Get Mystery Box with random crypto!

በዩኒቨርሲቲያችን ድጋፍ በመከናወን ላይ የሚገኘው የዋሻ አንባ ገዳም (እሙሃይ ገዳም ) የጎርፍ ውሃ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

በዩኒቨርሲቲያችን ድጋፍ በመከናወን ላይ የሚገኘው የዋሻ አንባ ገዳም (እሙሃይ ገዳም ) የጎርፍ ውሃ መፋሰሻ (ዲች) ግንባታ ሂደትና የስራ አፈፃፀምም ተጎበኘ

ደማዩ :- | ሰኔ 25/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት|

በማቻከል ወረዳ የሚገኘው ዋሻ አንባ ገዳም (እሙሃይ ገዳም) የደብረ ማርቆስ ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) ፣ ሌሎችም የዩኒቨርሲቲያችን ከፍተኛ አመራሮች እና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አካላት በተገኙበት በገዳሙ ውስጥ በዩኒቨርሲቲው ድጋፍ በመከናወን ላይ የሚገኙ የተፈጥሮ ሐብት ጥበቃ ስራዎች ተጎብኝተዋል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከገዳሙ የመሬት አቀማመጥ ጋር በተያያዘ እያጋጠመ ያለውን የመሬት መንሸራተት ለመከላከል የተፈጥሮ ሃብት ጥብቃ ስራ ላይ ትኩረት እንደተደረገ ጠቁሞ በ 5.2 ሚልዮን ብር ወጭ ወደ 1 ኪ .ሜ የሚጠጋ ርዝመት ያለው የጎርፍ ውሃ መፋሰሻ (ዲች) ግንባታ እየተከናወነ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

በጉብኝታቸውም እየተከናወኑ የሚገኙ የእንስሳት እርባታ እና አትክልትና ፍራፍሬ ችግኞችን ተመልክተዋል።

በገዳሙ ውስጥ በተከናወኑ የልማትና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራዎች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ሽልማትና የየእውቅና መርሐ ግብር ተከናውኗል።



ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!

ለአዳዲስ መረጃዎች


#ቴሌግራም፡ https://bit.ly/3HbDPCB

# ፌስቡክ፡ https://bit.ly/3mYfnNW

#ዩቲዩብ፡ https://bit.ly/3L73hu3

#ድህረ ገጽ፡ www.dmu.edu.et