Get Mystery Box with random crypto!

ምርጥ_ታሪክ አንዲት ሴት በምሬት ስታለቅስ ኑሕ ዐለይሂሰላም ተመለከቷት'ና፦ «ለምን ታለቅሻለሽ | ከሁሉም ፈሰስ ፈሰስ ኢስላሚክ የእውቀት ግብይት ማግኛ

ምርጥ_ታሪክ

አንዲት ሴት በምሬት ስታለቅስ ኑሕ ዐለይሂሰላም ተመለከቷት'ና፦ «ለምን
ታለቅሻለሽ?» አሏት።

ሴትዮዋም፦«በለግላጋ የወጣትነት እድሜ ላይ የሚገኝ ጎረምሳ
ልጅ ሞቶብኝ ነው» አለቻቸው።

ኑሕም ዐለይሂሰላምም ፦ «የልጅሽ እድሜው ስንት ነበር...?»አሏት።

ሴትዮዋም፦ «ገና እኮ 300 አመቱ ነው» አለቻቸው።

ኑሕ ዐሰ ሊያፅናኗት እየሞከሩ፦ «ታድያ እድሜያቸው ከ60-70
የማይሻገሩ ኡመቶች መሀል ብትኖሪ ምን ልትሆኚ ነው?»
በማለት ጠየቋት።

ሴትዮዋም፦ «እንዴ! ከ60-70 አመት ብቻ የሚኖሩ ኡመቶች አሉ
እንዴ?» ብላ በመገረም ጠየቀቻቸው።

ኑሕም፦ «አዎን» አሏት።


ሴትዮዋም፦ «ግን ይችን ውስን አመት በህይወት ሲቆዩ አላህን
ያምፁታል» በማለት አስከትላ ጠየቀቻቸው። (የኛን ጉድ
አላየች...)

ኑሕም፦ «እንደውም አብዝኻኛዎቻቸው አማፅያን ናቸው» ብለውጉዳችንን አወጡት።

ሴትዮዋም፦ «ግን እነዝያ ኡመቶች ለውስን ግዜ ብለው ዱንያ
ላይ ይስገበገባሉ?» ስትል ጥያቄዋን ሰነዘረች።

ኑሕም፦ «አዎና! እንደውም ዋና ጭንቀታቸው ዱንያ ነው፤
ጥቂቶቻቸው ሲቀሩ» አሏት።
ሴትዮዋም፦ «ታድያ በመካከላቸው በሚፈጠሩ ጉዳዮችስ ይወቃቀሳሉ?» ስትል ጠየቀች።

ኑሕም፦ «ኧረ እንደውም በትንንሽ ጉዳዮች ይገዳደላሉ» ብለው
መለሱላት።

ሴትዮዋም፦ «ግን እንደው ለዚህች አጭር እድሜ ብለው ጎጆ
ይሰራሉ...?» ስትል ጠየቀቻቸው።

ኑሕም፦ «ወይ ጎጆ...! ኧረ እንደውም ለመቶዎች አመታት
የሚቆዩ ትላልቅ ህንፃዎችን ነው ሚገነቡት፤ ግና ትተውት ይሞታሉ» አሏት።
ሴትዮዋ በምትሰማው ነገር ተደንቃ፦ «ኧረ ወድያ...! እኔ እዝያ
ኡመት ውስጥ ብሆን ህይወቴን በሙሉ አንዲት ዛፍ ስር ሱጁድ
አድርጌ እጨርሳት ነበር(ደሞ ለ60 አመት!) » አለቻቸው
ይባላል...

አጂብ ነው ወላሂ

እስቲ ራሳችንን እንፈትሽ?

@delilsuleyman
@delilsuleyman