Get Mystery Box with random crypto!

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር የሚፈቱ ፣ ለትውልድ የሚተላለፉ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር የሚፈቱ ፣ ለትውልድ የሚተላለፉ ፣ ሊታዩና ሊጨበጡ የሚችሉ የተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጅክቶችን እየሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ

=========

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ ሚያዝያ 21/2015 ዓ.ም |ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት| ዩንቨርሲቲው ከመማር ማስተማሩ ስራ ባሻገር የማህበረሰቡን ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ ፕሮጀክቶች ላይም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

በዛሬው ዕለትም በሸበል በረንታ የተቀናጀ የማህበረሰብ አቀፍ ልማት ፕሮጀክት በተከናወኑ ተግባራት፣ ባጋጠሙ ችግሮች እና ወደ ፊት በሚከናወኑ እቅዶች ዙሪያ የዩኒቨርሲቲው የፕሮጀክቱ አባላት ፣ የአግሪሰርቪስ ኢትዮጵያ ሰራተኞች ፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣ ከጠቅላላ አገልግሎት ፣ከፋይናንስ ፣ከግዥናኦዲት ባለሙያዎች በተገኙበት የአንድ ዓመት የስራ እንቅስቃሴ ግምገማ ተካሂዷል ፡፡

የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አስካለማርያም አዳሙ (ዶ.ር ) እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ባሻገር የአካባቢውን ማህበረሰብ ችግር የሚፈቱ ፣ለትውልድ የሚተላለፉ፣ ሊታዩና ሊጨበጡ የሚችሉ የተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ ፕሮጅክቶችን እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

ከደብረ ማርቆስ ዩቨርሲቲ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ መብራቴ በላቸው ( ዶ.ር ) ፕሮጀክቱ በ2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት የሚተገበር እንደሆነ ጠቁመው የማህበረሰቡን ህይወት ማሻሻልና መቀየር ዓላማ እንዳደረገ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ይህ ፕሮጀክት በሸበል በረንታ ወረዳ ዘጠኝ ቀበሌዎች እንደሚተገበርና ከዩኒቨርሲቲው ከምህንድስና ፣ ከግብርናና ተፈጥሮ ሃብት ፣ ከጤና ሳይንስ ፣ ከስነ - ባህሪ ተቋማትና ኮሌጆች የተውጣጡ ምሁራን እንደተሳፋበት ጨምረው ገልፀዋል ፡፡

በአግሪ ሰርቪስ ኢትዮጵያ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች አስተባባሪ አቶ ተመስጌን ወንድይፍራው በበኩላቸው እንደገለፁት ፕሮጀክቱ የማህበረሰቡን ንቃተ ህሌና የሚያጎለብቱ የስልጠናና የምክክር መድረክ በማመቻቸት እና የምግብ ዋስትናን ለማስጠበቅ በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ዘርፎች ተሳታፊ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰው ከእነዚህም ውስጥ በተፈጥሮ ሃብት ልማት ዘርፍ የተሸረሸሩና የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማልማት የአፈር ለምነትን ማስጠበቅ ፤ የውሃ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ ግድቦችን መስራት፣ ለወጣቱ የስራ ዕድል መፍጠር ፣ ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን በማስቀረት ዙሪያ የተከናወኑ መሆናቸውን ጨምረው አብራርተዋል፡፡

በፕሮጀክቱ በቀጥታ ተጠቃሚ የሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችም በጠቅላላው 5 ሺህ ሰባት መቶ ቤተሰቦች እንደሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም 2 ሺህ አራት የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ገልፀዋል ፡፡

በስራው ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችም በዝርዝር የተዳሰሱ ሲሆን የፕሮጀክቱ የስምምነት ሂደት መጓተት ፣ የአጋሮች አብሮ ለመስራት ቁርጠኛ አለመሆንና ወደ ተግባር አለመግባት፣ የግንባታ ቁሳቁሶች በቀላሉ አለማግኘት የሚሉትን ዋናዋና ችግሮች መሆናቸውን አንስተዋል ፡፡

በማጠቃለያ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተው ሀሳባቸውን የሰጡት የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ታፈረ መላኩ ( ዶ.ር ) የተሰሩት ስራዎች ጥሩና ለማህበረሰቡ እጅግ አስፈላጊ መሆናቸውን ገልፀው ይህ ውይይት የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት መካሄዱ ያለፈውን ሂደትና የመጣውን ውጤት አመዛዝኖ ለወደፊቱ ይበልጥ ለስራ መነሳሳትን ይፈጥራል ብለዋል ። በተጨማሪም የተሰጡ አስተያየቶችን ተቀብሎ በማሰተካከል እና ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት ከዚህ የበለጠ መስራት ተገቢ መሆኑን አሳስበዋል ፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!

=============

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች


#ቴሌግራም፡ https://bit.ly/3HbDPCB

#ፌስቡክ፡ https://bit.ly/3mYfnNW

#ዩቱዩብ፡ https://bit.ly/3L73hu3

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et