Get Mystery Box with random crypto!

ደብረ ሰላም በዓለ እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን - ባሕር ዳር

የቴሌግራም ቻናል አርማ debreselambealeegziabhier — ደብረ ሰላም በዓለ እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን - ባሕር ዳር
የቴሌግራም ቻናል አርማ debreselambealeegziabhier — ደብረ ሰላም በዓለ እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን - ባሕር ዳር
የሰርጥ አድራሻ: @debreselambealeegziabhier
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.05K
የሰርጥ መግለጫ

✝️ በሰ/ት/ቤቱ የተከፈተ ገጽ ሲሆን ፤ በደብሩ የሚከናወኑ መረጃዎችን እና ማስተዋወቂያዎችን በውስጡ ያገኛሉ።
👉 Facebook fb.me/debreselambealeegziabhier
👉 YouTube
youtube.com/c/debreselambealeegziabhier
የመወያያ ግሩፕ ➩ @DebreSelam
💡ለጥያቄ እና አስተያየት 👇
▹ @BealeEgziContact

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 07:23:12
እንኳን ለሰ/ት/ቤታችን ፩፰ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አደረሳችሁ

እነሆ የ/ደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ሰ/ት/ቤት ሕጻናት ክፍል የተመሠረተበትን 18ኛ ዓመት ዓመታዊ የምሥረታ በዓል የፊታችን ነሐሴ 29/2014ዓ.ም 7:00 ሰዓት ጀምሮ በደመቀ ሁኔታ ያከብራል።

እርስዎም በእለቱ በመገኘት የሰንበት ት/ቤታችን 18ኛ ዓመት በጋራ እንዲያከብሩ በልዑ እግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።

በጉባኤው የተካተቱ መርሐ ግብራት
ያሬዳዊ ዝማሬ
ዝማሬ(በሕጻናት)
ስነ ጹሑፍ
አጭር የሥራ አፈጻጻም ሪፖርት
ጭውውት
ትምህርት

ዕለት :-29/12/2014ዓ.ም
ሰዓት:-ከቀኑ 07:00 ሰዓት
ቦታ:-በሰ/ት/ቤቱ አዳራሽ

Facebook fb.me/debreselambealeegziabhier

YouTube
youtube.com/c/debreselambealeegziabhier

የመወያያ ግሩፕ ➩ @DebreSelam

ለጥያቄ እና አስተያየት
▹ @BealeEgziContact
60 views04:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 20:01:04
“በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ።”
  — መዝሙር 118፥26
ላለፉት 1ዓመት ከ 10 ወራት በሰ/ት/ቤታችን የተከታታይ ኮርስ ትምህርት ሲማሩ የነበሩ አባላት ዛሬ 22/12/2014 እንዲህ በደመቀ ሁኔታ ተመረቁ።

    የመርሀግብሩ የፎቶ ቅኝት በጥቂቱ

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈተ ገጽ ሲሆን ፤ በደብሩ የሚከናወኑ መረጃዎችን እና ማስተዋወቂያዎችን በውስጡ ያገኛሉ።

Facebook fb.me/debreselambealeegziabhier

YouTube
youtube.com/c/debreselambealeegziabhier

የመወያያ ግሩፕ ➩ @DebreSelam

ለጥያቄ እና አስተያየት
▹ @BealeEgziContact
385 views17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 07:42:31 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
መዝ.91(92)፥13


መንፈሳዊ የምርቃት ጥሪ

እነሆ የደብረሰላም በዓለ እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤት ለተከታታይ አንድ አመት ከስድስት ወር ሲያስተምራቸው የነበሩ ደቀመዛሙርትን ዛሬ እሑድ ነሐሴ 22/2014 ያስመርቃል።

በእለቱም በተመራቂ ተማሪዎች
ያሬዳዊ ዝማሬ(ወረብ)
የበገና ዝማሬ
መነባንብ
የግል ዝማሬ
ኪነጥበብ
ትምህርት፦በተጋባዥ መምህራን
እንዲሁም ሌሎች ለነፍስ ስንቅ የሚሆኑ መርሃግብራት ይቀርባሉ።

እርስዎም በዕለቱ በመገኘት የመርሐ ግብራችን ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል፡፡

➤ ቀን ፡ ዛሬ እሑድ ነሐሴ 22/2014
➤ ሰዓት፡ ከቀኑ 7:30
➤ ቦታ ፡ በደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት አዳራሽ

አዘጋጅ ፡ የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ይላኩ...

Instagram + Facebook + Telegram
YouTube - www.youtube.com/c/DebreSelamBealeEgziabhier
280 views04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 16:14:41 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
መዝ.91(92)፥13


መንፈሳዊ የምርቃት ጥሪ

እነሆ የደብረሰላም በዓለ እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤት ለተከታታይ አንድ አመት ከስድስት ወር ሲያስተምራቸው የነበሩ ደቀመዛሙርትን ነገ እሑድ ነሐሴ 22/2014 ያስመርቃል።

በእለቱም በተመራቂ ተማሪዎች
ያሬዳዊ ዝማሬ(ወረብ)
የበገና ዝማሬ
መነባንብ
የግል ዝማሬ
ኪነጥበብ
ትምህርት፦በተጋባዥ መምህራን
እንዲሁም ሌሎች ለነፍስ ስንቅ የሚሆኑ መርሃግብራት ይቀርባሉ።

እርስዎም በዕለቱ በመገኘት የመርሐ ግብራችን ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል፡፡

➤ ቀን ፡ ነገ እሑድ ነሐሴ 22/2014
➤ ሰዓት፡ ከቀኑ 7:30
➤ ቦታ ፡ በደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት አዳራሽ

አዘጋጅ ፡ የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ይላኩ...

Instagram + Facebook + Telegram
YouTube - www.youtube.com/c/DebreSelamBealeEgziabhier
127 views13:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 19:31:40 በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋል፥በአምላካችንም አደባባይ ውስጥ ይበቅላሉ።
መዝ.91(92)፥13


መንፈሳዊ የምርቃት ጥሪ

እነሆ የደብረሰላም በዓለ እግዚአብሔር ሰንበት ትምህርት ቤት ለተከታታይ አንድ አመት ከስድስት ወር ሲያስተምራቸው የነበሩ ደቀመዛሙርትን የፊታችን እሑድ ነሐሴ 22/2014 ያስመርቃል።

በእለቱም በተመራቂ ተማሪዎች
ያሬዳዊ ዝማሬ(ወረብ)
የበገና ዝማሬ
መነባንብ
የግል ዝማሬ
ኪነጥበብ
ትምህርት፦በተጋባዥ መምህራን
እንዲሁም ሌሎች ለነፍስ ስንቅ የሚሆኑ መርሃግብራት ይቀርባሉ።

እርስዎም በዕለቱ በመገኘት የመርሐ ግብራችን ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል፡፡

➤ ቀን ፡ እሑድ ነሐሴ 22/2014
➤ ሰዓት፡ ከቀኑ 7:30
➤ ቦታ ፡ በደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት አዳራሽ

አዘጋጅ ፡ የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ይላኩ...

Instagram + Facebook + Telegram
YouTube - www.youtube.com/c/DebreSelamBealeEgziabhier
248 views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 21:36:21 “አፌ ጥበብን ይናገራል፥ የልቤም አሳብ ማስተዋልን።”-መዝሙር 49፥3

ታላቅ መንፈሳዊ የስነ-ፅሁፍ
ምሽት
<<አቤቱ በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው>>ማቴ 17፥4

የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ቤ/ክ ሰ/ት/ቤት የመሠናዶ ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ የፊታችን አርብ "ቡሄ እና ሌሎችም" በሚል ርዕስ ልዩ የስነ-ፅሁፍ ምሽት አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል።
በዕለቱ:- ፅሁፎች
ግጥሞች
መነባንብ
ተውኔቶች
ዝማሬ
እና መሰል ለነፍስ ስንቅ የሆኑ መርሀ ግብራት ተካተውበታል።

እርስዎም በእለቱ በመገኘት የመርሀግብሩ ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።

ቀን፦ 20/12/2014 ዓ.ም
ሰዓት፦ 9:30
ቦታ፦ደ/ሰ በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት አዳራሽ

አዘጋጅ ፡ የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት የመሰናዶ ተማሪዎች ግቢ ጉባኤ

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ይላኩ...

Instagram + Facebook + Telegram
YouTube - www.youtube.com/c/DebreSelamBealeEgziabhier
382 views18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 20:11:49 ሰሞኑን በከተማችን ባሕርዳር Ours ካፌ በሚባል ቦታ የሠራተኛዋን ሥዕለ ማርያም እና የጸሎት መጽሐፍ ቀምቶ በመቅደድ ከፎቅ በመወርወር የተፈጸመው አጸያፊ ተግባር ዙሪያ በብፁዕ አባታችን አቡነ አብርሃም የተላለፈ መልእክት በዩቲዩብ ገጻችን ይመልከቱ












የባሕረዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚዲያ
@AndnetMedia @EOTCBDSSU • #ዩቲዩብ #YouTube
130 views17:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 14:03:02 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፲፮(16)

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ስድስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር ።

ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው ። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ።

የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው ። እነርሱም "የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል" አሏት ። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ ።

የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት "የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ"። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ።

አባቷ ዳዊትም "ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች" እያለ በበገና አመሰገናት ። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች ።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ።

ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና "የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል" አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ።

ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው "አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን"።

በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም "በመፍራት ቁሙ" አለ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።

ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት "በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው"።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው "ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ"። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ።

የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

++++++++++++++++++++
ነሐሴ ፲፮(16) ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም(ፍልሰቷ፣ ትንሳኤዋና እርገቷ)
፪. ቅዱሳን ሐዋርያት
፫. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ጊጋር ሶርያዊ(ሰማዕት)

ወርኀዊ በዓላት
፩. ኪዳነ ምህረት(የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም)
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ(የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮጵያ(የቅ/ላሊበላ ወንድም)
፬. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
፭. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፮. አባ ዳንኤል ጻድቅ
፯. ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ(ወንጌሉ ዘወርቅ)

++++++++++++++++++++
ወደ ማደሪያዎቹ እንገባለን።
እግሮቹ በሚቆሙበት ሥፍራ እንሰግዳለን።
አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ።
አንተና የመቅደስህ ታቦት።
ካህናቶችህ ጽድቅን ይልበሱ።
ቅዱሳንህም ደስ ይበላቸው።
ስለ ባሪያህ ስለ ዳዊት..."
(መዝ.131(132)፥7)

ወዳጄ ሆይ! ተነሺ።
ውበቴ ሆይ! ነዪ።
በዓለት ንቃቃትና በገደል መሸሸጊያ ያለሽ ርግብ ሆይ!
ቃልሽ መልካም፡ ውበትሽም ያማረ ነውና፡
መልክሽን አሳዪኝ።
ድምጽሽንም አሰሚኝ።
(ማሕልየ መሓልይ. 2፥13)

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ይላኩ...

Instagram + Facebook + Telegram
YouTube - www.youtube.com/c/DebreSelamBealeEgziabhier
366 views11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 10:29:58 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


መንፈሳዊ ጉባኤ

እንሆ የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት ዛሬ እሑድ ነሐሴ 15/2014 በአይነቱ ልዩ የሆነ "የህይወት ልምድ ልውውጥ" መርሐግብር አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል።
በእለቱም፦ ወጣትነታቸውን በአገልግሎት ያሳለፉ፤ አሁንም በአገልግሎት ላይ ያሉ፤ በአለማዊውም ስኬታማ የሆኑ ደክተር እህት ወንድሞቻችን ተጋብዘዋል።

እርስዎም በዕለቱ በመገኘት የመርሐ ግብራችን ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጠርተንዎታል፡፡

➤ ቀን ፡ ዛሬ እሑድ ነሐሴ 15/2014
➤ ሰዓት፡ ከቀኑ 8:00
➤ ቦታ ፡ በደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት አዳራሽ

አዘጋጅ ፡ የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ይላኩ...

Instagram + Facebook + Telegram
YouTube - www.youtube.com/c/DebreSelamBealeEgziabhier
307 views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 22:26:58
“ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል።”
  — መዝሙር 89፥12
    የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት የቡሔን በዓል እንዲህ በደመቀ እና ትዉፊቱን በጠበቀ መልኩ አክብሮ ዋለ።
  13/12/2014
የበዓሉ የፎቶ ቅኝት በጥቂቱ
    ጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከረድኤት በረከቱ ያሳትፈን
446 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ