Get Mystery Box with random crypto!

አስደሳች ዜና በኮሌጃችን ተመርቀዉ ማስተርስ ትምህርታችሁን ያልቀጠሉ የምታዉቋቸዉ  ተማሪዎች ካሉ | QDED 2010 Entry

አስደሳች ዜና
በኮሌጃችን ተመርቀዉ ማስተርስ ትምህርታችሁን ያልቀጠሉ የምታዉቋቸዉ  ተማሪዎች ካሉ በ2015 ዓም ወረሃዊ ክፍያዉ በወቅቱ ከተገለጸላችዉ ሳይጨምር በወር 1000/አንድ ሺህ ብር / እየከፈሉ በሁለት ዓመት ዉስጥ ትምህርታችዉን እንድያጠናቅቁ ኮሌጁ ይህንን ዕድል አመቻችቷል ስለሆንም የዲግሪ ዶክመንታችዉን /ቴምፖ/እና student copy ኮፒ በማድረግ እንዲሁም 4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ በመያዝ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በሚገኘዉ የርቀት ትምህርት ዲን ጽ/ቤት   በማስመራት በተፈቀደዉ ዲስካዉንት በመጠቀም  እንዲመዘገቡ  እንዲተላለፍ በታላቅ አደራ እናሳዉቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
1.  እስከ 16/1/2015 ለሚመጡ የምዝገባ በነፃ ከቀን 16/01/2015 በኃላ ሲመጡ የምዝገባ 500 ብር በአቢስንያ ባንክ ኩዊንስ ኮሌጅ   አካዉንት ቁጥር 61787879 እያስገቡ ደረሰኝ በመያዝ እንዲመጡ እናሳስባለን፡፡
2.  ከሌላ ኮሌጅ /ዩንቨርሲት በዲግሪ ተመርቆ ማስተርስ መቀጠል የሚፈልግ ወዳጅ ፡ ዘመድ፡ ጓደኛ እንዲሁም የስራ ባልደረባ ካለ በወር 1400 /አንድ ሺህ አራት መቶ ብር ወረሃዊ ክፍያ እንደሆነ አዉቆ ከላይ የተጠቀሰዉን ዶክመንት ይዞ በመምጣት  እንዲመዘገብ እና ትምህርቱን መቀጠል እንዲችል እንድታበረታቱ በታለቅ አክብሮት እንጠይቃለን!
አቶ ዳንኤል ተሸመ
የርቀት ት/ት ዲን ጽ/ቤት