Get Mystery Box with random crypto!

በፍቅር እፍ ብለው ይከንፋሉ። ሆኖም ነገሩ ሁሉ እየተገለጠላቸው ሲመጣ፣ አታለለችኝ አታለለኝ መባባል | Deinstein_21

በፍቅር እፍ ብለው ይከንፋሉ። ሆኖም ነገሩ ሁሉ እየተገለጠላቸው ሲመጣ፣ አታለለችኝ አታለለኝ መባባል ይጀምራሉ!

ጃፓናውያን ከሶቭየት ህብረት የተሰባበሩ የቢራ ጠርሙሶችን እየገዙ ወደ ባህር ይጥሏቸው ነበር። ስለምንስ ይህን አደረጉ?

ጃፓን ከሶቭየት በርካሽ ዋጋ መጠናቸው እጅግ የበዛ የጠርሙስ ስብርባሬዎችን ታስገባ ነበር። ሆኖም ጃፓናውያኑ የሚፈልጉት ስብርባሪ ጠርሙሶችን ሳይሆን ጠርሙሶቹ ታሽገው የሚመጡባቸውን የእንጨት ሳጥኖችን ነበር።

ከመርከብ ላይ እቃውን እንደተረከቡ ወዲያውኑ ጠርሙሱን ወደ ባህሩ ይጥሉታል። የተቀረውን የማሸጊያ ሳጥን በቀስታ ይበታትኑትና በአገሪቷ ውስጥ ላሉ የፈርኒቸር አምራቾች ያከፋፍሉታል።

ጃፓን ውስጥ ጥራት ያለው የእንጨት ምርት እጥረት ነበርና ይህን ዘዴ ተጠቅመው ለአመታት ከሶቭየቶች በርካሽ ዋጋ ሳጥኖችን ሲያስገቡ ቆዩ። በመጨረሻም ሶቭየት ማሸጊያዎቹን ወደ ካርቶን ስትቀይር ጃፓናውያን የተሰበሩ ጠርሙሶችን መግዛት አቆሙ።

#ቁምነገሩ ሰዎች ከእኛ የሚፈልጉትን ነገር በእርግጠኝነት ማወቅ አንችልም። ያለንም አማራጭ ቢኖር ሙሉ እምነታችን በእነርሱ ላይ እስኪሆን ድረስ በተጠንቀቅ መቆየት ነው። የብዙ ባለትዳሮች ችግርም ይሄ ነው።

በፍቅረኛነት ዘመናቸው አንደኛቸው በሌላኛቸው ውስጥ ያለውን ሰይጣን ማስተዋል አይችሉም።

በፍቅር እፍ ብለው ይከንፋሉ። ሆኖም ነገሩ ሁሉ እየተገለጠላቸው ሲመጣ፣ አታለለችኝ አታለለኝ መባባል ይጀምራሉ።

መተማመን በራሱ ችግር የለውም ሆኖም ግን ማስተዋል የሌለበት እምነት ገደል ይከታል::