከተቶታል። ነብያችን ሰዐወ ስለአንድነት ይሰብካሉ አህባሾች አንድ አንሆንም ይላሉ። እውነት ቁርኣን እና ሀዲስ የሚከተሉ ከሆነ ለምን አንድነት ቃል ከበዳቸው። የአይ*ሁድ ተላላኪ ለኢስላም ሳይሆን ኡማን ለመከፋፈል ነው የሚሰሩት። ህዝበ ሙስሊሙ እየታገለ ያለው ይህን መሰሪ ነው።

አንድነት ለሙስሊሙ ብቸኛ አማራጭ ነው። የአህባሽ አንጃ አንድነትን ለመከፋፈል ከጠላቶች ጋር እየሰራ መሆኑ በግልፅ እያሳየ ይገኛል። መንግስት ለሀገር ሰላም እና መረጋጋት የአህባሽ አንጃ ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወስዳል ብለን እንጠብቃለን።

ህዝባዊ መጅሊስ እንጂ አህባሻዊ መጅሊስ አይደገምም አንቀበልም

#አንድነት #ለሀገር #ሰላም
_________________________________________
የኡስማን ኢብን አፋን-ጠሮ መስጂድ ወጣት ጀምዐ
@delilsuleyman
@delilsuleyman
67 viewsላተህዘን, 16:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 15:21:09 አላህ መጅሊሱን ከእንግዲህ ቡኃላ ህዝቡ የማያለቅስበት እና ለሀገርም ሸክም የማይሆንበት ያድርገው
**********
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለቀጣይ 3 ዓመታት የሚመሩ ኃላፊዎችን በዛሬው ዕለት ሐምሌ 11/2014 እየተካሄደ ባለው ጉባኤ መረጠ::
ሸኽ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ ፕሬዝዳንት
ሸኽ አብዱልከሪም ሸኽ በድረዲን ም/ፕሬዝዳንት
ሸኽ አብዱልአዚዝ ም/ፕሬዝዳንት
ሸኽ ሀሚድ ሙሳ ፀሀፊ
የተመረጡ አመራሮች ተቋሙ ተቋማዊ አሰራሪን ተከትሎ ለህዝብ እና ለሀገራችን ጠቃሚና የሚዳሰሱ ሥራዎችን ለመስራት ዓቅሙና ፅናቱን ይስጣቸው:: ህዝብም ከወሬ አልፎ በተባር ከጎናቸው በመቆም የተቋሙ ሁለንተናዊ ግንባታ ላይ ኃላፊነቱን ዲወጣ ጥሪየን አቀርባለሁ:: መንግስትም ህገመንግስታዊ የሆነውን ህግን የማስከበር ሥራውን በአግባቡ በመወጣቱ እናመስግናለን::

Rabbiin Gumii dhimma Islaamaa kana kana booda kan ummanni keenya irraa boohuufii ba’aa biyyaa ta’uu irraa haa baraaru
***********
Gumiin dhimma islaamaa federalaa
Guyyaa har’a 11/2014 Gumii hotela Sheratonitti ta’een
1.She Hajji Ibrahim tufa prezidaantii
2.Sh Abdulkerim She Bedredin itti aana
3.She Abdulaziz She Abdulwali itti aana
4. She Hamid Musa barreesaa ta’uun filatamanii jiruu.
Rabbiin humna cima jarmaya kana ijaaruuf kan ummata keenyafii biyyaafis tolu ijaran isaaniif haa kennu. Ummanni keenyas qabatamaadhaan biraa dhaabbatee gadi dhaabuu qaba.
Mootummaanis heera mootumma irrati hundaahee seera kanchiisuu isaatiif haa galtoomu.
62 viewsHH+ $$, 12:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 15:16:48 የኢትዮጲያ ሙስሊሞች የተቋማዊ ለውጥ እና አንድነት 2ኛ ዙር አገር አቀፍ ጉባዔ በስኬት ተጠናቋል
53 viewsHH+ $$, 12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 15:13:49 መልካም ዜና
===========
ሲጠበቅ በነበረው በዛሬው የመጅሊስ ጉባዔ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ፕሬዝዳንት ተደርገው ተሹመዋል። ከስራቸውም ሁለት ምክትሎች ተመርጠዋል።


በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ እየተካሄደ በሚገኘው ሁለተኛ ዙር ጉባዔ ከቀድሞ 300 ተሳታፊዎች መካከል 261ዱ ተገኝተዋል። ቀሪዎቹ 39ኙ በሞት፣ በህመምና በሐጅ ጉዞ ምክንያት ሳይታደሙ ቀርተዋል።


በዚህ ጉባዔ ላይ በርካታ የመጅሊሱ አመራሮች እየተመረጡ ሲሆን ዋና ፕሬዝዳንቱ ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ መደረጋቸው ታውቋል።


አላህ ለኡማው የሚበጁ ያድርጋቸው። መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ ብያለሁ ሸይኽ ሐጂ!

መላው የኢትዮ ሙስሊምና ለዚህ ለውጥ ህይዎታችሁን፣ ንብረታችሁን፣ ክብራችሁንና ጊዚያችሁን ለሰዋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን።
አል-ሐምዱ ሊላህ አላህ ቀሪ ዘመናችንን ያሳምርልን።
56 viewsHH+ $$, 12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ