Get Mystery Box with random crypto!

#ምንኛ_ያማረች_ምክር ➩ አያት ለልጅ ልጁ የመከረው ጣፋጭ ምክር! የምትወዴውን ሰው ማሞገስ አ | ከሁሉም ፈሰስ ፈሰስ ኢስላሚክ የእውቀት ግብይት ማግኛ

#ምንኛ_ያማረች_ምክር

➩ አያት ለልጅ ልጁ የመከረው ጣፋጭ ምክር!

የምትወዴውን ሰው ማሞገስ አታብዛ፣
ጌታውን ከማይታዘዝ ሰው ጋር አትጓዝ፣
ቁጭ ስትል ሰዎችን አትማ፣

በራሱ ጊዜ ከአንተ የራቀን ጓዴኛ ለመቅረብ አትሯሯጥ፣

ራስህን አታቅል፥ አትኩራ፣
እጅግም አትለሳለስ፥ እጅግም አትንጠባረር፣

እውነቱን የሚያወራ ሰው በብዛት አይምልም፥ ታማኝ ሰው ራሱን መልካም አድርጎ አይስልም፣

ሥራውን ለአላህ ብሎ የሚሠራ ሰው ኋላ ላይ አይጸጸትም፣

ቸር ሰው አይመጻደቅም፣
ራስህን ሁን፥ ሌሎች እንዴሚፈልጉት አትሁን፣

ሰዎችን ማክበርህ የሆነ የምትፈልግባቸው ጉዳይ አለ ማለት አይደለም። ስለ ዲንህና አስተዳዴግህ ልታስተምራቸው ጅማሮ እንጅ፣

አክብር → ትከበራለህ!

➣ በጸባይህ ውብ ሁን!
➣ ባለህ ተብቃቃ፥ ራስህን ዝቅ በማድረግ ትልቅ ሁን።

➣ ከኋላህ ሆኖ ስለአንተ ወዴሚያወራ ሰው አትመልከት። ምክንያቱም እርሱ በመሠረቱ ከኋላህ እንጅ ከፊት ለፊትህ አይዴለም።

➣ ከቁርኣን ምን ያክል እንደምትሸመድድና እንዴምትቀራ ለሰዎች አትንገራቸው። ይልቁንም በአንተ ውሰጥ ቁርኣንን እንዲያዩ አድርጋቸው።

➣ የተራበን አብላ፣ የተራቆተን አልብስ፣ እርዳታህን የሚሻን አግዝ፣ ለየቲም እዘን፣ የበደለህን እለፈው፣ ለወላጆችህ መልካም ዋል፣ ለሁሉም ፈገግ በል!

➣ ቁም ነገሩ ከቁርኣን ምን ያክል ደርሰሃል ወይንም ሸምድደሃል ሳይሆን፤ ቁርኣን በአንተ ውስጥ የት ደርሷል የሚለው.

ሼር በማድረግ አትርሱ ሁሉም ምክር ከአላህ ነው

@delilsuleyman
@delilsuleyman