Get Mystery Box with random crypto!

ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ሴት ተማሪዎች የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና ተሰጠ ======== | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ሴት ተማሪዎች የስራ ፈጠራ ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

================

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ፡- | ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ከነርቸር ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ከሐምሌ 8-11/2015 ዓ.ም ለ4 ተከታታይ ቀናት ለ105 ተመራቂ ሴት ተማሪዎች የስራ ፈጠራ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ መከኒካልና ኢንደስትሪያል ትምህርት ክፍል መምህር እሱባለው ነጋ ወጣቶች የተቀጣሪነት መንፈስን ብቻ ይዘው ቅጥርን መጠባበቅ ልምድ እያደረጉት በመምጣታቸው ከዚህ አስተሳሰብ ወጥተው ከራቸው አልፈው ለሌሎች የስራ እድል ፈጣሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ስልጠናዎችን እየሰጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ ስልጠናውም ተማሪዎች የስራ ፈጠራ መንፈስን እንዴት ማምጣት እንደሚቻል፣ የተጠኑ ቢዝነሶች አጀማመር ፣ ትርፍና ኪሳራን እንዴት መለየት እንደሚቻል እና የቢዝነስ ሀሳብ ይዘው የገንዘብ እጥረት ለገጠማቸው የስራ መጀመሪያ ገንዘብ እንዴት ማፈላለግ እንደሚቻል ፣ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ተማሪዎችም በቀላሉ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ያስችላል ብለዋል፡፡

ሰልጣኝ ተማሪ ትዕግስት ግዛቸው ስልጠናው የመውጫ ፈተና ፈጥሮባቸው የነበረውን ጭንቀት የሚያስረሳና ለስራ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን ገልፃ ይህን እድል ላመቻቹላቸው አካላት እና ስልጠናውን ለሰጧቸው መምህራንም ምስጋናዋን አቅርባለች፡፡


ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!

ለአዳዲስ መረጃዎች


#ቴሌግራም፡ https://bit.ly/3HbDPCB

# ፌስቡክ፡ https://bit.ly/3mYfnNW

#ዩቲዩብ፡ https://bit.ly/3L73hu3

#ድረ_ገጽ፡ www.dmu.edu.et