Get Mystery Box with random crypto!

የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

የቴሌግራም ቻናል አርማ degusamraw — የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®
የቴሌግራም ቻናል አርማ degusamraw — የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®
የሰርጥ አድራሻ: @degusamraw
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 747
የሰርጥ መግለጫ

የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ:: (በመ/ር ሲራክ ሰሎሞን)
...
አንተ ሰው ቃለ እግዚአብሔርን ተማር፤ ባትለወጥም ዝም ብለህ ተማር! ኹልጊዜ ተማር። ላትስተካከል ትችላለህ፤ ላትለወጥ ትችላለህ፤ ግን ተማር፤ ቢያንስ ቢያንስ ጥሩ ሰው እንኳን ባትኾን ራስህን ለመውቀስ የምትችልበት ዓቅም ታገኛለህ፤ ካልተማርክ ግን ራስህን እንኳን መውቀስ የምትችልበት ዓቅም አታገኝም::

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-19 20:05:10 የአርቲስት ንብረት ገላው ሰርግ ዝማሬዎች በተወዳጅ ዘማሪዎቻችን

62 viewsMr. Sirak Solomon, 17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 12:23:31
63 viewsMr. Sirak Solomon, 09:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 11:25:08

ምስክርነት ይሉሃል እንዲህ ነዉ፡፡

የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታማኝ አገልጋይ የሆነው ታምራት ቶላ ሪኮርድ ሰብሮ ማራቶን በማሸነፍ የወርቅ ሜዳልያ ለሀገራችን አስገኝቷል።
እግዚአብሔርን ያሰቀደመ፣ በእምነቱ ሙሉ የሆነ ሰው በአደባባይ( በማዕተቡ፣ በማማተቡ፣ በክሩ፣ በስነ-ምግባሩ፣ ወ.ዘ.ተ) ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያንን ያወድሳል እንዲሁም በሄደበት ቦታ እና ስፍራ ያከብራታል፡፡
66 viewsMr. Sirak Solomon, 08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 11:21:08
145 viewsMr. Sirak Solomon, 08:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 09:38:13

62 viewsMr. Sirak Solomon, 06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:30:14
ድንቅ ንግግር

ከአትሌታችን ጎትይቶም ገ/ስላሴ አንደበት የወጣ ቃል ነው

"የእኔ እናትና አባት ሲደሰቱ ብሰማና ባያቸው ደስ ይለኝ ነበር"

ለሀገራችን ሶስተኛውን ወርቅ በማራቶን ያስገኘችው ጎይትቶም ገ/ስላሴ ከድሉ በኋላ አስተያየቷን ሰጥታለች።

"ደስ ብሎኛል ደስታዬ ግን የተዘበራረቀ ነው ፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደተደሰተው የእኔ እናት እና አባትም ሲደሰቱ ብሰማና ባያቸው ደስ ይለኝ ነበር።

እግዚአብሔር ሰላሙን ያምጣ ደስታው ትልቅ ነው፣ ግን ደግሞ ትንሽ ተዘበራረቀብኝ አምና በዚህ ጊዜ የት እንደነበርኩ አውቃለሁ መንገድ ተከፍቶ ነው የወጣሁት።

በመጀመርያ እግዚአብሔር ነው የረዳኝ፣ ከዚያም በማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እንደ ወንድም ሆነው እንዳይከፋኝ እያገዙ ለዚህ ያበቁኝ አሰልጣኞቼ ናቸው አይዞሽ ሁሉም ያልፋል እያሉ እዚህ አደረሱኝ። አመሰግናቸዋለሁ!

እግዚአብሔር አምላክ ሀገራችን ኢትዮጵያን ሰላም ያድርግልን!!!

የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን፤ አብረው እናገልግል።

#ሼር
#share #Join

https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

ምንጭ:- አብይ ወንድይፍራው
101 viewsMr. Sirak Solomon, 18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:21:07
የጆርጅ ኦርዌል ትንቢታዊ መጽሐፍና የእኛ አሁናዊ ሁኔታ መመሳሰል!
ጆርጅ ኦርዌል የተባለ ድንቅ ጸሐፊ በ1949 እ.አ.አ. “Ninty eighty four” በሚል ርዕስ ለትውልድ ዓይን መግለጫ የሚሆን መጽሐፍ አበርክቷል። ይህ ሰው The Animal Farm, The Spider እና በሌሎች መጽሐፍቶቹ በዓለም ላይ ይታወቃል። አሁን የማነሳው መጽሐፍ ‘1984’ የሚለው ሲሆን ምክኒያቴም መጽሐፉ በአገራችን የሚካሄደውን የመንግሥትና የፖለቲካ ሥሪት በትንቢት ደረጃ አስቀድሞ የተመለከተ ስለሚመስል ነው። ሁለተኛው በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከተመለከቱት ጠቃሚ ርእሰ ጉዳዮች መካከል “አዲስ ንግግር/NEW TALK” የሚለው ትንቢታዊ ጽንሰ ሐሳቡን በመጋራት ዜጎች፣ የሥረዓታዊ ጥቃት ዒላማ የተደረጉት ኦርቶዶክሳዊያን ክርስቲያኖች ቸግሩን ለመቀልበስ ያለብንን ኃላፊነት ለማጉላት ነው።
የመረጥኩት ርዕሰ ጉዳይ የድርጊትና የንግግር መቃረንን የሚመለከትና የዚህ ሥርዓታዊ ጠባይ ምንጭ ምን እንደሆነ ጆርጅ ኦርዌል ከተነበያቸው ነጥቦች በመነሳት ነው።
ይህ መጽሐፍ የተጻፈው እንደ ልበወለድ ነው። ነገር ግን እንደ መንፈሳዊ ትንቢት አንዳንድ ነገሮቹ በኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ በተለይ ለኦርቶዶክሶች ሁለገብ ጥቃትና የአጥቂዎቹን ጠባይ የወለደውን ርእዮት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ሰውየው አሁን እየሆነብን ያለውን የሚናገር ይመስላል። መጽሐፉን ፈልጋችሁ አንብቡት። በመሥመር ላይም ይገኛል። ለአሁኑ እኔ ጥቂት ጥቅሶችን በአማርኛ እየተረጎምኩ በራሴ አገላለጥና አስተያየት በመጨመር አቅርቤዋለሁ።
--- ተከተሉኝ

ወደ ክፍል 1 ይቀጥላል---

የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን፤ አብረው እናገልግል።

#ሼር
#share #Join

https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
64 viewsMr. Sirak Solomon, 18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:26:55
የልቤ ደረሰ

በአጭሩ እንኳን ደስ አላችሁ!!!

ኬንያዊቷ አትሌትም በመጨረሻ ጠባይዋን አሳምራ ጎይትቶምን አቅፋታለች። በስፖርት ዓለም ከፍልሚያ በኋላ ሰላም ነው። ለእስራኤል የሮጠችው አትሌትም ከባድ ነበረች። ኤርትራዊቷም በጀግንነት ዐራተኛ ወጥታለች።
62 viewsMr. Sirak Solomon, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:26:13
እንኳን ደስ አለን

ምስክርነት ይሉሃል እንዲህ ነዉ፡፡

ኢትዮጵያ በሴቶች ማራቶን ወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች ባለማህቶቦቹ ደገሙት ጎይትቶም ገብረስላሴ በአለም አትሌቲክስ ሻምዮና የማራቶን ሪከርድ እግዚአብሔር ይመስገን!!!
እግዚአብሔርን ያሰቀደመ፣ በእምነቱ ሙሉ የሆነ ሰው በአደባባይ( በማዕተቡ፣ በማማተቡ፣ በክሩ፣ በስነ-ምግባሩ፣ ወ.ዘ.ተ) ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያንን ያወድሳል እንዲሁም በሄደበት ቦታ እና ስፍራ ያከብራታል፡፡

እህታችን፣ ልጃችን ጎይትቶም ገብረስላሴ በጣም ኩርተንብሻል እግዚአብሔር አምላክ በእምነትሽ ያጽናሽ!!! እኛም በምንሄድበት ስፍራ ሁሉ ቅድስት ቤተ-ክርስቲያናችንን እንድናከብርና እንድናወድስ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን

የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን፤ አብረው እናገልግል።

#ሼር
#share #Join

https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv
74 viewsMr. Sirak Solomon, 16:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 19:08:12
200 viewsMr. Sirak Solomon, 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ